“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሲያምኑኝ ከፋኝ

(በሚስጥረ አደራው)  በእርግጥ…..ስስቅ አይተውኛል፤ በደስታ ስቦርቅ ስጮህ ሰምተውኛል። ሀዘንና ጭንቀት ይጋባል ስላሉኝ፤ በሽታዬን ለሌላው እንዳላጋባ፤ የውስጤን ደብቄ ደስተኛ መስዬ መታየት ጀመርኩኝ። የማስመስለው ደስተኛ መስዬ በመታየት የሰዎችን ክብር እንዳገኝ አልነበረም፤ የማስመስለው በእኔ ሀዘንና ጭንቀት ሌሎች እንዳይጨነቁ በማሰብ ብቻ እንጂ። ከዚህ በላይ ለሌሎች የሚሰጥ ምን ስጦታ አለ? የእናትነትን ፍቅር...
ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

ማኑዋል- Life’s Instruction Manual

(ሚስጥረ አደራው) ብዙ እቃዎችን ስንገዛ አብሮ የሚሰጠን የመመሪያ ደብተር ወይም ማንዋል አለ። ይህ ማኑዋል የገዛነው እቃ እንዴት እንደሚሰራ፤ እንዴት እንደሚገጣጠም፤ እንዴት እንደሚለወጥ፤ ችግር ካለ ማንን እንደምናማክር፤  ሌሎች ብዙ ስለ እቃችን ጠቃሚ እውነታዎችን የሚይዝ ደብተር ነው። ብዙዎቻችን ግን ይህንን ማኑዋል ጊዜ ወስደን አናነበውም። ማኑዋሉን ሳያነብ የገዛውን እቃ ለመገጣጥም የሚሞክር ሰው ምናልባት...

ምናልባት….ምናልባት…..

(በሚስጥረ አደራው) ቁርሴን ከረፈደ ስለበላሁኝ፤ የምሳ ሰዓቴን ለእረፍት ልጠቀምበት አሰብኩኝና፤ ከመስራ ቤቴ ፊት ለፊት ወዳለው መናፈሻ ሄድኩኝ። አግድም አግድም ከተዘረጉት ወንበሮች ወደ አንደኛው እየተጓዝኩኝ ሳለ፤ከሳሩ መካከል የቀደበቀች የወረቀት ቁራጭ አይኔን ሳበችኝ። በእጅ ጽሁፍ ከተጻፈ ደብዳቤ ላይ ተቀዳ የቀረች የወረቀት ቅዳጅ ናት። የወደቀ ወረቀት የማንሳት ልምድ ባይኖረኝም የሆነ ስሜት ይህቺን የወረቀት ቅዳጅ...

አለምን እየመራት ያለው ሰይጣን ማን ነው?

(በሚስጥረ አደራው) “ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ለፈጣሪ ባለን የምስጋና መጠን ይወሰናል። ህይወታችንን እጅግ መልካም ለማድረግ አልያም እርግማን ወደሞልው የሰቀቀን ኑሮ ለመለወጥ የሚያስችለን የገዛ አመለካከታችን ነው። አንዳንዶቻችን በቤታችን ጓሮ የተተከለውን ጽጌሬዳ ስንመለከት ጽጌሬዳው በእሾህ መወረሱ ያበሳጨናል፤አንዳንዶች ደግሞ እሾሁ ጽጌሬዳ ማብቀሉ ይገርማቸዋል። ሁሉ ነገር እኛ በሚኖረን የህይወት መነጽር ይወሰናል።...

ጠጌ ጠጌ አይነኬ “Asymptote”

(በሚስጥረ አደራው)  ምንም እንኳን ሂሳብ ላይ እምብዛም ብሆንም ካልተረሱኝ ጥቂት የሂሳብ ጥበቦች (መደመርና መቀነስ ናቸው ዋነኞቹ መቼም) ሌላ አይምሮዬ ውስጥ አልላቀቅም ብሎ የቀረው “Asymptote” የሚለው የሂሳብ ጽንሰ ሃሳብ ነው። የያኔው የሂሳብ አስተማሪዬ አቶ ኤሊያስ ለ” Asymptote” የሰጡን አማርኛ ፍቺ በወቅቱ “ጠጌ ጠጌ አይነኬ” የሚል ነበር።...