“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

As A Man Thinketh- ክፍል አራት

by | Jul 24, 2015 | ትርጉሞች | 1 comment

“As A Man Thinketh” -By James Allen

ትርጉም- በሚስጥረ አደራው

ክፍል አራት

Effect of Thought on Circumstances.

የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ

የሚከተሉትን ሰዎች ታሪክ እንደምሳሌ እንውሰድ፦የመጀመሪያው ሰው በኑሮው የሚማረር ነው፤ በድህነት ውስጥ ያለ።ሁኔታዎች እንዲለወጡ ይፈልጋል፤ በስራውም ሆነ በመኖሪያው ምቾቱ እንዲጨምርለትም ይሻል። የሚከፈለው ደሞዝ አነስተኛ ስለሆነ ፍትህን ለማግኘት ብሎ ስራውን አክብሮ አይሰራም።ለሚከፈለው አነስተኛ ክፍያ ምላሽ ስራውን በመበደል አሰሪውን የተበቀለ ይመስለዋል። እንዲህ አይነት ሰው የብልጽግና መሰረት የሆኑት ዋና ነጥቦች አልገቡትም ማለት ነው። ስብዕናው እየተማረረበት ካለው ህይወት ሊያወጣው አይችልም፤ በአንጻሩ የድህነቱን ጉድጓድ ወደ ጥልቅ ይቆፍርበታል እንጂ።

ሁለተኛው ሰው ሃብታም ሲሆን፤ በባህሪው ሲበዛ ስግብግብ ነው፤ ይህ ስግብግብነቱ ብዙ ምግብ በመመገብ የሚመጣ ክፉ በሽታ ላይ ጥሎታል። ገንዘቡን ለሌሎች ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም፤ ሆዳምነቱን ግን ለምንም ነገር አሳልፎ መስጠት አይፈልግም። በገንዘቡ ደስተኛ ህይወትን መምራት ይፈልጋል; ስግብግብ ባህሪው ግን ክፉ በሽታ ላይ ስለጣለው ህይወቱን እንዳያጣጥም አድርጎታል። እንዲህ አይነት ሰው፤ ጤናማ ህይወትን ለመምራት ብቁ አይደለም፤ ምክንያቱም ጤናማ ህይወትን ለመምራት መሰረት የሆኑ ነጥቦች ስላልገቡት።

ሶስተኛው ሰው በስሩ ሰራተኞች ያሉት ቀጣሪ ነው። ይህ ሰው ገንዘብ ለመቆጠብ እና ትርፍ ለማግኘት ሲል ለሰራተኞቹ ተገቢውን ክፍያ አይከፍላቸውም።  ነገር ግን ትርፋማ አይደለም፤ ለኪሳራውም ሁኔታዎችን ያማርራል፤ የራሱ ስራ ተመልሶ እየጠለፈው መሆኑን አይረዳም። እንዲህ አይነት ሰውም ትርፋማ ለመሆን የበቃ አይደለም።

እንዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች የሰው ልጅ ለሚገጥሙት ችግሮች በአብዛኛው መንስዔው እራሱ  እንደሆነ ለማስረዳት የተጠቀምንባቸው ምሳሌዎች ናቸው። ጥሩ ውጤን እየጠበቀ፤ ከሃሳቡ ጋር አብረው የማይሄዱ ድርጊቶችን ይፈጽማል። ማለትም ወደ ጥሩ ውጤት የሚመሩ ነገሮችን በማድረግ ፋንታ ወደ ተቃራኒው ጥግ የሚያደርሱ እርምጃዎችን መውሰድ ማለት ነው። የሶስቱን ሰዎች ምሳሌ ወሰድን እንጂ፤ በተለያየ አይነት መልኩ ከፍላጎታቸው ጋር የሚቃረኑ ድርጊቶችን  ሰዎች ሲፈጽሙ ይታያሉ።

አስተሳሰብ በጣም ጥልቅ የሆነ ነገር ነው፤ የእያንዳንዱ ሰው የደስታ  ትርጉምም የተለያየ ነው፤ በዚህ ምክንያት ሁኔታዎች መወሳሰባቸው አይቀርም። አንድ ሰው ሌላውን ከውጪ በሚያየው ነገር ብቻ መዳኘት አይችልም። ለምሳሌ አንድ ሰው በጣም ታምኝ ሆኖ ሳለ፤ ችግረኛ ሆኖ እናገኘዋለን። ታማኝ ያልሆነው ሌላው ሰው ደግሞ፤ ባለጸጋ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። ይህንን በተመለከት ሰው ታምኝ ስለሆነ ድሃ ይሆናል፤ አጭበርባሪ ስለሆነ ደግሞ ሃብታም ይሆናል ብሎ መደምደም ስህተት ነው። ምክንያቱን ታማኝ ያልሆነው ሰው ሙሉ በሙሉ መጥፎ፤ ታማኝ የሆነው ሰው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ጻዲቅ ነው ማለት ስለማይቻል። ታማኝ ያልሆነው ሰው ታማኝ የሆነው ሰው የሚጎድለው መልካም ነገር ሊኖረው ይችላል። ታማኝ የሆነው ሰው ድግሞ በሌላኛው ባህሪ ውስጥ የሌለ ክፉ ባህሪ ይኖርበት ይሆናል። ታማኙ ሰውም ሆነ አጭበርባሪው የመልካምነታቸውን ያህል (ባላቸው የተለያየ መልካም ጎን)፤ የዘሩት ያጭዳሉ፤ እንደ መጥፎ ባህሪያቸውም ዋጋቸውን ይከፍላሉ።

መልካምነት ይጎዳል የሚለው አመለካከት በብዙ ሰዎች ዘንድ የተለመደ አስተሳሰብ ነው። ሰው አይምሮውን ፍጹም እስካላጸዳ ድረስ፤ እያንዳንዱን ክፉ ሃሳብ እና እኩይ ተግባር ከነፍሱ ላይ አጥቦ እስካላስወገደ ድረስ፤ ችግሮቹ በመጥፎ አስተሳሰቡ ምክንያት የሚከፍላቸው ዋጋዎች መሆናቸውን መረዳት አይቻለውም። ጥሩው ለመጥፎ፤ መጥፎውን ለጥሩ ለውጦ የሚሰጥ ህግ አለማችን የላትም። መልካም አስተሳሰቦች በፍጹም መጥፎ ውጤቶችን አይሰጡም። መጥፎ ሃሳቦች እና ድርጊቶችም በፍጹም ጥሩ ውጤቶችን አይሰጡም። ይህ ማለት ከበቆሎ፤ በቆሎ ይወጣል እንጂ ሌላ ነገር አይፈጠርም ማለት ነው። ሰዎች ይህንን ህግ በተፈጥሮ ደረጃ ያውቁታል (በቆሎ ዘርቶ ብርቱካን የሚጠብቅ ገበሬ የለም)፤ ነገር ግን በራሳቸው ህይወት ውስጥ አስገብተው መረዳት ግን ይሳናቸዋል። አስተሳሰብንም እንድዚህ የተፈጥሮ ህግ ለመረዳት ቀላል ነው፤ በአይምሮዋችን ያልዘራነውን በኑሮዋችን አናጭደውም።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. Tariku

    really important truth….that no one can reject…

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *