“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የ20ኛው ክፍለ ዘመን አስርቱ ትዕዛዛት

by | Apr 8, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

እኒህ ትዕዛዛት፤ ሙሴ የጻፋቸው አስርቱ  ትዕዛዛት አይደሉም፤ የመጽሃፍ ቅዱሱን ትዕዛዛት የሚጋፉም አይደሉም። ከየትኛውም ሃይማኖት የማይወግኑ ህግጋት ናቸው።  እኒህ ትዕዛዘት ከደስታ ለራቀው ለዚህ ትውልድ የተጻፉ ናቸው።አሁን ከምኖረው ኑሮ በመነሳት ደስታችንን ለማግኘት የሚረዱን ትዕዛዛት ናቸው ።ሳንሰብር ሳናጣምም ከተገበርናቸው፤ ደስተኛ ለመሆን መንገዳችችንን ቀላል ያደርጉልናል….

ትዕዛዝ አንድ– እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር-ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ለፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ ይቀናሉ። አይገርምም?

ትዕዛዝ ሁለት–  አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው-የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ?ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮትቻን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

ትዕዛዝ  ሶስት- እራስህን ሁን- በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባነተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ሁን

ትዕዛዝ አራት-  ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር- አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

ትዕዛዝ አምስት- የውሸት ደስታን አትፈልግ- በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ። እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ።

ትዕዛዝ ስድስት- ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን- ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን እራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ።

ትዕዛዝ  ሰባት- መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው- ብዙ ሰውች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን  በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ።ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአለሙ ፈጣሪ ስጠው።

ትዕዛዝ  ስምንት- የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን- ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው።እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

ትዕዛዝ  ዘጠኝ-  መልካም አስብ መልካም ተናገር- በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅ፧ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

ትዕዛዝ አስር-  ለምን እንደምትኖር እወቅ- ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት።ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው?  መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት የለወጣል።

 

 

 

 

 

 

 

 

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *