by Mistre | Nov 29, 2020 | ግጥም
ቢኖር … ቀን ቀን ከሰው ጋራ፤ የረሳሽው ጭንቀት፤ ሃሳብ ከነበረ ሌሊቱን ጠብቆ፤ ሲጋፋሽ ካደረ በቅዠት አለም ውስጥ፤ ላነባሽውን ለቅሶ ፊትሽን የሚያደርቅ፤ በመዳፍ እጆቹ እንባሽን አብሶ ቢኖር ከጠበበ ጊዜ፤ ከተጣበበ ሰዓት፤ ከጠፋ ደቂቃ፤ መናፈቅሽን አውቆ ጊዜ ዘግኖ ‘ሚሰጥ፤ እልፍ አእላፍ ዘመን ከሰው ሁላ ነጥቆ ቢኖር የአለም ኦናነንት፤ የፍቅር መመነን፤ እንደሳት ሲፈጅሽ አውሎ ነፋስ ሆኖ፤ ፍቅር እንደአሸዋ፤ የሚያዘንብ...
by Mistre | Aug 19, 2020 | መነቃቂያ inspiring stories
(በሚስጥረ አደራው) ጽሁፉን የሚያነበውና ታሪኩ የተጻፈለት ሰው ስለ አንድ ጽሁፍ እኩል ስሜት ሊኖራቸው አይችልም። ሰሞኑን አንድ ትምህርት ላይ ይህ ታሪክ ከጆሮዬ ዘለቀ። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ብቸኛ ማንበብ የሚችል ሰው ነበረ። ይህ ሰው ከእርሱ ሌላ የሚያነብ ሰው በከተማው ባለመኖሩ ከፍተኛ ኩራት ይሰማው ነበር። ኩራት ብቻም ሳይሆን ደብዳቤ እንዲነበብላቸው ወደ እርሱ የሚመጡ ሰዎችን ይንቅ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን...
by Mistre | Aug 12, 2020 | መነቃቂያ inspiring stories
(በሚስጥረ አደራው) ይህንን አባባል ስሰማ የምር ደንግጫለሁ። “የመጨረስን ጣዕም ካላወቅክ፤ ለራስህ ክርብ አይኖርህም” ። በዛው ቅጽበት ጀምሬ የጨረስኩት ምንድን ነው ብዬ እራሴን ጠየቅኩኝ? የጀመርኳቸው ብዙ ነገሮች በህሊናዬ መጡ፤ የጨረስኳቸው ነገሮች ግን..… ነገርን ጀምሮ መጨረስ የሚሰጠው ስሜት ልዩ ነው። ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማን ለሌሎች የገባነውን ቃል ማክበር ሲሳነን ነው። የጥፋተኝነት ስሜት...
by Mistre | Jun 14, 2020 | መነቃቂያ inspiring stories
(በሚስጥረ አደራው) ፍቅር በፍትህ አፈር ላይ የምትበቅል ተክል ናት። የፍትህ አፈር ሚዛናዊ ነው፤ ያልተመጣጠነ ነገር ሁሉ ሚዛኑን ይደፋዋል። ከልክ በላይና በታች የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተክሉን ይገለዋል። ሁሉንም ነገር በልኩና በመጠኑ፤ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ሲሆን፤ ፍቅር ታብባለች። The Road less Traveled በተሰኘው መጽሃፍ ላይ ጸሃፊው ፍቅርን እንዲህ ውብ አድርጎ ከፍትህና ከመሪነት ጋር ሽምኖ አቅርቦታል...
by Mistre | Oct 21, 2019 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት
በሚስጥረ አደራው ዛፍ መሆን እመኛለሁ ያለውን ባለቅኔ ዛሬ ነበር ማግኝት “መጽሀፍ አንብቤ እፎይ ባልኩኝ ሰዓት ምነው ዛፍ በሆንኩኝ፤እያልኩ እመኛለሁ ወይ ፍሬ አፈራለሁ ወይ ጥላ እሆናለሁ ቢያንስ አንዲት ወፍ በግል አምና ጎጆ ቤቷን፤ እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ ያኔ በትክክል ለአደራ እበቃለሁ”- ነብይ መኮንን/ስውር ስፌት ሰሞኑን በምኖርበት ከተማ ዛፎች ቅጠላቸውን የሚያጡበት ወቅት ነው። ላለፉት ወራቶች አረንጓዴ ለብሰው...
Recent Comments