“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

As A Man Thinketh- ክፍል ሶስት

by | Jul 22, 2015 | ትርጉሞች | 0 comments

“As A Man Thinketh” -By James Allen

ትርጉም- በሚስጥረ አደራው

ክፍል ሶስት

“Effect of Thought on Circumstances.”

“የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”

ሰው በውስጡ ብዙ ሃሳቦች፤ ምኞቶች እና ተስፋዎች አሉት። ከእነዚህ መካከል ገዝፈው ህይወቱን  የሚመራባቸው አስተሳሰቦች እና ምኞቶች እንዲሁም ተስፋዎች በስተመጨረሻ ፍሬ ማፍራታቸው አይቀርም። ግራ ቢያጋባም ሰው ለእሱ መልካም ካልሆነ ስፍራ (ጸሃፊው እስር ቤትን እና ድህነትን ይጠቅሳል) በእድል ወይም በአጋጣሚ አይገኝም። ይልቁንም በኑሮ ጉዞ ላይ ይመሩት በነበሩት አስተሳሰቦች እና ጥልቅ ፍላጎቶች ምክንያት ቀስ እያለ ተገፍቶ የደረሰበት ስፍራ ነው። በሌላ በኩል መልካም አስተሳሰብ የነበረው ሰው ድንገት ስህተት ቢሰራ እና ወንጀል ቢፈጽም፤ ውጫዊ በሆነ ነገር ተገፋፍቶ አልያም በአጋጣሚ ተገዶ ነው ልንል አንችልም። በአንጻሩ ያ የወንጀለኛ አስተሳሰብ ከመልካም ስብዕናው ስር ተደብቆ ለዘመናት የኖረ እና ሰዓቱ ሲደረስ የፈነዳ ነው።

አጋጣሚዎች ሰዎችን አይለውጡም፤ ሰውን ከድብቅ ማንነቱ ጋር ያስተዋውቁታል እንጂ። ሰውን ድንገት ከኑሮ ጎትቶ ወደ መጥፎ አለም የሚከት አጋጣሚ የለም፤ ወደ መጥፎ የሚመሩ አስተሳሰቦችን በውስጣችን ካልያዝን በቀር። በሌላ በኩል ወደ ደስታ ድንገት የሚወስድ አቋራጭ መንገድ ወይም አጋጣሚም የለም፤ ያ የደስታ ሃሳብ እና ምኞት ለረጅም ጊዜ በሰው ልብ ውስጥ የኖረ መሆን አለበት። ለዚህ ነው ሰው የኑሮው ጌታ፤ የአስተሳሰቡ ባለቤት እንዲሁም የህይወቱ ጠራቢ ነው የምንለው።

ወደዚህ ምድር ከመጣን ጀምሮ፤ በምድር ጉዞዋችን እያንጠለጠልን የምናልፋቸው የህይወት አጋጣሚዎች እና ልምዶች፤ የነፍሳችን ነጸብራቆች ናቸው። እንደ ነፍሳችን ንጽህና እና ግድፈት የሚከፈሉን ዋጋዎች።ሰው ወደራሱ የሚስበው የሚፈልገውን ነገር ሳይሆን፤ እራሱ የሆነውን ነገር ነው። አንዳንዴ የምንወስናቸው ውሳኔዎች እና ምኞቶቻችን እውን ከመሆን ሲገደቡ እናያለን።እንዲህ  የሚሆነው በውስጣችን ተደብቀው ያሉ አስተሳሰቦች እና ምኞቶች በምትኩ እውን ስለሚሆኑ ነው (Innermost desires and thoughts)። ድርጊታችን እና አስተሳሰባችን የእጣ ፋንታችን ወሳኞች ናቸው፤ የኑሮ እስር ውስጥ የሚከረችሙ ብረቶች ወይም እንደ ወፍ በነጻነት የሚያበሩ መልዕክቶች።

ሰው ስለተመኘ እና ስለጸለየ ብቻ የሚፈልገውን ያገኛል ማለት አይቻልም። ምኞቱ እና ጸሎቱ እውን የሚሆኑት ከተግባሩ እና ከአስተሳሰቡ ጋር መዋሃድ ሲችሉ ብቻ ነው። ታዲያ ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ሳይስማማ ሲቀር እና ከሁኔታዎች ጋር ሲጋፈጥ በውጤቶች ላይ እያመጸ ነው ማለት ነው። ችግሩ ከውጤቱ ጋር መጋፈጡ እና ለመለወጥ መነሳቱ ሳይሆን በጊዜው ሁሉ የውጤቱን መንስዔ ሲያዳብር መኖሩ ነው ። መንስዔውን ያዳብራል ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰዎች ኑሮዋችውን ለማሻሻል ይፈልጉና እራሳቸውን ለማሻሻል ግን ፈቃድኛ አይሆኑም፤ ስለዚህም የራሳቸው እስረኛ ሆነው ይቀራሉ። እራሱን በወቀሳ እና በማሳነስ የማያሸማቅቅ ሰው፤ ልቡ የመረጠውን ማሳካት አይሳነውም። ሌላው ይቅር ገንዘብን ለማከማቸት ብቻ የሚደክም ሰው እራሱ በቅድሚያ ብዙ ማንነቱን የሚነኩ መስዋቶችን ለመክፈል ይገደዳል(ከገንዘብ የላቀ ህልም ያለው ሰው ደግሞ እራሱን በእጅጉ ለመለወጥ ዝግጁ መሆን አለበት)።ጠንካራ የሆነ ህይወትን ለመምራት፤ ጠንካራ የሆነ ማንነትን ይጠይቃልና።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *