“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ለበጎ ወይስ ለመጥፎ?- ጊዜ ቢፈታውስ?

by | Aug 15, 2016 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 1 comment

(በሚስጥረ አደራው)

“There is nothing either good or bad, but thinking makes it so.”– William Shakespeare

በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል። እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” ሲሉት። ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው።

በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ። ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው።

ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል። ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት። ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው።

በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስላልተሰብረ ሳይወስዱት ቀሩ። ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል”

ይህ ታሪክ ዝነኛው የመንፈሳዊ መምህር አለን ዋትስ በአንድ ወቅት ያስተማረው ታሪክ ነው። ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን። ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን።

የገበሬው አመለካከት እጅግ የሚደንቅ ነው። የሚገጥሙት ነገሮች ምን ይዘው እንደሚመጡ ስልማያውቅ “መልካም” እና “መጥፎ” እድል እያለ እራሱን ላልተጠበቀ ሃዘን አያዘጋጅም። የፈረሱ መጥፋት መጥፎ እድል ነው ብሎ ለማለት አልደፈረም። ምክንያቱም የሆነው ነገር ምን ይዞ እንደሚመጣ ስላላወቀ። ፈረሱ ሌሎች ፈረሶችን ይዞ ሲመጣም “መልካም እድል” ብሎ ሊደመድም አልወደደም፤ እንደሰወኛ ብናስብ እንዛ ፈረሶች ባይኖሩ ልጁ አይሰበርም ነበር። የልጁን መሰበርም እንደ መጥፎ እድል ሊወስደው አልፈለገም፤ እንደሰወኛ ግን ልጁ እግሩ ባይሰበር ኖሮ፤ እንደሌሎቹ የሰፈር ወጣቶች ከአባቱ ተነጥሎ ወደ ጦር ሜዳ በተወሰደ ነበር።

እንዲህ አይነት አመለካከት ከአልታሰበ የስሜት መናወጥ ያድናል፤ እርግጥ ነው ቀላል አይደለም። ነገር ግን በህይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ የሚገጥሙን ሁኔታዎች ጊዜ ብቻ የሚፈታው ሚስጥር በውስጣቸው አለ። እግዜርን ባማረርንበት አፋችን እንድናመሰግነው ያደረገን አጋጣሚ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለ። በአንጻሩ በስንት ልመና ያገኘነውን ነገር ምነው ባትሰጠኝ ኖሮ ብለን ያማረርንበትም ጊዜ ይኖራል። በዚህ አለም ላይ ያለምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። “ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” የሚባለው አባባል እውነትነት አለው፤ ለነገሩ እንዴት የለውም? ተራ ሰው ሳይሆን ጠቢቡ ሰለሞን የተናገረው አባባል አይደለል?

ምናልባት አሁን እያለፍነበት ያለው ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድላችንንን እንድንማረር እያረገን ይሆናል፤ ነገ የሚመጣውን ግን አናውቅም። ወይም ደግሞ አሁን ጮቤ እየረገጥንበት ነገር ነገም ጮቤ ሊያስረግጠን እንደሚችል አናውቅም። ሁለቱም ጊዜ ብቻ የሚፈታቸው እውነታዎች ናቸው። የእኛ ችሎታና ጥበብ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበል እና ነገን ለነገ መተዉ ነው። “መጥፎ” እና “ጥሩ” እድል እያልን ነገሮችን ስንከፋፍል፤ አይምሮዋችን አስቀድሞ ነገሮችን ስለሚዳኝ ጭንቀት በጊዜው ከሚሆነው ነገር ጋር እንዳንስማማ ያደርገናል። ሁሉን እንዳመጣጡ የመቀበልን ጥበብ ያድለን!!!

(በግል የፌስ ቡክ ገጼ Mistre Aderaw ወይም በዌብሳይቴ ገጽ አሻራዬMyfootprint  ይከተሉኝ)

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. Tizita Haile

    You are absolutely amazing. Your ideas carry reality inside so they have helped me to shape new me! Thank you so very much!

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *