“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መነቃቂያ

"If you feed your mind as often as you feed your stomach, then you'll never have to worry about feeding your stomach or a roof over your head or clothes on your back"-Albert Einstein

አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

(በሚስጥረ አደራው) “ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ለፈጣሪ ባለን የምስጋና መጠን ይወሰናል። ህይወታችንን እጅግ መልካም ለማድረግ አልያም እርግማን ወደሞልው የሰቀቀን ኑሮ ለመለወጥ የሚያስችለን የገዛ አመለካከታችን ነው። አንዳንዶቻችን በቤታችን ጓሮ የተተከለውን ጽጌሬዳ ስንመለከት ጽጌሬዳው በእሾህ መወረሱ ያበሳጨናል፤አንዳንዶች ደግሞ እሾሁ ጽጌሬዳ ማብቀሉ ይገርማቸዋል። ሁሉ ነገር እኛ በሚኖረን የህይወት መነጽር ይወሰናል።...

ሀሙስ ከደረስን እሁድ ብዙ አይርቅም!

(በሚስጥረ አደራው) ህይወት ከሰባት ቀናቶች የበለጠ እድሜ የላትም፤ የትኛው ቀን ላይ ነን? ይህንን ያለው ታዋቂው ገጣሚ ሮበት ብላይ ነው።  ገጣሚው ይህንን የተናገረው አሜሪካ በወቅቱ የነበረችበትን ጦርነቶች አስመልክቶ ተቃውሞውን በገለጸበት ግጥሙ ውስጥ ነበር። ይህ ሰው ስነጥብበን ለሰላም ለማዋል ብዙ ተግቷል፤ እንደውም “American Writers Against the Vietnam War” የሚል ማህበርም መስርቶ ነበር፤ ይህ...

Zahir ;The rout to holiness or madness-ክፍል አንድ

Zahir ;The rout to holiness or madness-ክፍል አንድ

(በሚስጥረ አደራው) ለዛሬ እንደመወያያም አልያም እንደ ሃሳብ ላነሰው የወደድኩት የፓውሎ ኮዌሎ ድርሰት ከሆነውና “ዛሂር” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከወደድኳቸው አባባሎች ውስጥ አንደኛውን ነው። ዛሂር ማለት ይላል የመጽሐፉ ደራሲ፦ In Arabic, Zahir is a visible presence incapable of going unnoticed. It is someone or something that once it comes to our...

መቆረጥ ያለበት ተስፋ

(በሚስጥረ አደራው)  የጥበቃ ልኩ ምን ያህል ነው? በተስፋና በከንቱ ጥበቃ መካከል ያለው መስመር ምን ያህል ቀጭን ነው? በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ ቢኖርስ? አንዳንድ ነገሮች ላይመጡ ያስጠብቁናል፤ ተስፋ መቁረጥ አልያም መተው፤ ከተስፋ መቁረጥ በተለየ አወንታዊ የሚሆንበት አጋጣሚ የለም? ጎረቤቴ ነው፤ ይህ ሰዓሊ። ሰዓሊ ያልኩት አዘውትሮ ቀለምና ብሩሹን ይዞ ገርበብ ካለው በራፉ ላይ ስለሚቀመጥ ነው። ተመሳሳይ የስዕል ሸራ...

እኔን? በእንግሊዘኛ ምንድን ነው?

(በሚስጥረ አደራው)  ሰው ሲያደናቅፈው፤ ወይም የሆነ አደጋ ሲደርስበት "እኔን" ማለት በእኛ ማህበረሰብ የተለመደ ነው። ያንን ሰው  አወቅነውም አላወቅነውም፤ ለቤተሰባችንም ሆነ ለመንገደኛ "እኔን" ስንል አይምሮዋችን ሁለቴ አስቦ አይደለም። "እኔን" ማለት የለመደብኝ ከእናቴ ነው፤ ሳላውቀው ውስጤ ተዋህዷል መሰለኝ እኔም ሰው ደንቀፍ ሲያደርገው፤ ወይም ሲጋጭ ብቻ የሆነ አስደንጋጭ ነገር ሲከሰት "እኔን" እላለው። ታዲያ...

ቁልፉ ማን ዘንድ ነው?

(በሚስጥረ አደራው) የተዘጋ በር የብዙ ነገሮች ምሳሌ ነው። ምኞቶቻችን፤ ፍላጎቶቻችን እንዲሁም ህልሞቻችን በተቆለፈ በር ይመሰላሉ። መጠየቃችን፤ መፈለጋችንና ልፋታችን ደግሞ በሩን እንደማንኳኳት ይቆጥራል። "አኳኩ ይከፈትላችኋል" የሚለው ቃል በብዙዎቻችን ህሊና ውስጥ የተቀረጸ ቅዱስ ቃል የሆነውም የእድሜ ጀንበር ግዜዋ ደርሶ እስክትጠልቅ ድረስ በሮች መዘጋታቸው እኛም ማንኳኳታችን ስለማይቀር ነው። ስለ በርና ማንኳኳት መጻፍ...

ህልምህን እየገደልከው ነው? Are You killing your Dreams?

(በሚስጥረ አደራው) ህልም እስከወዲያኛው ይሞታል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይቀበራል። ሳይሞት የሚቀበር ነገር ህልም ነው። የሰው ልጅ ያለ ህልም አይኖርም፤ አዲስ ጫማ ከመግዛት አንስቶ ሌላ ሰው እስከመሆን ድረስ ያልማል። አንዳንዴ ህልሙ እውን ሆኖለት የፈለገውን ሲያገኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ህልሙን በምክንያት ቀብሮ የኑሮ ጉዞውን ይቀጥላል። ህልም ሳይሞት ይቀበራል ያልኩት፤ ሰው በውስጡ "እንዲህ ማድረግ እኮ እፈልግ ነበር"...

“ሰጠኝ” እና “አገኘሁ”

(በሚስጥረ አደራው) የድሮ የኢኮኖሚክስ አስተማሪዬ ነበሩ። ስማቸው ለጊዜው ተዘነጋኝ። ነገር ግን ከአመታት በፊት የተናገሩት ነገር ዛሬም ድረስ አይምሮዬ ውስጥ አለ። አንድ  ቀን የመጨረሻውን የሴሚስተሩን ፈተና ከተፈተንን በኋላ ስለ ውጤት ሲመክሩን እንዲህ ነበር ያሉት። “ከተማሪዎች ባህሪ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር፤ ውጤታቸው ጥሩ ሲሆን ማለትም ኤ ሲሆን “ኤ አገኘሁኝ” ይላሉ። በአንጻሩ ውጤታቸው መጥፎ ሲሆን ደግሞ ለምሳሌ ሲ...

በአንገታችን ላይ ያለውን ሀብል ፍለጋ……

(በሚስጥረ አደራው) ሳምንቱን ሙሉ የስልኬን ቻርጀር ፈልጌ አጥቼው ጠፋ ብዬ ተስፋ ቆረጬ ነበር። አዲስ ቻርጀር ለመግዛት በማሰብ ላይ ሳለው፤ ዛሬ ጠዋት ድንገት አገኘሁት። ያገኘሁት ደግሞ አስር ጊዜ ፈልጌ ካጣሁበት ከቦርሳዬ ውስጥ ነበር። በራሴ ሳቅኩኝ……እንኳንም ሌላ ከመግዛቴ በፊት አገኘሁት ብዬ ደስ አለኝ። ግራ የገባኝ ግን፤ ያለማጋነን ይህንን ቦርሳ ደግሜ ደጋግሜ ፈትሼዋለው፤ እንዴት አላየሁትም? የሚለው ነው። ነገሩ...

ጸንተህ ለመቆም ከፍርሃትህ የሚበልጥ ነገር ፈልግ!

ፍርሃት በሁለት መንገድ የሚከፈል ይመስለኛል። አንደኛ እራሳችን የምንፈጥረው ፍርሃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሌሎች በውስጣችን የሚጭሩት ፍርሃት ነው። ሁለቱም ሀይለኛ ስሜቶች ናቸው። ሁለቱም ጉልበትን የማሸብረክ፤ ውሳኔን የማስቀየር፤ አላማን የማሳት፤ አሸማቆ ወደ ብቸኝነት ጉድጓድ የማስገባት ጉልበት አላቸው። እራሳችን በራሳችን የምንፈጥረውና ሌሎች በኛ ሊጭሩት የሚሞክሩት ፍርሃት የየራሳቸው ባህሪ አላቸው። እንደሚከተለው...

© 2023 Asharaye.net. All rights reserved.