“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መፈራረቅ….ሰው የማያመልጠው የተፈጥሮ ህግ

የዚህ ሀገር ብርድ እንደ ሀገራችን ብርድ ደግ አይደለም። ሰውን ብቻም ሳይሆን ዛፎቹን ሁሉ እራቁታቸውን የሚያስቀር ጨካኝ ብርድ ነው። ትላንት በቅጠል ተውበው የነበሩት ዛፎች ዛሬ እራቁታቸውን ሳያቸው፤ እንደሰው አይምሮ ቢኖራቸው ምን ይሉ ይሆን ብዬ በምናብ አሰብኩኝ። አመቱን ሙሉ ያበቀሏቸው ቅጠሎች፤ እንደዘበት እረግፈው ማንም ሲረማመድባቸው ሲያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን? የብርዱ ከባድነት እንደሰው ተስፋ ያስቆርጣቸው ይሆን?...

እንደትልቅ ሰው አስብ እንደ ህጻን እመን!!!

(በሚስጥረ አደራው) በቀደም ጠዋት ይህንን  አባባል ከሰማሁኝ በኋላ፤ ቀኑን ሙሉ በህሊናዬ ሲያቃጭል ዋለ። ማመን ምን ያህል ከባድ ጥበብ መሆኑን ተረዳሁኝ። ሀሳቦቻችን እና ምኞቶቻችን እጃችን ሊገቡ ያልቻሉት፤ አዋቂነትቻን ጣልቃ እየገባብን መሆኑ በግልጽ ገባኝ። እምነት የሁሉም ነገር መሰረት ነው። መቼ እንደሆነ ባላስታውሰውም አንድ ሰው እንዲህ ስል ሰምቼው ነበር “በህይወቴ ቀላሉ ነገር፤ብዙ ሀብት ማካበት ነበር፤ ከባዱ ነገር...

ማነው ትክክል?

በሚስጥረ አደራው ለትክክለኛነት እና ለስህተተኛነት ጥያቄዎቻችንን መልስ እንደመስጠት፤ ለእውነት እና ለሃሰት መለኪያችን መስፈርትን እንደማግኘት፤ ለማንነታችን  ትርጉምን እንደመፈልግ ህሊናን የሚረብሽ ምን ነገር አለ? ልብ እና አይምሮ ሲቃረኑ፤ እምነት እና ፍላጎት ሲጣሉ፤ ግለኝነትና ማህብረሰብ መስመር ሲለዩ ምን ማድረግ እንችላለን?በመንታ መንገድ ላይ ቆመው እንደመዋዥቅ ምን የሚያስጨንቅ ነገር አለ? አንዳንዴ በውስጣችን ልክ...

“As A Man Thinketh” – ክፍል ሰባት

“As A Man Thinketh” -By James Allen ትርጉም- በሚስጥረ አደራው ክፍል ሰባት አስተሳሰብ እና አላማ አስተሳሰባችን ከአላማ ጋር እስካልተዛመደ ድረስ ግቡን አይመታም። የብዙ ሰዎች አይምሮ በኑሮ ወጀብ ከወዲያ ወዲህ ይንገላታል። አላማቢስነት ከደካማ ማንነት የሚመነጭ ነው። ከወዲያ ወዲህ በሃሳብ በመዋዠቅ ሰው የኑሮውን ጸጥታ ያደፈረሳል። በህይወታቸው አላማ እና ግብ የሌላቸው ሰዎች፤ በቀላሉ ለጭንቀት፤...

As A Man Thinketh- ክፍል ስድስት

“As A Man Thinketh” -By James Allen ትርጉም- በሚስጥረ አደራው ክፍል ስድስት አስተሳሰባችን በጤናችን እና አካላችን ላይ ያለው ተጽዕኖ ሰውነታችን የአይምሮዋችን ባሪያ ነው። የምናስበውን አስፈጻሚ ክፍል ማለት ይቻላል። በብልህነት የመረጥናቸውንም ሆነ በደመነፍስ የምናስባቸውን ነገሮች ሰውነታችን ወደ እውነት ይቀይራቸዋል። ሰውነታችን ለበሽታ ሲጋለጥ እና ሲጠወልግ፤ ለጠወለገ አስተሳሰባችን ዋጋ እየከፈለ ነው...

As A Man Thinketh- ክፍል አምስት

“As A Man Thinketh” -By James Allen ትርጉም- በሚስጥረ አደራው ክፍል አምስት Effect of Thought on Circumstances. የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ ጭንቀት እና መከራ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ውጤቶች ናቸው። ሰው ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር አብሮ መሄድ ሲያቅተው፤ በሰብዓዊ ህግ ስር ተገዝቶ መኖር ሲሳነው የመከራን ቀንበር ይሸከማል። የጭንቀት ማብቂያው ነፍስን ማጽዳት ነው፤ አይምሮን የሚያጎድፉ...