“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

አዋቂነት….. ሞኝነት?

by | May 22, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ልጅ እያለን፤ ለደስታ ያለን አመለካከት የተለየ ነበር። ለመሳቅ ምክንያት አያሻንም ነበር፤ ለመደሰት ልጅ ከመሆናችን የዘለለ መስፈርት አልነበረንም ነበር፤ ደስታ ግብ ሳይሆን ከማንነታችን ጋር፤ ከልጅነታችን ጋር አብሮ የተዋሃደ የተፈጥሮ ጸጋ ነበር። እድሜ ሲጨምር እና ማደግ የሚሉት ፈሊጥ ሲመጣ  እኛ ለደስታ ያለን አመለካከት ተለወጠ (ነገር ግን ደስታ ምንነቷ የተለወጠ ነው የሚመስለን)  ። አንድ ጸሃፊ የልጅነትን መልካም ገጽታ እንዲህ ይገልጸዋል  “ሁሌም የሚቆጨኝ እንደ ልጅነቴ ብልህ አለመሆኔ ነው” ሲል።

ዛሬ ከልጅነት አለም እርቀናልና ለመሳቅ ምክንያትን እንሻለን፤ ለመደሰት አላማ እና ግብ እንፈጥራለን። ምክንያቱም ደስታ ተለፍቶ የሚደረስበት የህይወት መንገድ ስለሚመስለን። ለዚህ ነው ጸሃፊው እንደ ልጅነቴ ብልህ አለመሆኔ ይቆጨኛል ያለው። እስቲ አስታውሱ አንዳንዴ ስዎችን ደስተኛ መሆናቸውን ስትጠይቋቸው “ምን የሚያስደስት ነገር አለ” ብልው የሚልሱት ብዙዏች ናቸው። አንዳንዶቻችን ያሰብነውን ስራ እስክንይዝ፤ የምንፈልገውን ገንዘብ እስክናገኝ፤ የምንወደውን ሰው በእጃችን እስንካስገባ፤ የምንፈልግበት የህይወት ደረጃ ላይ እስክንደርስ፤ እያልን ደስታችን ቤታችን እንዳይገባ እንከለክለዋለን። ሞኝነታችን እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፤ ምን አልባት ያሰብነውን ብናገኝ እንኳን ላንደሰት እንችላለን፤ ምክንያቱም ደስታ ከውጫዊ ነገሮች ጋር አብሮ የሚቋጠር ቁስ ባለመሆኑ። ደስታ ሁሌም ከበራችን ቆሟል በቀጠሮ አላስገባ ብለነው ነው እንጂ።

ወደ ደስታ የሚውስድ ምንም አይነት መንገድ የለም፤ ይልቁንም ደስታ ወደምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰን ብቸኛው መንገድ ነው እንጂ። ምንም አይነት የህይወት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳን እራሳችንን ለማስደሰት ከወሰንን፤ እና እንደ ልጅነታችን ብልህ መሆንን ካወቅንበት ለመደሰት ብዙም ባልለፋን ነበር። አሁን ላነሳሁት ነጥብ ማስረጃ የሚያሻን ከሆነም ዙሪያችንን እንቃኝ፤ ቤቱ የሞላለት ሁሉ ደስተኛ እንዳይደለ ብዙ ምስክሮች በዙሪያችን አሉ። ይህን ሚስጥር የተረዱ ብልሆች ልጆች ብቻ ናቸው፤ ነፍስ ማወቃችን ሞኝ አደረገን እና የህይወት ውሉ ጠፋብን። እውቀታችን አላዋቂነታችንን ይበልጥ አጎላው፤ ፍልስፍናችን ኑሮዋችንን እንደማቅለል፤ ይበልጥ አወሳሰብብን። ለደስታ ያለን አመለካከት ገዘፈና፤ ደስተኛ ለመሆን የምንከፍለው ትልቅ መስዋትነት እንዳለ እራሳችንን አሳመንንን፤እውነታው ግን አሁንም ልክ እንደልጅነታችን ነው። እንደ ልጅነታችን ብልህ መሆን ያሻናል፤ አዋቂነት ሞኝነቱ ይበዛልና። እንደው ብናስተውለው እኮ፤ የሰው ልጅ ሁሉ ከልጅነት መልካም ባህሪው ባይላቅቅ፤ አለም እንዲህ በክፋት ባልተጨማለቀች ነበር። ምድር ላይ የደረሱ ጥፋቶች ሁሉ፤ ሰው በአዋቂነቱ የፈጸማቸው ናቸው።  አሁን የተጠናወቱን የክፋት ባህሪዎች ሁሉ፤ ከአዋቂነታች ጋር አብረው ያደጉ እኩይ ማንነቶች ናቸው።

እናም ሁሌም አንድ ነገር ለራሳችን እናስታውስ ወደ ደስታ የሚወስድ ምንም መንገድ የለም፤ ይቅል ደስታ ወደፈለግንበት መንገድ የሚወስደን ሰፊው ጎዳና ነው። ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር፤ ያኔ ፈጣሪ ይጎደለውን በተዓምሩ ይሞላዋል። ሌላው ደግሞ እንደልጅነታችን ወደ ብልህነት ለመመልሰ እንታገል፤ የዋሁ የልጅነት ህይወት እውነተኛ የሰውልጅ ተፈጥሮ፤ ፈጣሪን የሚመስለው ማንነቱ ነውና።

 

 

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *