“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መቆረጥ ያለበት ተስፋ

(በሚስጥረ አደራው)  የጥበቃ ልኩ ምን ያህል ነው? በተስፋና በከንቱ ጥበቃ መካከል ያለው መስመር ምን ያህል ቀጭን ነው? በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ ቢኖርስ? አንዳንድ ነገሮች ላይመጡ ያስጠብቁናል፤ ተስፋ መቁረጥ አልያም መተው፤ ከተስፋ መቁረጥ በተለየ አወንታዊ የሚሆንበት አጋጣሚ የለም? ጎረቤቴ ነው፤ ይህ ሰዓሊ። ሰዓሊ ያልኩት አዘውትሮ ቀለምና ብሩሹን ይዞ ገርበብ ካለው በራፉ ላይ ስለሚቀመጥ ነው። ተመሳሳይ የስዕል ሸራ...

እኔን? በእንግሊዘኛ ምንድን ነው?

(በሚስጥረ አደራው)  ሰው ሲያደናቅፈው፤ ወይም የሆነ አደጋ ሲደርስበት “እኔን” ማለት በእኛ ማህበረሰብ የተለመደ ነው። ያንን ሰው  አወቅነውም አላወቅነውም፤ ለቤተሰባችንም ሆነ ለመንገደኛ “እኔን” ስንል አይምሮዋችን ሁለቴ አስቦ አይደለም። “እኔን” ማለት የለመደብኝ ከእናቴ ነው፤ ሳላውቀው ውስጤ ተዋህዷል መሰለኝ እኔም ሰው ደንቀፍ ሲያደርገው፤ ወይም ሲጋጭ ብቻ...

ቁልፉ ማን ዘንድ ነው?

(በሚስጥረ አደራው) የተዘጋ በር የብዙ ነገሮች ምሳሌ ነው። ምኞቶቻችን፤ ፍላጎቶቻችን እንዲሁም ህልሞቻችን በተቆለፈ በር ይመሰላሉ። መጠየቃችን፤ መፈለጋችንና ልፋታችን ደግሞ በሩን እንደማንኳኳት ይቆጥራል። “አኳኩ ይከፈትላችኋል” የሚለው ቃል በብዙዎቻችን ህሊና ውስጥ የተቀረጸ ቅዱስ ቃል የሆነውም የእድሜ ጀንበር ግዜዋ ደርሶ እስክትጠልቅ ድረስ በሮች መዘጋታቸው እኛም ማንኳኳታችን ስለማይቀር ነው። ስለ...

ህልምህን እየገደልከው ነው? Are You killing your Dreams?

(በሚስጥረ አደራው) ህልም እስከወዲያኛው ይሞታል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይቀበራል። ሳይሞት የሚቀበር ነገር ህልም ነው። የሰው ልጅ ያለ ህልም አይኖርም፤ አዲስ ጫማ ከመግዛት አንስቶ ሌላ ሰው እስከመሆን ድረስ ያልማል። አንዳንዴ ህልሙ እውን ሆኖለት የፈለገውን ሲያገኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ህልሙን በምክንያት ቀብሮ የኑሮ ጉዞውን ይቀጥላል። ህልም ሳይሞት ይቀበራል ያልኩት፤ ሰው በውስጡ “እንዲህ ማድረግ እኮ እፈልግ...

“ሰጠኝ” እና “አገኘሁ”

(በሚስጥረ አደራው) የድሮ የኢኮኖሚክስ አስተማሪዬ ነበሩ። ስማቸው ለጊዜው ተዘነጋኝ። ነገር ግን ከአመታት በፊት የተናገሩት ነገር ዛሬም ድረስ አይምሮዬ ውስጥ አለ። አንድ  ቀን የመጨረሻውን የሴሚስተሩን ፈተና ከተፈተንን በኋላ ስለ ውጤት ሲመክሩን እንዲህ ነበር ያሉት። “ከተማሪዎች ባህሪ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር፤ ውጤታቸው ጥሩ ሲሆን ማለትም ኤ ሲሆን “ኤ አገኘሁኝ” ይላሉ። በአንጻሩ ውጤታቸው መጥፎ ሲሆን ደግሞ ለምሳሌ ሲ...

በአንገታችን ላይ ያለውን ሀብል ፍለጋ……

(በሚስጥረ አደራው) ሳምንቱን ሙሉ የስልኬን ቻርጀር ፈልጌ አጥቼው ጠፋ ብዬ ተስፋ ቆረጬ ነበር። አዲስ ቻርጀር ለመግዛት በማሰብ ላይ ሳለው፤ ዛሬ ጠዋት ድንገት አገኘሁት። ያገኘሁት ደግሞ አስር ጊዜ ፈልጌ ካጣሁበት ከቦርሳዬ ውስጥ ነበር። በራሴ ሳቅኩኝ……እንኳንም ሌላ ከመግዛቴ በፊት አገኘሁት ብዬ ደስ አለኝ። ግራ የገባኝ ግን፤ ያለማጋነን ይህንን ቦርሳ ደግሜ ደጋግሜ ፈትሼዋለው፤ እንዴት አላየሁትም? የሚለው ነው። ነገሩ...