by Mistre | May 26, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories
ከሰውነታችን 70 በመቶ ያህሉ ውሃ ነው። የእኛ ሰውነት ብቻም ሳይሆን የምድርም ተመሳሳይ ድርሻ የተሸፈነው በውሃ ነው። ውሃ ከሰው ልጅም ሆነ ከማንኛውም የተፈጥሮ ውጤት ጋር ትልቅ ቁርኝነት አለው። እኔ እንኳን ለዛሬ ስለ ውሃ ምንነት እና ጥቅም ሳይሆን ላካፍላችሁ የፈለግኩት፤ አንድ የጃፓን ተመራማሪ በውሃ ላይ ያደረጉትን ምርምር እና ምናልባትም ለራሳችን ያለንን አመለካከት እስከወዲያኛው ሊቀይር የሚችለውን ግኝታቸውን ነው።...
by Mistre | May 22, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories
ልጅ እያለን፤ ለደስታ ያለን አመለካከት የተለየ ነበር። ለመሳቅ ምክንያት አያሻንም ነበር፤ ለመደሰት ልጅ ከመሆናችን የዘለለ መስፈርት አልነበረንም ነበር፤ ደስታ ግብ ሳይሆን ከማንነታችን ጋር፤ ከልጅነታችን ጋር አብሮ የተዋሃደ የተፈጥሮ ጸጋ ነበር። እድሜ ሲጨምር እና ማደግ የሚሉት ፈሊጥ ሲመጣ እኛ ለደስታ ያለን አመለካከት ተለወጠ (ነገር ግን ደስታ ምንነቷ የተለወጠ ነው የሚመስለን) ። አንድ ጸሃፊ የልጅነትን መልካም...
by Mistre | May 19, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories
አልፎ አልፎ ከምሰማቸው ተራናጋሪዎች ወይም አስተማሪዎች ማለት እችላለው፤ ሳድጉሩ የተባለው ህንዳዊው ዮጊ ( sadhguru) አንዱ ነው። ዛሬ ደስ የሚል መልዕክት ሰማሁኝ እና ላካፍላችሁ ፈለግኩኝ። በቅድሚያ እራስን ስለመለወጥ ያለን አስተሳሰብ ምንድን ነው? እራሳችንን መቀየር አለብን ስንልስ ምን መለወጥ እንደምንፈልግ እናውቃለን? መለወጥ የምሻውስ ሰዎች እንዲወዱን እና እንዲቀበሉን ብለን ነው ወይስ አሁን ያለንበት ህይወት...
by Mistre | May 12, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት
ብዙዎቻችን፤ በፍቅር ግንኙነታችንም ሆነ በተለያዩ ግንኙነቶቻችን ውስጥ፤ ፍቅርን ያለቦታው እናስሰዋለን፤ አለመፍለቅቂያው እንፈልገዋለን። ለዚህም ነው ፍቅር ደብዛው የጠፋ የሚመስለው። አንድ የውጪ ሃገር መምህር ይህንን ደስ በሚል ቋንቋ እንዲህ ገልጸውታል “በአህያው ጀርባ ላይ ሆነው አህያውን እንደመፈለግ ማለት ነው” ሲሉ። ፍቅርን የምንፈልግ ሰውች ልክ አህያው ላይ ተቀምጦ አህያው ወዴት ነው ብሎ...
by Mistre | May 11, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት
እንዴት አድርጌ እንደማርግዝዥ ባላውቅም፤ ልወልድሽ አስቤያለው። ስቃይሽ አልገባኝ ቢል መስዋትነትሽን ባልረዳው፤ ውለታሽን መክፈል ቢያቅተኝ፤ ጥልቅ የሆነው እናትነትሽን ለመመርመር ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ወሰንኩኝ። ምን ላድርግ ፍቅርሽን እኮ የሰው ህሊና ሊመረምረው ፤ ውለታሽን የሰው ልብ ሊሸከመው አይችልም። እንኳን ሰው እኔ የስጋሽ ክፋይ አልተረዳሁትም…….እናም ልወልድሽ ወሰንኩኝ።...
Recent Comments