“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

በመተው….

(በሚስጥረ አደራው) በቀደም ለታ አንዲት የማደንቃት ድምጻዊት ቃለመጠየቅ ሲደረግላት እየሰማሁኝ ነበር። ይህች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊት ባለትዳር ነበረችና ጋዜጠኛው የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረ። “በዚህ ሙያሽ ላይ ባለቤትሽ እርዳታ ያደርጋል? ይደግፍሻል?” “ባለቤቴ ይደግፈኛል……በመተው ይደግፈኛል፤ እራሴን እንድሆን በመተው፤ የስራ ቀጠናዬ ውስጥ ባለመግባት በመተው ይደግፈኛል” ብላ መለሰች። መልሷ ውስጤ...
ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

(ሚስጥረ አደራው) ብዙ እቃዎችን ስንገዛ አብሮ የሚሰጠን የመመሪያ ደብተር ወይም ማንዋል አለ። ይህ ማኑዋል የገዛነው እቃ እንዴት እንደሚሰራ፤ እንዴት እንደሚገጣጠም፤ እንዴት እንደሚለወጥ፤ ችግር ካለ ማንን እንደምናማክር፤  ሌሎች ብዙ ስለ እቃችን ጠቃሚ እውነታዎችን የሚይዝ ደብተር ነው። ብዙዎቻችን ግን ይህንን ማኑዋል ጊዜ ወስደን አናነበውም። ማኑዋሉን ሳያነብ የገዛውን እቃ ለመገጣጥም የሚሞክር ሰው ምናልባት...

ምናልባት….ምናልባት…..

(በሚስጥረ አደራው) ቁርሴን ከረፈደ ስለበላሁኝ፤ የምሳ ሰዓቴን ለእረፍት ልጠቀምበት አሰብኩኝና፤ ከመስራ ቤቴ ፊት ለፊት ወዳለው መናፈሻ ሄድኩኝ። አግድም አግድም ከተዘረጉት ወንበሮች ወደ አንደኛው እየተጓዝኩኝ ሳለ፤ከሳሩ መካከል የቀደበቀች የወረቀት ቁራጭ አይኔን ሳበችኝ። በእጅ ጽሁፍ ከተጻፈ ደብዳቤ ላይ ተቀዳ የቀረች የወረቀት ቅዳጅ ናት። የወደቀ ወረቀት የማንሳት ልምድ ባይኖረኝም የሆነ ስሜት ይህቺን የወረቀት ቅዳጅ...

አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

(በሚስጥረ አደራው) “ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ለፈጣሪ ባለን የምስጋና መጠን ይወሰናል። ህይወታችንን እጅግ መልካም ለማድረግ አልያም እርግማን ወደሞልው የሰቀቀን ኑሮ ለመለወጥ የሚያስችለን የገዛ አመለካከታችን ነው። አንዳንዶቻችን በቤታችን ጓሮ የተተከለውን ጽጌሬዳ ስንመለከት ጽጌሬዳው በእሾህ መወረሱ ያበሳጨናል፤አንዳንዶች ደግሞ እሾሁ ጽጌሬዳ ማብቀሉ ይገርማቸዋል። ሁሉ ነገር እኛ በሚኖረን የህይወት መነጽር ይወሰናል።...

ሀሙስ ከደረስን እሁድ ብዙ አይርቅም!

(በሚስጥረ አደራው) ህይወት ከሰባት ቀናቶች የበለጠ እድሜ የላትም፤ የትኛው ቀን ላይ ነን? ይህንን ያለው ታዋቂው ገጣሚ ሮበት ብላይ ነው።  ገጣሚው ይህንን የተናገረው አሜሪካ በወቅቱ የነበረችበትን ጦርነቶች አስመልክቶ ተቃውሞውን በገለጸበት ግጥሙ ውስጥ ነበር። ይህ ሰው ስነጥብበን ለሰላም ለማዋል ብዙ ተግቷል፤ እንደውም “American Writers Against the Vietnam War” የሚል ማህበርም መስርቶ ነበር፤ ይህ...