“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የፐርሽያው አለቃ ገብርሃና

by | Jul 14, 2017 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 1 comment

(በሚስጥረ አደራው)

በፐርሽያ (አሁኗ ቱርክ) ጥንታዊ ጽሁፎች ውስጥ ናስረዲን በጣም ታዋቂ ገጸባህሪ ነው። እንደሚባለው ይህ የሱፊ ፈላስፋ ናስረዲን በ13ኛው ክፍለዘመን የነበረ ብልህ መምህር ነበር። በእሱ ስም የሚተረኩ በጣም ብዙ ታሪኮች፤ ቀልዶችና፤ ትምህርት አዘል መልዕክቶች፤ ዛሬም ድረስ ይነገራሉ። ምናልባት ሳስበው ልክ እንደኛ አገር አለቃ ገብርሃና ይመስለኛል። በእኛ ሃገር ብዙ ቀልዶች አለቃ ገብረሃና እንደተናገሯቸው በማለት፤ በእሳቸው ስም ዘመናትን ይሻገራሉ። የፐርሺያው ሙላህ ናስረዲንም በስሙ የሚተረኩ እጅግ ብዙ አስደናቂ ትሪኮች አሉት፤ አባዛኛዎቹ ሳቅ የሚጭሩና፤ እንዲህም ይታሰባል እንዴ? የሚያሰኙ ናቸው፤ እስቲ ለዛሬ ሶስቱን ልጋብዛችሁ

ይዘንባል ብዬ አላሰብኩም ነበር
አንድ ቀን ናስረዲን ከአንድ ሌላ ወዳጁ ጋር በመንገድ ይጓዛሉ። ናስረዲን በጀርባው ዣንጥላ ይዞ ነበር። ጥቂት ከተጓዙ በኋላ ሃይለኛ ዝናብ ዘነበ። ከናስረዲን ጋር ይጓዝ የነበረው ሰው “ዣንጥላውን ለምን አትዘረጋውም?” ሲል ጠየቀው። ይሄኔ ናስረዲን “ዣንጥላዬ ሰባራ ነው፤ ብዘረጋው ምንም ጥቅም የለውም” አለው። ግራ የተጋባው ሰውም “ታዲያ ለምን ይዘኸው መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ናስረዲንም “ይዘንባል ብዬ ስላሰብኩኝ” አለው ይባላል።

እናውቃለን ያላችሁት አናውቅም ላሉት ንገሯቸው

በሌላ ጊዜ ደግሞ ናስረዲን በመንደሩ ለተሰበሰቡ ሰዎች ንግግር እንዲያደርግ ተጋበዘ። በዕለቱ ወደተሰበሰቡት ሰዎች ቀርቦም “ዛሬ ስለምን እንደማወራ ታውቃላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። የተሰበሰቡት ሰዎችም “አናውቅም” ሲሉ በህብረት መለሱ። ናስረዲም “ምን እንደምናገር እንኳን ለማያቁ ሰዎች ምንም የመናገር ፍላጎት የለኝም” ብሎ ንግግር ሳያደርግ ጥሏቸው ሄደ።

የተሰበሰቡት ሰዎችም በሐፍረት ተውጠው እንደገና ለሁለትኛ ጊዜ ጋበዙት። በዚህ ቀንም ናስረዲን ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቀ ” ስለምን እንደማውራ ታውቃላችሁ?” አላቸው። የተስበሰቡት ሰዎች ያለፈውን ስህተት ላለመድገም “አዎ እናውቃለን” ሲሉ መለሱለት። ይሄኔ እሱም ” የምታውቁ ከሆነ ለምን ደግሜ እነግራችኋለው? ነገር በመደጋጋም ጊዜዬን አላጠፋም” በማለት ለሁለተኛ ጊዜ እንደታሰበው ንግግር ሳያደርግ ጥሏቸው ሄደ።

ተሰብስበው የነበሩት ሰዎችም ከቅድሞ በበለጠ ደንገጡና፤ ለመጨረሻና ለሦስተኛ ግዜ ናስረዲን ንግግር እንዲያደርግ አግባብተው ጋበዙት። ናስረዲን እንደመጀመሪያና እና ሁለተኛው ግዜ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃቸው “ስለምን እንደማወራ ታውቃላችሁ?” አለ። የተበሰበሰቡት ሰዎችም ከመጀመሪያውና ከሁለተኛው ቀን በመማር የተቀላቀለ መስል ሰጡት ። ከፊሉ “እናውቃለን” ሲል ከፊሉ “አናውቅም” ሲሉ መለሱ። ናስረዲንም “እናውቃለን ያላችሁት አናውቅም ላሉት ንግሯቸው” ብሎ ለሶስተኛ ጊዜ ንግግር ሳያድረግ አመለጣቸው።

ከእኔ በላይ የአህያዬን ቃል አመንክ

አንድ ግዜ ደግሞ የናስረዲን ጎረቤት የናስረዲንን አህያ ለመዋስ ወደቤቱ መጣ። “ናስረዲን ወዳጄ እባክህ አህያህን ለአንድ ቀን ልዋሰው?” ሲል ጠየቀው። ናስረዲንም መልሶ “አይይ አህያዬን ለሌላ ሰው አውሼዋለው” አለ። ይህንን ባለበት ቅጽበት የአህያው ድምጽ ተሰማ። ጎረቤቱም በመደናገር “ይኽው የአህያህን ድምጽ እየሰማው አይደለም እንዴ? ምናለ ብታውሰኝ?”ብሎ ሞገተው። ናስረዲንም “የአህያዬን ቃል ከእኔ ቃል አብልጦ ለሚያምን ወዳጅ ምንም ነገር ላውሰው አይገባውም” ሲል አሰናበተው።

እንግዲህ የናስረዲን ታሪኮች በብዛት ለዛ ያላቸውና ፈገግ የሚያስብሉ ናቸው፤ በውስጣቸው ግን…….እንዲህም ይታሰባል ያስብላሉ። እኔ የፐርሽያው አለቃ ገብረሃና ያልኩት ለማወዳደር ሳይሆን፤ ሁለቱም በቀልድ እየተወራረሱ የሚቀርቡ ብዙ ደስ የሚሉ ታሪኮች ስላሏቸው ነው። ምናልባት በሌሎች ሰዎች የተነገሩ ነገርን በእነሱ ስም የሚተረኩ፤ ብዙ ታሪኮች ይኖራሉ። ለምሳሌ እንደው አንድን ወፍ ዘራሽ ቀልድ ዝም ብሎ ከመናገር ፤ አለቃ እንዳሉት ሲባል ይጣፍጣልና ነው መሰል።
በሳቅና በፈገግታ የተሞላ ቀን ይሁንላችሁ!!!

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *