“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መምህር ውሃ!!!

by | May 26, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ከሰውነታችን 70 በመቶ ያህሉ ውሃ ነው። የእኛ ሰውነት ብቻም ሳይሆን የምድርም ተመሳሳይ ድርሻ የተሸፈነው በውሃ ነው። ውሃ ከሰው ልጅም ሆነ ከማንኛውም የተፈጥሮ ውጤት ጋር ትልቅ ቁርኝነት አለው። እኔ እንኳን ለዛሬ ስለ ውሃ ምንነት እና ጥቅም ሳይሆን ላካፍላችሁ የፈለግኩት፤ አንድ የጃፓን ተመራማሪ በውሃ ላይ ያደረጉትን ምርምር እና ምናልባትም ለራሳችን ያለንን አመለካከት እስከወዲያኛው ሊቀይር የሚችለውን ግኝታቸውን ነው።

ዶ/ር ሙሳሮ ኢሞቶ የጃፓን ተወላጅ ናቸው።  በሺህ 1992, Doctor of Alternative Medicine ከተባሉ በኋላ፤ ከውሃ ጋር ያላቸው ቁርኝነት በእጅጉ ጨመረ። በምድራችን ላይ ውሃ ያያዘውን ሚስጢር እንደ ሳይናሳዊ ተመራማሪ ብቻም ሳይሆን ከዛ በላቀ መልኩ ለማጥናት ሞከሩ። እንግዲህ ከብዙ ምርምር በኋላ ነው ዶ/ር ኢሞቶ በአለም ላይ ሁሉ ተቀባይነት ያገኘውን ብሎም ሁሉን ያስደመመውን ውጤታቸው ይዘው ብቅ ያሉት።

ብዙዎቻችን አስተሳሰባችን እና ለኛ ያለን አመለካከት ምን ያህል ህይወትቻንን እንደሚጎዳው ደጋግሞ ቢነገረንም፤ ለራሳችን ቀና አመለካከት ለማዳበር ቀላል አልሆነልንም ወይም እምብዛም ጥረት አላደረግንም። ይልቁንም ለውድቀታችን እና ለእንቅፋቶቻችን ሌሎችን መውቀስ ተገቢ አድርገነዋል። እራሳችን ለራሳችን ከምንነግረው አፍራሽ ንግግር ይልቅ የሰዎች አስተያየት ጎልቶ እንደ ችግር ይታየናል። እውነታው ግን ከሌሎች ሰዎች ይልቅ የራሳችን ጠላት እራሳችን መሆናችን ነው።

ይህ የዶ/ሩ ምርምር የእለት ተለት ኑሮዋችንን፤ አስተሳሰባችንን፤ ከአንደበታችን የሚወጡትን ቃላቶች፤ አትኩሮታⶭንን ልብ ብለን  እንድንቃኝ ያደርገናል። ምርምሩ በውሃ ላይ መደረጉ ዝም ብሎ በአጋጣሚ የሆነ ነገር አልነበረም፤ የሰው ልጅ ከውሃ ጋር ያለውን ቁርኝነት ከግምት በማስገባት እንጂ።

ምርምሩ

ዶ/ር ኢሞቶ ንጹህ ውሃን በመቅዳት በተለያየ እቃ ከፋፍለው ያስቀምጣቸዋል (ለዚህ ጽሁፍ በተላያየ የጠርሙስ እቃ በማለት እናቀርባለን)። ውሃውን በተለያየ ብርጭቆ ከፋፍለው ካኖሩት በኋላ በያንዳንዱ እቃ ላይ የተለያየ መልክዕክት ያለው ጽሁፍ አኖሩበት። ጽሁፎቹ ገሚሱ መልካም መልዕክቶችን ገሚሱ ደግሞ አሉታዊ  መልዕክቶችን የያዙ ነበሩ።  በላያቸው መልዕክት መጻፍ ብቻም ሳይሆን መልዕክቱ ላይ ትኩረት ተሰጠበት። በመቀጠል ጠርሙሶቹን በሙሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ በረዶነት እንዲቀየሩ ተደረገ። በመጨረሻ የተለያየ መልዕክት የያዙት በረዶዎች በማጉያ መሳርያ ወይም ማይክሮስኮፕ እንዲታዩ ተደረገ።በሚያስገርም ሁኔታ መልካም መልዕክት የተደረገባቸው ጠርሙሶች ውስጥ የተገኙት በረዶዎች፤ በውስጣቸው የሚያማምሩ ቅርጽ ያላቸው  የውሃ ሞሎኪውሎችን ይዘው ተገኙ። በአንጻሩ አሉታዊ እና መጥፎ ጽሁፍ የሰፈረባቸው በረዶዎች ምንም የማይማርክ እና ዝብርቅርቅ ቅርጽ ያዙ። ከጽሁፎቹ መካከል “ፍቅር” “ጸሎት” “አዶልፍ ሂትለር” “አልወድህም” የመሳሰሉት ይገኙበታል።

ይህ ቀላል የምርምር ውጤት፤ እራሳችንን እንዴት መቅረብ እንዳለብን የሚያሳስብ ይመስለኛል። ውስጣችን እና መንፈሳችን የሚይዘው ቅርጽ፤ እንደውሃው በራሳችን ላይ ባለን አመለካከት ይወሰናል። ይህች ምድር ብዙ ተዓምራቶችን አሳይታናለች፤ ሁሉም ተዓራቶች ግን  በእምነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እኔ እና እናንተም ውስጥ ተዓምር ፈጣሪ ሃይል አለ። ይህ ሃይል ሁሌም ቢሆን በስራ ላይ ነው፤ መልካም አስተሳሰብ ኖረንም አሉታዊ አመለካከት ያዝንም፤ በአስተሳሰባችን መጠን እና ይዘት መሰረት ውጤቱን ያሳየናል። ክፉ አመለካከቶችን በያዝን ቁጥር፤ ተዓምር ሰሪው የሰውነት ሃይላችን፤ የሚያደላው እና እየሳበ የሚያቀርብል ክፉ ነገሮችን ነው። ምክንያቱም በህይወታችን እውነት የሚሆኑት ነገሮች በሙሉ ደጋግመን የምናስባቸው እና ትኩረት የምንሰጣቸው ነገሮች ናቸው። ለምሳሌ እኔ ትምህርት አይገባኝ ብሎ ደጋግሞ ለራሱ የሚነግር ሰው፤ በሂደት እውነትም ትምህርት አይገባውም። ትምህርት እንዳይገባው ሆኖ ስለተፈጠረ ሳይሆን ለራሱ የመረጠው እውነታ ይህ ስለሆነ ብቻ።

ለዚህ ነው የዶ/ር ኢሞቶን ምርምር ምንም እንኳን ቆየት ቢልም ላቀርበው የወሰንኩት። በአይምሮዋችን መልካም አስተሳሰቦችን ስንዘራ ደስ የሚል ነፍስን እና ህይወትን መፍጠር እንችላለን። ነገር ግን በአንድ ቀን ውሳኔ የሚለወጥ ነገር አይደለም። ደጋግመን ደጋግመን ተጋባራዊ በማድረግ ባህሪ ልንዳርገው ይገባል እንጂ። ለሰውም ሆነ ለራሳችን የምንሰጠውን አስተያየት በጥንቃቄ ማጤን አለብን። ይህ ማለት መልካም ነገሮችን ብቻ በመነጋገር እንሸነጋገል ማለቴ አይደለም። ግን አሉታዊ አነጋገሮችን ብቻ ሃሳብ መግለጫ አድርገን አንቁጠር ማለቴ ነው። አንዳንዴ በየማህበራዊ ድረገጹ ላይ አስተያየቶችን ሳይ ድንቅ ይለኛል፤ ከመልዕክቱ ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ጸያፍ ነገር ሰፍሮ ሳይ ለተሳዳቢው ሰው አዝናለው፤ “አፍህን ስትከፍት ማንነትህን አየሁት” የሚል የቆየ አባባል አለና።

እናም ወዳጆቼ ከዚህች አጭር ጽሁፍ ጥቂት ነገር እንኳን ብትወስዱልኝ ደስ ይለኛል። ቢያንስ የህይወታችን መልክ ለራሳችን ባለን አመለካከት እንደሚወሰን እናስተውል። እራሳንን ካለወደድነው፤ የማይወደድ ማንነት መያዛችን ግድ ነው። እራሳችንን ካላከበረነው የማይከበር ማንነት መውረሳችን እውነት ነው። ስለዚህ የውሃው ጠርሙስ ላይ እንደሰፈረው መልዕክት……………እኛ ጭንቅላት ላይ የሰፈረው መልዕክት ምን ይሆን? ብለን እራሳችንን እንጠይቅ።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *