Zahir ;The rout to holiness or madness-ክፍል አንድ

Posted on Posted in መነቃቂያ

(በሚስጥረ አደራው)

ለዛሬ እንደመወያያም አልያም እንደ ሃሳብ ላነሰው የወደድኩት የፓውሎ ኮዌሎ ድርሰት ከሆነውና “ዛሂር” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከወደድኳቸው አባባሎች ውስጥ አንደኛውን ነው። ዛሂር ማለት ይላል የመጽሐፉ ደራሲ፦

In Arabic, Zahir is a visible presence incapable of going unnoticed. It is someone or something that once it comes to our attention occupies our very being, we can think of nothing else. ቀለል ባለ ትርጉም ዛሂር ማለት ሃሳባችንን ሙሉ የሚቆጣጠር ነገር ማለት ነው፤ሰው ወይም ሌላም ነገር ሊሆን ይችላል። አንዴ አይምሮዋችን ውስጥ ከገባ ለማወጣት የሚከብደን፤ ያለሱ ሌላው ሃሳብ ሃሳብ የማይመስለን ያ ነገር ዛሂር ሲሆንብን ነው።

“Esther asks why people are sad”

“That’s simple” said the old man “They are prisoners of their personal history. Everyone believes that the main aim in life is to follow plan. They never ask if that plan is Theirs or if it was created by another person. They accumulate experiences, memories, things, other people’s ideas and its more than they can possibly cope with. And that is why they forget their dreams.”- ገጽ 209

ኤስተር በመጽሐፉ ላይ ያለች አንዲት ገጸ ባሕሪ ናት። ከላይ የተቀነጨበው ንግግር የኑሮዋን ትርጉም ለመፈለግ ይረዳት ዘንድ ወደ ሩቅ ሃገር ተጉዛ ከአንድ አዋቂ  ጋር ያደረገችው ንግግር ነበር።

“ሰዎች ለምን ሃዘንተኛ ይሆናሉ?”

“በገዛ ታሪካቸው ስለሚታሰሩ”።

እያንዳንዳችን አሁን “እኔ” ብለን የምንገልጸው ማንነት ከጀርባው ቡዙ የታሪክ ጉንጉን አለው። ሰውየው ለኤስተር የመለሱላት መልስ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ ነበር። ሰዎች ደስታቸውን የሚነጠቁት ለራሳቸው በሚነግሩት ታሪክ ስለሚታሰሩ ነው። ለራሳችን የምንነግረው ታሪክ ደግም፤ ካሳለፍነው ህይወት ውስጥ ከመልካሙ ይልቅ መጥፎውን፤ ከስኬታችን ይልቅ ውድቀታችንን፤ ከትክክሉ ይልቅ ስህተቱን፤ ስለራሳችን ካለን አመለካከት ይልቅ ሌላው ስልኛ ያለውን አመለካከት አጉልቶ የሚያሳይ የተዛባ ታሪክ ነው።በእንዲህ አይነቱ ታሪክ መታሰርን ነው “Prisoners of their personal history” ሲሉ የገለጹት።

ትላንትና፤ ዛሬና ነገ በቦታ የሚጣሉት በሰው ህይወት ውስጥ ብቻ ሳይሆን አይቀርም? ታላንትናችን የኖረበትን ትቶ ፈቀቅ ካላለ ለአሁኑ ደቂቃ እንዴት ቦታ ይኖረናል? ኑሮ የሚቀመረው በጊዜ ነው፤ ስለጊዜ ከተባሉ አባባሎች ውስጥ የጊዜንና የህይወትን ግንኙነት በሚገባ ይገልጻል ብዬ የማስበው ይህንን ነው፤-

“ህይወቴን እውዳለው የሚል ሰው ጊዜውን እንዲሁ አያጠፋም፤ ምክንያቱም ህይወት የተሰራችው ከጊዜ ነውና”። እያንዳንዱ ነገራችን በጊዜ ላይ የተመሰረተ ነው፤ አይምሮና ጊዜ ጎን ለጎን ወይም ደግሞ ቢያንስ በተቀራራቢ እርቀት ካልተጉዙ ትልቅ የህይወት ክፍተት ይከሰታል። ያ ደግሞ እስር ነው…..ወይ በትላንትና ትዝታ ወይም በነገ ምኞት መታሰር። ከሁሉም ግን አስከፊው በትላንት ታሪካችን ዛሬንና ነገን ማበላሸት ነው።

ሰው ምንም ያህል የውጪ ጠላት ቢኖረው የገዛ እራሱን ያህል የሚጥለው ግን ማንም የለም። ለራሳችን የምንነግረው ታሪክ ሁሉ ነገራችንን ይወስነዋል። በገዛ ህሊና የሚተረክ ታሪክ ወይ የነጻነት ቁልፍ ነው አልያም ደግሞ ከባድ እስር ቤት ነው። ያለፈ ታሪክን ፈጽሞ ለመርሳት መሞከር ከመጸሐፍ ላይ ምዕራፍን እየገነጠሉ እንደመጣል ነው። መርሳት ብንችል እንኳን ታሪካችን የተገነጠሉ ምዕራፎች እንዳሉት ጎዶሎ መጽሐፍ ይሆንብናል። ነገር ግን ያለፈ ታሪካችን ከጊዜው ጋር እንዲያልፍ ልንፈቅድለት ይግባል አለበለዚያ ስህተቶቻችን እና ውድቀቶቻችን ካቴና ሆነው ባለንበት ሊያቆዩን ይችላሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ነው ህልማችንን የምረሳው። ህልምን ስናነሳ ከላይ የሰፈረው አባባል ላይ ደስ የሚል ነገር አለ። ሌላው የሰዎችን ደስታ የሚነጥቀው ነገር ኑሮን እንደ አንድ የአላማ ማሳኪያ መድረክ ብቻ አድርጎ መቁጠሩ ነው። አላማ መልካም ነገር ቢሆንም፤ መኖር ማለት አንድን ህልም ማሳካት ብቻ ነው ብሎ ማሰቡ፤ ህልማችን በእርግጥም የእኛ ነው? ብለን እንዳንጠይቅ ያደርገናል፤ ያው…. በስኬት ግርግር ይበልጡንም እንዳንጠፋ ለማለት ነው።

2 thoughts on “Zahir ;The rout to holiness or madness-ክፍል አንድ

  1. Self awareness is the key.
    We crawl is the system they built, to be called successful in their system. Even they don’t want all people to be successful, it scares them, cuz when u reach on success, u push more, and more and u might discover something they have been hiding.
    They don’t want ppl to know their true higher self, they made ppl to believe they need permission from a higher entity (God) to be successful, and all the good stuff.
    The past is the past, the future is the future, it’s not in our hand neither for the universe. There’s only “what is happening”. The “Now” will be always on our hand and we should make “the now count”.
    ….Btw declacifying the pineal gland gives us the true self awareness that we’ve been looking for our whole Life. Pineal gland (third eye) is a gland in our brain filled with water and crystals,it secrets the DMT. Its not demonic or Illuminati as they brain washed us. They even spray white chemicals on air and put fluoride in our toothpaste, drinking bottled or tap water. Fuoride is not good for ppl, it automatically focus on the pineal gland and calcify it, sucking the water out turning it in to empty dried bony organ, which allows them to manage us easily. We do what they tell us, we just strive hard our life to be the most obedient and get awarded for it, cuz we become “Successful”

Do you have any comments?