“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የፐርሽያው አለቃ ገብርሃና

(በሚስጥረ አደራው) በፐርሽያ (አሁኗ ቱርክ) ጥንታዊ ጽሁፎች ውስጥ ናስረዲን በጣም ታዋቂ ገጸባህሪ ነው። እንደሚባለው ይህ የሱፊ ፈላስፋ ናስረዲን በ13ኛው ክፍለዘመን የነበረ ብልህ መምህር ነበር። በእሱ ስም የሚተረኩ በጣም ብዙ ታሪኮች፤ ቀልዶችና፤ ትምህርት አዘል መልዕክቶች፤ ዛሬም ድረስ ይነገራሉ። ምናልባት ሳስበው ልክ እንደኛ አገር አለቃ ገብርሃና ይመስለኛል። በእኛ ሃገር ብዙ ቀልዶች አለቃ ገብረሃና እንደተናገሯቸው...

እኔን? በእንግሊዘኛ ምንድን ነው?

(በሚስጥረ አደራው)  ሰው ሲያደናቅፈው፤ ወይም የሆነ አደጋ ሲደርስበት “እኔን” ማለት በእኛ ማህበረሰብ የተለመደ ነው። ያንን ሰው  አወቅነውም አላወቅነውም፤ ለቤተሰባችንም ሆነ ለመንገደኛ “እኔን” ስንል አይምሮዋችን ሁለቴ አስቦ አይደለም። “እኔን” ማለት የለመደብኝ ከእናቴ ነው፤ ሳላውቀው ውስጤ ተዋህዷል መሰለኝ እኔም ሰው ደንቀፍ ሲያደርገው፤ ወይም ሲጋጭ ብቻ...

ሰኞ ለት ተያየን በድንገት…..እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ

(በሚስጥረ አደራው) “ሰኞ ለት ተያየን በድንገት ማክሰኞ በህልሜ መጣ ሞኞ እሮብን ለፍቅር ተሳሰብን ሀሙስ ልቤን አለው ደስ ደስ አርብ ላይ ብንውል ሳንተያይ ቅዳሜ ተኛሁኝ ታምሜ እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ” ሰኞ ተጠንስሶ እሁድ ከፍጻሜ የደረሰ ፍቅር አጋጣሟችሁ ያውቃል? ፍቅር እንዲህ መንገዱ አልጋ በአልጋ ቢሆን ማን ይጠላ ነበር። ሰኞ ያገኙትን ሰው እሮብ ለፍቅር ማሰብ፤ ሀሙስ በደስታ መጥለቅለቅ፤ አርብ...

ዝምታ መልስ ይሆናል?

“ለዋልኩት ውለታ ይሄነው ወይ ውርሴ? ልፋቴ ድካሜ ይሄ ነው ወይ ውርሴ? እንግዲህ ምን ልበል ይህ ከሆነ ቅርሴ አሃ….ዝምታ ነው መልሴ ክፉ ደግ አትበል አታውጋ ምላሴ አሃ ዝምታ ነው መልሴ…….” ማዳመጫዬን ሰክቼ የማዳምጠው ይህንን ውብ የመሐሙድን የሀዘን ድባብ የተላበሰ ዘፈን ነበር። እውነት ግን ዝምታ ትክክለኛ መልስ ይሆናል? ሰው መልካም ስራ ሰርቶ የማይገባውን ክፍያ...

መጀመሪያ ቃል ነበረ……

“መጀመሪያ ቃል ነበረ….” ይላል ቅዱሱ መጽሃፍ። ቃል ትልቅ ሀይል እና ጉልበት ያለው ነገር መሆኑን ይህ ጥቅስ ያስረዳል። ይህ አባባል ከሀይማኖታዊ ትርጓሜው በዘለለ በእለት ተእለት ኑሮዋችንም ትልቅ ጉልበት ያለው መልዕክት ነው። በቃል መልካምም መጥፎም ነገሮች በኑሮዋችን ውስጥ ህይወት ይዘራሉ። እውን ሆነው በአይናችን የምናያቸው ነገሮች ሁሉም ሁለቴ የተፈጠሩ ናቸው። በመጀመሪያ በአይምሮዋችን...