“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ህልምህን እየገደልከው ነው? Are You killing your Dreams?

by | May 8, 2017 | መነቃቂያ inspiring stories | 3 comments

(በሚስጥረ አደራው)

ህልም እስከወዲያኛው ይሞታል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይቀበራል። ሳይሞት የሚቀበር ነገር ህልም ነው። የሰው ልጅ ያለ ህልም አይኖርም፤ አዲስ ጫማ ከመግዛት አንስቶ ሌላ ሰው እስከመሆን ድረስ ያልማል። አንዳንዴ ህልሙ እውን ሆኖለት የፈለገውን ሲያገኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ህልሙን በምክንያት ቀብሮ የኑሮ ጉዞውን ይቀጥላል።
ህልም ሳይሞት ይቀበራል ያልኩት፤ ሰው በውስጡ “እንዲህ ማድረግ እኮ እፈልግ ነበር” እስካለ ድረስ ህልሙ እስትንፋስ አለው ብዬ ስለማምን ነው። “ቢሆን ኖሮ” የሚል ማንኛውም ሰው፤ ሳይሞት ነገር ግን ከብዙ ምክንያቶች እና አጋጣሚዎች ስር የተቀበረ ህልም አለው።
እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ማስረገጥ እፈልጋለው፤ ብዙን ጊዜ “ህልም” ስንል፤ ሌሎች የሚያጸድቁት ትልቅነትንና በአደባባይ የሚታይን ክብር አይደለም።ሁላችንም የምንጋራው ትክክለኛ ህልም ፤ ኑሮዋችንን ሀሴት በሚሰጠን መልኩ መምራትና ከኑሮ ውስጥ ማትረፍ የምንችልውን ሁሉ ማትረፍን ነው። ያ ደግሞ ለሁላችንም የተለያየ ነው……
ሆኖም ግን ነገሮች ከአሰብናቸው በላይ ሲከብዱ፤ አስቀድመን ያላሰብንቸው ነገሮች ሲከሰቱ፤ ህልማችን ቅዠት ይመስለናል፤ ደስታ ይሰጠናል ብለን ያሰብነውን የህልም ኑሮ ወደታች ቀብረን፤ አጋጣሚ በሚቀድልን ቦይ መፍሰስ እንጀምራለን። ምንም እንኳን ከህልማችን እርቀን ብንጓዝም ፤ ሁሌም በውስጣችን “እንዲህ አስብ ነበር እኮ” ማለታችን ግን አይቀርም።
ዘ ፒልግሪሜጅ የተሰኘው የፓውሎ ኮዌሎ መጽሀፍ ላይ፤ ሰው ህልሙን መግደል ሲጀምር፤ የሚከተሉትን ሶስት ምልክቶች ያሳላይል ይላል።

1- የመጀመሪያ ምልክት “ጊዜ የለኝም” ማለት ማብዛት ነው- ጸሀፊው “እጅግ ጊዜ የጠበባቸው ሰዎች ለሚፈልጉት ነገር ሁሌም ጊዜ ይኖራቸዋል፤ በአንጻሩ በጊዜያቸው ምንም የማይሰሩ ሰዎች ናቸው የቀኑን ማጠር የሚያማርሩት” ይላል። ለነገሩ ማን ነው በዚህ ምድር ላይ ከ 24 ሰዓታት በላይ የተሰጠው? ህልም ካለን ወይም ማድረግ የሚያስደስተን ነገር ካለ፤ ግዜ ፈጽሞ ችግር ሊሆን አይችልም። ጊዜ አጥቼ ነው ማለት ስንጀምር በእርግጥም ህልማችን ላይ ግድያ እየፈጸምን ነው። ቅድሚያ የምሰጠውን ነገር ማስተዋል ሲቻለን፤ እውነትም 24 ሰዓታት ለምንፈልገው ነገር በቂ መሆኑ ይገለጽልናል።

2- ሁለተኛ ምልክት “እርግጠኝነታችን” ማብዛት ነው።- ይህ ማለት ከውጊያው በፊት ቀድመን ስንሸነፍ ነው። ሁሉን ነገር ተንብየን፤ የነገሩን ከንቱነት ለራሳችን ሰብከን፤ ከህይወት የሚገባንን ሳይሆን ጥቂቱን ብቻ መጠየቅ እንጀምራለን። ከጸሀፊው አንደበት የሚከተለውን ልጠቅስ ወደድኩኝ
“we never see the delight, the immense delight in the hearts of those who are engaged in the battle. For them, neither victory nor defeat is important; what’s important is only that they are fighting the Good Fight.”
“The good Fight” የሚለው ጸሀፊው፤ ልባችን የሚጠይቀንን ጥልቅ መሻት ሁሉ ነው።
ለሚፈልጉት ነገር የሚዋጉ ሰዎች ፤ ድልና ሽንፈቱ አይደለም የሚያበረታቸው። የሚያበረታቸው ለሚፈልጉት ነገር መታገላቸው ብቻ ነው፤ እምነት እና ህልማቸውን ነው ጽናታቸው። የብዙዎቻችን ችግር ግን ድልና ሽንፈትን፤ እውቅናና መዘንጋትን መሰረት ማድረጋችን ነው። ከመንገዱ ጋር እንጂ ከመደረሻው ጋር ፍቅር ሊይዘን አይገባም። መንገዱን ስንወደው ነው መሄድ የማናቋርጠው።

3- የመጨረሻው ምልክት – “ህይወት እንደ እሁድ ከሰዓት” መሆን ስትጀምር ነው- ይህ ማለት ሁሉን በጸጋ ተቀብለን ስንኖር፤ ከኑሮ የምንፈልገውን መጠየቅ ስናቆም፤ ህልማችን እየሞተ ነው ማለት ነው። እዚህ ላይ ነው ብዙዎቻችን የምሸወደው፤ እራሳችንን እንደበሳል ቆጥረን፤ የምናስበው ሁሉ የልጅነት ቅዠት ነው ብለን እናምናለን። ከውስጥ ግን ሁሌም በትንሹ የሚጮህ ድምጽ አለ “ቢሆን ኖሮ” የሚል – ይህ ድምጽ የህልማችን ጣር ነው።
“We become our own worst enemy. We say that our dreams were childish, or too difficult to realize, or the result or our not having known enough about life. We kill our dreams because we are afraid to Fight the Good Fight.”-Paulo Coelho
ሁሉንም እርግፍ አርጎ መተው ለግዜው ሰላም የሚሰጥ ይመስላል፤ ነገር ግን ከውስጣችን የምንፈልገው ነገር እውን እስካልሆነ ድረስ ሁሌም ሰላም መንሳቱ አይቀርም። ሳይሞት የምንቀብረው ህልማችን፤ እየፈነቀለ “ቢሆን ኖሮ” ያስብለናል። ህይወት አጭር ናት፤ የምንፈልገው እና የምናልመው ነገር ደስታን የሚሰጠን ከሆን በምክንያት አንቅብረው። ሶስቱን ምልክቶች ካየን፤ ህልማችንን ወዴት እንዳደረስነው እራሳችንን እንጠይቅ።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

3 Comments

  1. Tizita Haile

    Thank You Mister! I love your blogs and knowledgeable facts. As long as you write, I continue not only read, but grow big!

    Reply
  2. Bereket

    Thought become things ይባላል። አሁን ሚስጥሩ የገባኝ ራስ ላይ መስራት ነው። ይሄው ሁለት ወር አስቆጥሬያለው። ለውጥም አምጥቻለው ራሴ ላይ ስሰራ ስልጠናዎችን እና መፅሀፎችንም እንዲሁ የጥሞና ጊዜ እጠቀማለው ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሁነኛ ፁሁፍ እፈልግ ነበር ሆን ብዬ ማንበብ ፈልጋለው። ስለዚህ ይህንን ፔጅ አገኘው ያገኘውትም የሆነ ግሩፕ ላይ ቪድዮ ተለቆ ነው መጨረሻ ላይ ዌብሳይቱን አገኘው ይሄው እየተመገብኩ ነው። እድሜ ይስጥልኝ

    Reply
  3. Temesgen

    10Q for ur interesting and gentle idea!!!. ur work is like make restart to persons life!!!

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *