Queen Sheba loads forty mules with gold bricks
As gift for Solomon …..
What foolishness is to take gold?
To Solomon, when the dirt of his land is gold.
You who think to offer your intelligence, reconsider.”- Rumi
የምትሰጡትን ነገር ልብ በሉ (ትርጉም)
ያቺ ንግሥት ሳባ፤ ጠቢቡን ሰለሞን በጎበኘች ጊዜ
አነውልሏት ነበር? የምኞት የናፍቆት የጉጉት አባዜ?
አልሰማ ብላ ነው? ወይስ መካሪ አጥታ
ለሸክም የሚከብድ ወርቅ ይዛ መሄዷ፤ ለክብሩ ስጦታ
ወርቅ ለሰለቸው
ወርቅ እየረገጠ፤ ወርቅ ሆኖበት ቤቱ
ማላገጥ አይሆንም? ወርቅን እጅ መንሻ ስጦታ መስጠቱ?
አንዳንዴ……
ለሰው እጅ መንሻ የገበርነው ግብር
እውቀት፤ ጥበብ፤ ፍቅር፤ ሙገሳና ክብር
ለእኛ ውድ ሆኖ እጅ…..ግ አግዝፈነው
ተቀባዩ እጅ’ ላይ ፤ ተራ ኢምንት ሆኖ፤ ሲረክስ አየነው!
(ትርጉም-በሚስጥረ አደራው)
0 Comments