“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“የሴት ልጅ”

(በሚስጥረ አደራው)  አገር ሰላም ብዬ ወደ ስራዬ ለመሄድ በጠዋቱ ጉዜዬን ጀምሬያለው። ከሰሞኑን አንድ ወዳጄ የሰጠኝን ብዙ ዘፈን ያለበት ማጫወቻ እያጫወትኩኝ ነበር። ድንገት ከዚህ ቀደም ልብ ብዬ አድምጬው የማላውቀው የተወዳጁ ዘፋኝ የአለማየው እሸቴ ዘፈን መስረቅረቅ ጀመረ። የመጀመሪያውን የዘፈኑን ስንኝ ስሰማ ግን የሆነ ስሜት ጭንቅላቴን መታኝ፤ ስንኙ እንዲህ ይላል “ሴት ያሳደገው ልጅ ከመባል ዘወትር ለማኝ ሆኖ...

ቁልፉ ማን ዘንድ ነው?

(በሚስጥረ አደራው) የተዘጋ በር የብዙ ነገሮች ምሳሌ ነው። ምኞቶቻችን፤ ፍላጎቶቻችን እንዲሁም ህልሞቻችን በተቆለፈ በር ይመሰላሉ። መጠየቃችን፤ መፈለጋችንና ልፋታችን ደግሞ በሩን እንደማንኳኳት ይቆጥራል። “አኳኩ ይከፈትላችኋል” የሚለው ቃል በብዙዎቻችን ህሊና ውስጥ የተቀረጸ ቅዱስ ቃል የሆነውም የእድሜ ጀንበር ግዜዋ ደርሶ እስክትጠልቅ ድረስ በሮች መዘጋታቸው እኛም ማንኳኳታችን ስለማይቀር ነው። ስለ...

ሶስት አለሞች አንዲት ነፍስ 

(በሚስጥረ አደራው) እንደዛሬ ያለው ቀን ሲገጥመኝ ይህን አስባለው። ሰው በሶስት አለሞች ውስጥ ገባ ወጣ እያለ እድሜውን የሚፈጅ ፍጡር ይመስለኛል። በእያንዳንዱ አለም የምንሰነብትባቸው የግዜ እርዝማኔዎች ቢለያዩም። ከአንዱ አለም ወደ ሌላው እየተዘዋወርን ይህንን እረጅም የህይወት ጉዞ እንለዋለን…. “ይህች አንዲቷ ነፍስ ሶስት አለሞች ለምዳ እፎይ ብላ አትኖርም አዬ የሰው እዳ” የመጀመሪያው...

ህልምህን እየገደልከው ነው? Are You killing your Dreams?

(በሚስጥረ አደራው) ህልም እስከወዲያኛው ይሞታል ብዬ አላምንም። ነገር ግን ይቀበራል። ሳይሞት የሚቀበር ነገር ህልም ነው። የሰው ልጅ ያለ ህልም አይኖርም፤ አዲስ ጫማ ከመግዛት አንስቶ ሌላ ሰው እስከመሆን ድረስ ያልማል። አንዳንዴ ህልሙ እውን ሆኖለት የፈለገውን ሲያገኝ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ህልሙን በምክንያት ቀብሮ የኑሮ ጉዞውን ይቀጥላል። ህልም ሳይሞት ይቀበራል ያልኩት፤ ሰው በውስጡ “እንዲህ ማድረግ እኮ እፈልግ...

ሰኞ ለት ተያየን በድንገት…..እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ

(በሚስጥረ አደራው) “ሰኞ ለት ተያየን በድንገት ማክሰኞ በህልሜ መጣ ሞኞ እሮብን ለፍቅር ተሳሰብን ሀሙስ ልቤን አለው ደስ ደስ አርብ ላይ ብንውል ሳንተያይ ቅዳሜ ተኛሁኝ ታምሜ እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ” ሰኞ ተጠንስሶ እሁድ ከፍጻሜ የደረሰ ፍቅር አጋጣሟችሁ ያውቃል? ፍቅር እንዲህ መንገዱ አልጋ በአልጋ ቢሆን ማን ይጠላ ነበር። ሰኞ ያገኙትን ሰው እሮብ ለፍቅር ማሰብ፤ ሀሙስ በደስታ መጥለቅለቅ፤ አርብ...