“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ዝምታ መልስ ይሆናል?

“ለዋልኩት ውለታ ይሄነው ወይ ውርሴ? ልፋቴ ድካሜ ይሄ ነው ወይ ውርሴ? እንግዲህ ምን ልበል ይህ ከሆነ ቅርሴ አሃ….ዝምታ ነው መልሴ ክፉ ደግ አትበል አታውጋ ምላሴ አሃ ዝምታ ነው መልሴ…….” ማዳመጫዬን ሰክቼ የማዳምጠው ይህንን ውብ የመሐሙድን የሀዘን ድባብ የተላበሰ ዘፈን ነበር። እውነት ግን ዝምታ ትክክለኛ መልስ ይሆናል? ሰው መልካም ስራ ሰርቶ የማይገባውን ክፍያ...

መጀመሪያ ቃል ነበረ……

“መጀመሪያ ቃል ነበረ….” ይላል ቅዱሱ መጽሃፍ። ቃል ትልቅ ሀይል እና ጉልበት ያለው ነገር መሆኑን ይህ ጥቅስ ያስረዳል። ይህ አባባል ከሀይማኖታዊ ትርጓሜው በዘለለ በእለት ተእለት ኑሮዋችንም ትልቅ ጉልበት ያለው መልዕክት ነው። በቃል መልካምም መጥፎም ነገሮች በኑሮዋችን ውስጥ ህይወት ይዘራሉ። እውን ሆነው በአይናችን የምናያቸው ነገሮች ሁሉም ሁለቴ የተፈጠሩ ናቸው። በመጀመሪያ በአይምሮዋችን...

ለበጎ ወይስ ለመጥፎ?- ጊዜ ቢፈታውስ?

(በሚስጥረ አደራው) “There is nothing either good or bad, but thinking makes it so.”– William Shakespeare በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል። እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል...

“አይን አይኑን የሚያዩት ውሃ ቶሎ አይፈላም”

(በሚስጥረ አደራው) አለም አንድ ሆናለች በሚባልበት በዚህ ዘመን፤ ነገሮች እጅግ በፈጠኑበት በዚህ ጊዜ፤ የፈለግነውን መረጃ በቀላሉ እና በአፋጣኝ በምናገኝበት ወቅት፤ ነገሮችን በትዕግስት መጠበቁ እጅግ ከባድ ሆኖብናል። የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ በቀላሉ ማግኘት እንደምንችል የምንኖርበት ጊዜ እየሞገተን ነው ያለው። ጥረት እና ትዕግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየወረደ መጥቷል። የጊዜ ፍጥነት፤ የሁኔታዎች መመቻቸት፤...