“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር አይሁን

by | Jun 22, 2018 | መነቃቂያ inspiring stories | 2 comments

(በሚስጥረ አደራው)

“There’s a place in you that you must keep inviolate. You must keep it pristine, clean, so that nobody has the right to curse you or treat you badly. Nobody. No mother, father, no wife, no husband, nobody.” –Maya Angelou

ሰዎች ስለወቀሱን የማይርድ፤ ስለኮነኑን የማይወድቅ፤ ስለፈረዱብን የማይሞት፤ ስለጠሉን የማይፈራ፤ ስለተዉን የማይደክም መንፈስ በውስጣችን ሊኖር ግድ ይለናል። ከፈጣሪ የተሰጠን እውነተኛው ማንነታች ይህ ነው። ብዙዎቻችን ደካማ ስለተባልን ደክመናል፤ ሃጥያተኛ ስለተባልን ቆሽሸናል፤ ወንጀለኛ ስለተባልን ታስረናል።የሌሎች ሰዎች አስተያየትና መስፈርት ከእውነተኛው ማንነታችን አርቆናል፤ ሰላም ካለበት ስፍራ አውጥቶ የይሉኝታ ሰፈር ኗሪ አድርጎናል።

እውነት ነው ማናችንም ከተጽዕኖ ማምለጥ አንችልም። በመልካምም ሆነ በመጥፎ ሞርደ በየእለቱ መሞረዳችን አይቀርም። ማንነታችን የቤተሰባችን፤ የጓደኞቻችን፤ የአካባቢያችን የባህልና የእምነታችን ውጤት ነው። ሁሉም ነገራችን ላይ የአካባቢያችን ተጽዕኖ ያርፍበታል፤ ልክ ጣሪያ እንደሌለው ቤት በውጪ ያለው ሙቀትና ቅዝቃዜ፤ ዝናብና ንፋሱ፤ አቧራና ሽታው የራሳቸውን አሻራ ያኖሩበታል። በሌሎች ሰዎች ጉንፋን እኛ እናስነጥሳለን፤ በማህበረሰብ በሽታ እኛ የአልጋ ቁራኛ እንሆናለን፤ በሌሎች የእምነት ጥበት እኛ እንጨነቃለን፤። ለዚህ ነው ደስታችን በብዙ ነገሮች ተጽዕኖ ስር የሚወድቀው።

ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል፤ ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን!!!

 

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

2 Comments

  1. hirsi bashiir

    ena masgenalen astemariye

    Reply
  2. ANTIPAS OjO

    betam amesegnalew abzagnaw tsihufshn anbibewalew ena bezhiw ketyi

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *