“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል ሁለት)

by | Jul 11, 2016 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments


(በሚስጥረ አደራው)

በመጀምሪያው ክፍል (ሎጎቴራፒ ክፍል አንድ)  ስለ ሎጎ ቴራፒ በጥቂቱ ተረድተናል። ለማስታወስ ያህል ሎጎ ቴራፒ ሰዎችን ከጭንቀት ወይም ከተስፋ መቁረጥ ስሜት ለማላቀቅ ከሚረዱ የስነልቦና መንገዶች አንደኛው ነው። ሰዎች ተስፋ የሚቆርጡት አልያም ትርጉም የለሽ ኑሮ እንደሞኖሩ የሚሰማቸው የሚኖሩለት ነገር ስለሌላቸውና ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጥ ነገር ባለማግኘታቸው ነው በሚል መሰረተ ሃሳብ ላይ የተንተራሰ የስነልቦና ጥናት ነው። በሎጎ ቴራፒ አማካኘነት ሰዎች በህይወታችን ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር ሲያገኙ፤ ወይም የሚኖሩለት ነገር ሲኖራቸው ትልቅ መነቃቃትን በህይወታቸው ይፈጥርላቸዋል።

እንደ ፕ/ር ፍራንክል ጥናት በህይወታችን ትርጉም ልናገኝ  የምንችልባቸው  ሶስት መንገዶች አሉ። እነዚህ ሶስት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው

According to Frankl “we can discover this meaning in life in three different ways

1- By creating a work or doing a deed

2-By experiencing something or encountering someone

3-By the attitude we take toward unavoidable suffering

ነጣጥለን እንያቸው ካልን

1ኛ– ሰው በሚሰራው ስራ ለህይወቱ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል- እዚህ ላይ ብዙ ሰዎችን በምሳሌ መውሰድ እንችላለን፤ የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ሰዎች፤ በበጎ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፤ በጥበብ ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ ከብዙሃኑ ተነጥለው የልባቸው ጥሪ በማድመጥ የሚኖሩ ናቸው። የሚሰሩት የሚወዱትንና ትርጉም የሚሰጣቸውን ነገር ነው። እዚህ ላይ የሁላችንም ዝንባሌ እና ፍላጎት ይለያያል። ለእኛ ትርጉም የሚሰጠንና ልባችንን የሚያስደስተው ነገር ለሌላው ሰው ምንም ትርጉም ላይሰጠው ይችላል። የሚወዱትን የሚሰሩ ሰዎች ግን የሌላው ሰው ማረጋገጫ  ሳያስጨንቃቸው ለሚኖሩለት ነገር ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውንና መንፈሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። ስለዚህም እያንዳንዷ ቀን ለነሱ ትርጉም አላት፤ የጥቅም የለሽነት እና ትርጉም ማጣት አይሰማቸውም።

2ኛ– ሁለተኛው የህይወት አጋጣሚዎች ወይንም በህይወታችን የምናገኛቸው ሰዎች ለህይወት ያለንን አመለካከት ይቀይሩታል- ለምሳሌ ልጅ እና ሌሎች አብዝተን የምንወዳቸው ሰዎች የምንኖርለት ነገር እንዳለን ያሳስቡናል። ፕ/ሩ በዚህ ነጥብ ላይ እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት፤ በነዛ አስፈሪ የናዚ ኮንሰንትሬሽን ካምፖች ውስጥ ሆነው እንኳን አንዳንድ እስረኞች ልጆቻቸውን፤ ባሎቻቸውን፤ እናትና አባቶቻቸውን እያሰቡ ያንን የመከራ ህይወት በጽናት ያሳልፉት ነበር። መከራው ሲያበቃ ለመገናኘት የሚፈልጓቸው ሰዎች እንዳሉ ስለሚያስቡ ሞትን ይሸሹ ነበር። ለእነሱ ህይወት ትርጉም አላትና። ሌላው ደግሞ አንዳንድ የህይወት አጋጣሚዎች እንደ ዘበት የምንኖረውን ኑሮ እንድንቃኝና እንድንነቃ ያደርጉናል።

3ኛ-ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ ያለንን እይታ ማስተካከል-ይህ የመጨረሻው ነጥብ በህይወታችን መመሪያ ልናደርገው የሚገባን ትልቅ ነጥብ ነው። ልናስወግዳቸው የማንቻልቸውን ነገሮች እንዴት ነው መጋፈጥ የምንችለው? ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ አጋጣሚዎች የሚያሸክሙንን መከራ እንዴት ማቅለል እንችላለን? መልሱ አመለካከታችንን መቀየር የሚል ነው። ዶ/ር ኖርማን ቪንሰንት እንዲህ ሲል ተናግሯል “የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው”። ብዙዎቻችን ችግሩን እንጂ ችግሩን እንዴት እያየነው እንደሆነ ልብ አንልም። የሚያሳስበን የደረሰብን አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን አይምሮዋችን በምናልባት እየፈጠረ የሚስልልን መላምቶች ናቸው።

“A major cause of depression is self-absorption. By drawing on a person’s strengths, the tools and techniques of logotherapy help bring about a profound shift in awareness, from a ‘victim’ mentality to an optimistic attitude. Clients and students of logotherapy are in the habit of questioning themselves about what they really want and which kinds of choices will be most conducive to growth” Themeaningseeker.com

ለጭንቀት የሚዳርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ ዋናው ምክንያት ግን በነገሮች ተስፋ መቁረጥ እና ነገን አለመናፈቅ ነው። ነገን የማንናፍቀው ደግሞ የምንኖርለት ነገር ስለሌለን፤ ለህይወታችንም ትርጉም የሚሰጥ ነገር ስናጣ ነው። ከእንደዚህ አይነት ጭንቀት ለመወጣት ሎጎቴራፒ በጣም ትልቅ እገዛ ያደርግልናል። ይህንን ጥበብ በስራ ላይ ለማዋል እራሳችንን ልንጠይቀው የሚገቡን ጥያቄዎች አሉ ለምሳሌ፦ ብንሰራቸው የሚያስደስቱን ነገሮች ምንድን ናቸው? ለፍላጎታችን ቅድሚያ መስጠት ብንችል ምን ይሆናል ቅድሚያ የምንሰጠው? ህይወታችን አጭር መሆኗን ስናስብ ሳንፈጽመው ብንሞት የሚቆጨን ምንድን ነው? ለመኖር ምክንያት ይሆነናል የምንለውስ ነገር አለን? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ከቻልን ህይወታችን ተመልሶ አሰልቺና ድግግሞሽ አይሆንብንም። ይህ የሎጎቴራፒ ሃሳብ ሁላችንንም በተለያየ መጠን የሚረዳን ይመስለኛል፤ ከዚህ በተጨማሪ የራሳችን ምርምር በማድረግ ይህንን ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በማድረግ ህይወታችንን መለወጥ እንችላለን።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *