“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሲያምኑኝ ከፋኝ

(በሚስጥረ አደራው)  በእርግጥ…..ስስቅ አይተውኛል፤ በደስታ ስቦርቅ ስጮህ ሰምተውኛል። ሀዘንና ጭንቀት ይጋባል ስላሉኝ፤ በሽታዬን ለሌላው እንዳላጋባ፤ የውስጤን ደብቄ ደስተኛ መስዬ መታየት ጀመርኩኝ። የማስመስለው ደስተኛ መስዬ በመታየት የሰዎችን ክብር እንዳገኝ አልነበረም፤ የማስመስለው በእኔ ሀዘንና ጭንቀት ሌሎች እንዳይጨነቁ በማሰብ ብቻ እንጂ። ከዚህ በላይ ለሌሎች የሚሰጥ ምን ስጦታ አለ? የእናትነትን ፍቅር...

በመተው….

(በሚስጥረ አደራው) በቀደም ለታ አንዲት የማደንቃት ድምጻዊት ቃለመጠየቅ ሲደረግላት እየሰማሁኝ ነበር። ይህች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊት ባለትዳር ነበረችና ጋዜጠኛው የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረ። “በዚህ ሙያሽ ላይ ባለቤትሽ እርዳታ ያደርጋል? ይደግፍሻል?” “ባለቤቴ ይደግፈኛል……በመተው ይደግፈኛል፤ እራሴን እንድሆን በመተው፤ የስራ ቀጠናዬ ውስጥ ባለመግባት በመተው ይደግፈኛል” ብላ መለሰች። መልሷ ውስጤ...

ምናልባት….ምናልባት…..

(በሚስጥረ አደራው) ቁርሴን ከረፈደ ስለበላሁኝ፤ የምሳ ሰዓቴን ለእረፍት ልጠቀምበት አሰብኩኝና፤ ከመስራ ቤቴ ፊት ለፊት ወዳለው መናፈሻ ሄድኩኝ። አግድም አግድም ከተዘረጉት ወንበሮች ወደ አንደኛው እየተጓዝኩኝ ሳለ፤ከሳሩ መካከል የቀደበቀች የወረቀት ቁራጭ አይኔን ሳበችኝ። በእጅ ጽሁፍ ከተጻፈ ደብዳቤ ላይ ተቀዳ የቀረች የወረቀት ቅዳጅ ናት። የወደቀ ወረቀት የማንሳት ልምድ ባይኖረኝም የሆነ ስሜት ይህቺን የወረቀት ቅዳጅ...

ማን ቀድሞ ይታጠባል?- Zahir ክፍል ሁለት

(በሚስጥረ አደራው) “ሜሪ ሁለት የእሳት አደጋ ሰዎች የእሳት ቃጠሎን ለማጥፋት ወደ ጫካ ሄዱ እንበል። ግዳጃቸውን ሲጨርሱ በአቅራቢያው ወዳለ ወራጅ ውሃ ሄዱ። የአንደኛው ፊት በጥላሸት ተሸፍኖ ጥቁር ብሏል፤ የሁለተኛው ሰው ፊት ግን ንጹህ ነው፤ ጥያቄዬ ምን መሰለሽ፤ ከሁለቱ ማንኛቸው ፊታቸውን ቀድመው የሚታጠቡ ይመስለሻል?” “ይህማ ቀሽም ጥያቄ ነው፤ ፊቱ ጥላሸት የለበሰው ሰው ነዋ” “አይደለም!!! አየሽ ተሳሳትሽ፤ ፊቱ...

ጥላቻ ቀድሞ የሚገለው ማንን ነው? የምንጠላውን ወይስ እኛን?

(በሚስጥረ አደራው)  ሰሞኑን ታላቋ አሜሪካ በዘር ጉዳይ መታመሷ የዓለም መገናኛዎች ቀኑን ሙሉ እያወሩ የሰነበቱበት እርዕስ ነው። ምንም እንኳን በዘር ላይ የተመሰረተ ጥላቻ የነበረ ቢሆንም። ሰሞኑን ግን ይህንን ጥላቻ ከአሸለበበት የቀሰቀሰው አጋጣሚ ስለተከሰተ ነበር፤ የእይንዳንዱን ሰው የተደበቀ ስሜት ሊያወጣው የቻለው። በየዜና ጣቢያው ሲወሩ ከነበሩት ዜናዎች፤ ፉከራዎችና ምኞቶች ሁሉ ሃሳቤን የሰረቀው ነገር ግን ሌላ...