“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ዛሬ ደግሞ እስቲ እኔ ልውለድሽ

by | May 11, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 0 comments

 

እንዴት አድርጌ እንደማርግዝዥ ባላውቅም፤ ልወልድሽ አስቤያለው። ስቃይሽ አልገባኝ ቢል መስዋትነትሽን ባልረዳው፤ ውለታሽን መክፈል ቢያቅተኝ፤ ጥልቅ የሆነው እናትነትሽን ለመመርመር ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ወሰንኩኝ።  ምን ላድርግ ፍቅርሽን እኮ የሰው ህሊና ሊመረምረው ፤ ውለታሽን የሰው ልብ ሊሸከመው  አይችልም። እንኳን ሰው እኔ የስጋሽ ክፋይ አልተረዳሁትም…….እናም ልወልድሽ ወሰንኩኝ።

አየሽ ምጥሽን መረዳት ቢሳነኝ፤ ስቃይሽን፤ ውለታሽን፤ መስዋትነትሽን መመዘኑ ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ተመኘው። ከንቱነቴ ነው ይህን ያስመኘኝ……ባለእዳ መሆኔ ህሊናዬን ዘወትር ስለሚያሳምመው። ፍቅርሽን በተግባርሽ ባየውም፤ ጥልቀቱን መረዳት ግን አልተቻለኝም። ረቂቅ ሆንሽብኝ፤ እናትነት እንዴት እንዲህ ውስብስብ ሆነ?

ማን እንደተናገረው የማላውቀው አንድ አባባል ትዝ አለኝ “እግዚያብሄር በሁሉም ቦታ ላለመሆን ሲል እናትን ፈጠረ” የሚል። ያለምንም ማጋነን እውነት ነው። ከፈጣሪ በታች እጅግ ጥልቅ የሆነብኝ ያንቺ ፍቅር ነው። ፈጣሪስ ለሰው ልጅ የከፈለውን  መስዋትነት ሁሉ በጥበቡ ቻለው፤ እማዬ አንቺ እንዴት ቻልሽው? ይህ ምስጢር ግራ ቢገባኝ እኮ ነው፤ ልውለድሽ ያልኩት። ቢያንስ በትሹ ውለታሽን ለመክፈል እንዲቻለኝ።

ሁሉም ሰው በናቱ ይታበያል….ሁሉም ሰው የራሱን እናት የተለየች እንደሆነች ሆኖ ይመሰክራል፤ ሁሉም የናቱ ፍቅር የናቱ መስዋትነት፤ የናቱ መከራ፤ ከየትኛውም እናት የበለጠ እነደሆነ ይናገራል። ምን እንናድርግ፤ እናትነትን የሚያስረዳ  ነገር ብናጣ እኮ ነው። እና እኔም በናቴ ብታበይ …ግብዝነቴን አትታዘቡት

እማዬ እንዳልኩሽ እንዴት እንደማረግዝሽ አላውቅም…….ልወልድሽ ግን ወስኛለው። ብለፋ፤ ብጥር፤ አንቺ  የደረስሽበት የደግነት ጣሪያ ላይ መድርስ አልተቻለኝም። ከብዙ ማሰብ በኋላ አንድ ድምዳሜ ላይ ደረስኩኝ፤ ምንም አይነት መለካም ሰው ብሆን፤ ምንም አይነት አስተሳሰበ ምጡቅ ሰው ብሆን፤ የእናትን ያህል ፍቅር እና ደግነትን እንዲሁም ቻይነትን መጎናጸፍ አይቻልም። በቃ የእናትን ያህል አፍቃሪ ለመሆን  እናት መሆን ግድ ይላል። ማንም ተራ የሰው ልጅ ሊችለው አይችልም።

ዛሬ እንዲህ ኩርምት ብለሽ ሳይሽ፤ ከፋኝ…..ልጅነቴን፤ ጠላሁት፤ ለስቃይሽ መንስኤ ስለመሰልኝ፤ ወጣትነቴንም እረገምኩት፤ እራስ ወዳድ መሆኔን ስላሳየኝ። እማዬ ያንቺ አይኖች ሞጭሙጨው ፤ የኔን ብርሃን አጎሉት፤ ያንቺ ጎንጮሽች ጎድጉደው የኔን ጉንጮች ሞሉት፤ ያንቺ መዳፎች ቆርፍደው የኔ መዳፎች ለሰለሱ፤ ያንቺ ተረከዞች ተቀርድደው የኔ ተረከዞች ተዋቡ፤ ያንቺ እውቀት ተገታ የኔ አይምሮ እንዲሰፋ። ታዲያ እማዬ…..የኔ የምለው እኔነቴ ምንድን ነው? አሁንም እደግመዋለው…..ፋጣሪ ለሰው ልጅ የከፈለውን መስዋትንት በጥበቡ ቻለው……እናት ግን እንዴት ቻለችው?

እመኚኝ ፈጣሪ ላንቺ እድሜ ለኔ ብርታቱን ይስጠን እንጂ እወልድሻለው። ስዎች ይህን ሃሳቤን ሲሰሙ ተሳለቁብኝ። ልጅ እንዴት እናቱን ይወልዳል? ብለው ተዘባበቱብኝ። እኔ ግን መላ አላጣም……ስቃይዋ ከንቱ እንዳልቀረ ባሳውቃትስ? ሰው እንደወለደች እንድታውቅ ሰው ሆኜ ባሳያትስ? ህመሟ ልፋትዋ ውሃ እንዳልበላው በስራዬ ብመሰክርላትስ? ደግነቷን ሳልበርዝ በደሜ እንዳቆየሁት ባረጋግጥላትስ? ዳግም ወለድኳት ማለት አይደለም?

 

 

 

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *