“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

እራስህን ሆነህ ፍካ……

by | May 19, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

አልፎ አልፎ ከምሰማቸው ተራናጋሪዎች ወይም አስተማሪዎች ማለት እችላለው፤ ሳድጉሩ የተባለው ህንዳዊው  ዮጊ ( sadhguru) አንዱ ነው። ዛሬ ደስ የሚል መልዕክት ሰማሁኝ እና ላካፍላችሁ ፈለግኩኝ። በቅድሚያ እራስን ስለመለወጥ ያለን አስተሳሰብ ምንድን ነው? እራሳችንን መቀየር አለብን ስንልስ ምን መለወጥ እንደምንፈልግ እናውቃለን? መለወጥ የምሻውስ ሰዎች እንዲወዱን እና እንዲቀበሉን ብለን ነው ወይስ አሁን ያለንበት ህይወት ለራሳችንን ስላልተመቸን? ፍጹም ለመሆን ይሆን እየጣርን ያለነው?

ሰው ነንና ሌሎች ስለኛ የሚያስቡት ነገር በጣም ያስጨንቀናል፤ ተቀባይነታችን፤ ያሳስበናል። እናም ከሰልፋኛው ጋር አብሮ ለመሄድ ስንል እራሳችንን አለተፈጥሮው እንዲሆን እናስገድደዋለን። ከብዙሃኑ ጋር ለመቀላቀል ስንል፤ ማንነታችንን እናስጨንቀዋልን፤ ከጠባቡ የኑሮ ስርዓት እንዲገባ ስንል ብቻ፤ ማንነታችንን በይሉንታ እናቀጭጨዋለን። እንዲያም ሆኖ፤ ደስተኞች አንሆንም፤ ምክንቱም ያልሆኑትን ሆኖ ደስታን መጠበቅ ከባድ ነውና። ይህ የሚያሳስባችሁ እና መልስ ያጣችሁለት ነገር ከሆነ፤ ይህችን የመምህሩን ምሳሌ እንካችሁ…..

ጽጌሬዳ ሲነሳ ምን ትዝ ይላችኋል? እርግጠኛ ነኝ ውበት! ጽጌሬዳ በሁላችንም ህሊና ውስጥ ከውበት ጋር የተቆራኝ እድለኛ የተፈጥሮ ውጤት ነው። ማንም ሰው የጽጌሬዳን እንከን ሲያወጣ ሰምታችሁ አታውቁም። ግን ጽጌሬዳ አናቷ ላይ ካስቀመጠችው እንቡጥ ይልቅ፤ በላይዋ የተሸከመችው እሾህ አይበዛም? ታዲያ የእሾህ አባባ መባሉዋ ቀርቶ ጽጌሬዳ እንዴት ተባለች? ማንም  ሰው ጽጌሬዳን ሲያስብ ውብ የሆነውን እንቡጧን እንጂ፤ በላይዋ የተሸከመችውን አንድ ሺህ እሾዋን እንዴት ማሰብ ተሳነው?

ሁላችንም  እንደጽጌረዳ ነን፤ ከውስጣችን እራሳችንን እንደጽጌሬዳዋ ማፍካት ከቻልን ስዎች ኦሾዋችንን አይተው እንዳላዩ መሆን ይችላሉ። ከነ እሾዋችን ውበታችንን እና ማንነታችንን መቀበል ግድ ያላቸዋል። አብዛኛዎቻችን ግን፤ ሰዎች መልካሙን ገጽታችንን እንዲያዩልን ስንል፤ በላያችን ያለውን እሾህ አንድ በአንድ ለመንቀል እንሞክራል። ያ ጊዜ የሚፈጅ መፍትሄ ብቻም ሳይሆን የማይቻልም ነው፤ በዛ ላይ እኛነታችንን የሚያሳጣን ነው። ቀላሉ መፍትሄ እራሳችንን መሆን እና፤ መክሊታችንን መኖር ነው። ያኔ ማንነታችን ልክ እንደጽጌሬዳዋ መፍካት ይጀምራል። ሰዎችም የፈካውን ግሩም ማንነታችንን አልፈው እንከናችንን መመልከት ይከብዳቸዋል። ልክ ጽጌሬዳን ሲያስቡ እሾህን ማሰብ እንደሚከብድ ሁላ። እራሱን ያልሆነ እና ደስታ የራቀው ሰው ግን፤ እንቡጥ የሌለው በሾህ የተሞላ የጽንጌሬዳ ግንድ ማለት ነው። ሰዎች ውበቱን በፍጹም ማየት አይቻላቸውም።

መፍካት ስንል ምንድን ነው? መፍካት ማለት እራስን በመሆን መኖር መቻል ነው ብዬ አስባለው። እራሳችንን ስንሆን፤ ለኛ ብቻ የተሰጠንን መክሊት አውጥተን ልክ እንደ ጽጌሬዳዋ ሌላው እንዲያየው ማድረግ ይቻለናል። ፈጽሞ ሌሎች እንዲቀበሉን ስንል እራሳችንን መሞረድ እና ማስተካከል የለብንም። ሰዎች እኛነታችንን መቀበል ከቻሉ እሰየው፤ ካልቻሉ ግን የኛ ጥፋት አይደለም። በርግጠኝነት ለሰው ብለን የምንይዘው ማንነት፤ ለኛ በልክ እንዳልተሰፋ ልብስ አያምርብንም፤ ያ ደግሞ ለሌሎችም ሰዎች በግልጽ የሚታይ ነው። እናም የዛሬው መልዕክቴ እራስህን በመሆን በደስታ ፍካ…..ሰዎች ሳይወዱ በግዳቸው ደካማውን ጎን ቸል ማለታቸው አይቀርም የሚል ነው። በሁላችንም ውስጥ ለመፍካት የሚችል ማንነት አለ….ያንን ማውጣት ካልቻልን ግን የሾህ ግንድ መሆናችን ነው፤ ቀልብን የማይስብ ማንነት!!!

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *