“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ማን ቀድሞ ይታጠባል?- Zahir ክፍል ሁለት

by | Oct 19, 2017 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 3 comments

(በሚስጥረ አደራው)

“ሜሪ ሁለት የእሳት አደጋ ሰዎች የእሳት ቃጠሎን ለማጥፋት ወደ ጫካ ሄዱ እንበል። ግዳጃቸውን ሲጨርሱ በአቅራቢያው ወዳለ ወራጅ ውሃ ሄዱ። የአንደኛው ፊት በጥላሸት ተሸፍኖ ጥቁር ብሏል፤ የሁለተኛው ሰው ፊት ግን ንጹህ ነው፤ ጥያቄዬ ምን መሰለሽ፤ ከሁለቱ ማንኛቸው ፊታቸውን ቀድመው የሚታጠቡ ይመስለሻል?”

“ይህማ ቀሽም ጥያቄ ነው፤ ፊቱ ጥላሸት የለበሰው ሰው ነዋ”

“አይደለም!!! አየሽ ተሳሳትሽ፤ ፊቱ ጥላሸት የለበሰው ሰው የጓደኛውን ንጹህ ፊት ያይና የእሱም ፊት ንጹህ የሆነ ይመስለዋል። በተቃራኒው ፊቱ ንጹህ የሆነው ሰው የጓደኛውን ፊት መቆሸሽ ያይና የእሱም ፊት እንደዛው የቆሸሸ ስለሚመስለው ቀድሞ ይታጠባል”

“ምን ለማለት ፈልገህ ነው?”

ከላይ ያስነበብኳችሁ ንግግር ባለፈው ክፍል አንዱን  (ሲጫኑት ማንበብ ይችላሉ) ካቀረብኩላችሁ የፓውሎ ኮዌሎ ድረሰት ከሆነው ዛሂር ከተሰኘው መጽሃፍ ላይ የተወሰደ ነው። ጸሃፊው የሁለቱን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ታሪክ የተረከው እኛ ሰዎች ምን ያህል እራሳችን በሌሎች ጥሩነትና ክፋት ውስጥ እያየን የገዛ ቆሻሻችንና ንጽህናችንን ማየት እንደሚሳነን ለማስረዳት ነው።በአንድ በኩል የሌሎች ጥሩነት እኛ ምንም ስህተት እንደሌለብን ያሳምነንና ልክ ፊቱ በጥላሸት እንደተሸፈነው ነገር ግን የጓደኛውን ንጹህ ፊት አይቶ ሳይታጠብ እንደቀረው ሰው እንሆናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የሌሎች ሰዎች ጥፋት የእኛ ጥፋት እየመሰለን ልክ የጓደኛውን ጥላሸት አይቶ ንጹህ ፊቱን እንደታጠበው ሰው እንሆናለን።

እዚህ ላይ ነው ጥበቡ የሚመስለኝ። ምናልባት ነገሮችን ይበልጥ ያሰረዳን ከሆነ በመጽሃፉ ላይ ያለው ገጸባህሪ ከላይ የሰፈረውን ንግግር የተናገረበትን ምክንያት ላጫውታችሁ። ሰውየው ፍቅርን ፍለጋ ብዙ ባክኗል፤ ብዙ ድንቅ ሴቶችም በህይወቱ አጋጥመውታል ነገር ግን ማንኛቸውም የሚጋልብ ስሜቱን አስረው እፎይ ሊያሰኙት አልተቻላቸውም ነበር። ምንም እንኳን መልካም ሴቶች ቢሆኑም፤ እንደጉልቻ መለዋወጣቸው አልቀረም፤ ይሄኔ ነበር “ምናልባት የእነሱን መልካምነት እያየሁኝ እኔም መልካም የሆንኩ እየመሰለኝ፤ እነሱ ደግሞ የእኔን ጥፋት እያዩ ጥፋተኝነት እየተሰማቸው፤ አንዳችን የሌላችንን ፊት እያየን የተሸዋወድነው” ሲል ያሰበው።

አንዳንዴ ሰዎች ሲበዛ መልካም ይሆኑልናል፤ እኛ አጥፍተን እንኳን የእነሱ መልካምነትና ፍቅር የእኛን ጥፋት እንዳናይ ያደርገናል። ለምሳሌ ባሏ ሁሌ የሚበድላትን ምስኪን ሚስት አስቧት የእሷ ትእግስት የእሱን ክፋት ይጋርደዋል፤ የእሱ ክፋት ደግሞ የእሷን ንጽህና እንዳታይ ያደርጋታል፤ ለዚህም ነው ስህተቱ የእሷ ባይሆንም ይቅርታ ለመጠየቅ የምትገደደው። ጥንካሬዋን በእሱ ድክመት ውስጥ ታየዋለች፤ ልክ ፊቱ ንጹህ ቢሆንም የጓደኛውን ጥላሸት አይቶ ቆሻሻ ነኝ እንዳለው ምስኪን ሰራተኛ።

ሁላችንም የገዛ ፊታችንን እያየን ካልታጠብን በስተቀር በዚህ ጥልፍልፎሽ ውስጥ መታሰራችን አይቀርም፤ የሌላው ንጽህና የእኛ መስሎን ከነጥላሸታችን እንቆያለን አልያም የሌላው ጥላሸት የእኛ መስሎን መልካሙን ገጽታችንን ማየት ይሳነናል። ከእኛ ሲያልፍ ደግሞ በእኛ ቆሻሻ ሌሎች መታጠብ ሳይኖርባቸው ወንዝ እንዲወርዱ እናስገድዳቸዋለን። ምናልባት የህይወት ነጸብራቅነት ሌላው ገጽታ ይሆን?

“Marie, let’s suppose that two firemen go into a forest to put out a small fire. Afterwards, when they emerge and go over to a stream, the face of one is all smeared with black, while the other man’s face is completely clean. My question is this: which of the two will wash his face?
That’s a silly question. The one with the dirty face of course.’
No, the one with the dirty face will look at the other man and assume that he looks like him. And, vice versa, the man with the clean face will see his colleague covered in grime and say to himself: I must be dirty too. I’d better have a wash.’

What are you trying to say?’- Zahir Page 181

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

3 Comments

  1. abreham

    waw betam lek new bezuewn geze benedezeh wuset new yalenew.andachen beandachen wuset mesetawet nen

    Reply
  2. amsalu

    lek nesh

    Reply
  3. AYALEW MINALE

    BETAM ARIF ARIF NEGROCH ALU

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *