“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ጸንተህ ለመቆም ከፍርሃትህ የሚበልጥ ነገር ፈልግ!

ፍርሃት በሁለት መንገድ የሚከፈል ይመስለኛል። አንደኛ እራሳችን የምንፈጥረው ፍርሃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሌሎች በውስጣችን የሚጭሩት ፍርሃት ነው። ሁለቱም ሀይለኛ ስሜቶች ናቸው። ሁለቱም ጉልበትን የማሸብረክ፤ ውሳኔን የማስቀየር፤ አላማን የማሳት፤ አሸማቆ ወደ ብቸኝነት ጉድጓድ የማስገባት ጉልበት አላቸው። እራሳችን በራሳችን የምንፈጥረውና ሌሎች በኛ ሊጭሩት የሚሞክሩት ፍርሃት የየራሳቸው ባህሪ አላቸው። እንደሚከተለው...

መጀመሪያ ቃል ነበረ……

“መጀመሪያ ቃል ነበረ….” ይላል ቅዱሱ መጽሃፍ። ቃል ትልቅ ሀይል እና ጉልበት ያለው ነገር መሆኑን ይህ ጥቅስ ያስረዳል። ይህ አባባል ከሀይማኖታዊ ትርጓሜው በዘለለ በእለት ተእለት ኑሮዋችንም ትልቅ ጉልበት ያለው መልዕክት ነው። በቃል መልካምም መጥፎም ነገሮች በኑሮዋችን ውስጥ ህይወት ይዘራሉ። እውን ሆነው በአይናችን የምናያቸው ነገሮች ሁሉም ሁለቴ የተፈጠሩ ናቸው። በመጀመሪያ በአይምሮዋችን...

“አይን አይኑን የሚያዩት ውሃ ቶሎ አይፈላም”

(በሚስጥረ አደራው) አለም አንድ ሆናለች በሚባልበት በዚህ ዘመን፤ ነገሮች እጅግ በፈጠኑበት በዚህ ጊዜ፤ የፈለግነውን መረጃ በቀላሉ እና በአፋጣኝ በምናገኝበት ወቅት፤ ነገሮችን በትዕግስት መጠበቁ እጅግ ከባድ ሆኖብናል። የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ በቀላሉ ማግኘት እንደምንችል የምንኖርበት ጊዜ እየሞገተን ነው ያለው። ጥረት እና ትዕግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየወረደ መጥቷል። የጊዜ ፍጥነት፤ የሁኔታዎች መመቻቸት፤...

ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል ሁለት)

(በሚስጥረ አደራው) በመጀምሪያው ክፍል (ሎጎቴራፒ ክፍል አንድ)  ስለ ሎጎ ቴራፒ በጥቂቱ ተረድተናል። ለማስታወስ ያህል ሎጎ ቴራፒ ሰዎችን ከጭንቀት ወይም ከተስፋ መቁረጥ ስሜት ለማላቀቅ ከሚረዱ የስነልቦና መንገዶች አንደኛው ነው። ሰዎች ተስፋ የሚቆርጡት አልያም ትርጉም የለሽ ኑሮ እንደሞኖሩ የሚሰማቸው የሚኖሩለት ነገር ስለሌላቸውና ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጥ ነገር ባለማግኘታቸው ነው በሚል መሰረተ ሃሳብ ላይ የተንተራሰ...

“ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ……..”

“ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ፋንድያቸው ለምን ተለያያ?” ፣ ይህ አባባል ለከብቶች መንጋ ብቻም ሳይሆን ለሰዎች መንጋም የሚሰራ መሰለኝ። አንድ አይነት ትምህርት ቤት ገብተን፤ በአንድ አይነት መምህር ተምረን፤ በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠን፤ በስተመጨረሻ አንዳችን ከፍ ብለን ስንቆም ሌሎቻችን ግን ከጀመርንበት ፈቀቅ አንልም። ይህን ጥያቄ ስንጠይቅ የሰውን ልጅ የህይወት መስመሮች ሊቀይሩ የሚችሉ...