“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የወርቅ እንቁላሎች

by | May 23, 2016 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 3 comments

በየጊዜው በምንጸልየው ጸሎት ውስጥ  “የእዮብን ትዕግስት ስጠኝ” የምንለው የዚህችን ምድር ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መወጣጫው ትዕግስት  ስለሆነ ነው። ትዕግስት ማለት ነገሮች በጊዜያቸው እንዲሆኑ መጠበቅ ቢሆንም፤ ከምንም በላይ ትክክለኛው ትዕግስት በጥበቃችን ወቅት የምናሳየው አመለካከት እና ጽናት ጭምር ነው። እዚህ ላይ ኤዞፕ የጻፈው አንድ ተረት ትዝ አለኝ። ተረቱ እንዲህ ነው…….

በድሮ ጊዜ አንድ ባል እና ሚስት ይኖሩ ነበር። እኒህ ባልና ሚስት አንድ ስጎን ነበረቻቸው። ይህቺ ሰጎን ታዲያ በየቀኑ የወርቅ እንቁላል ትጥል ነበር። ሰጎኗ በምትጥለው የወርቅ እንቁላልም ባልና ሚስቶቹ ባለጸጎች ሁኑ። ታዲያ አንድ ቀን ሚስትየዋ ለባሏ “ውዴ ይህቺ ሰጎን በቀን በቀን እንቁላል ትጥላለች፤ አንድ ተጨማሪ የወርቅ እንቁላል ለማግኘት አንድ ተጨማሪ ቀን መጠበቅ አለብን። እንደዛ ከምናደርግ ለምን ሰጎናን ገድለን በሆዷ ያለውን ሙሉ የወርቅ እንቁላሎች ወስደን አንገላገልም” አለችው። ባልየውም በሚስትየው አባባል ተስማምቶ  ሰጎኗን አረዷት፤ ሆዷን ከፍተው ሲመለከቱ ምንም የወርቅ እንቁላል ሊያገኙ አልቻሉም፤ አንድም እንኳን። ምክንያቱም ሰጎኗ ልክ እንደሌሎች ሰጎን ነበረች። እንቁላሉን የምትጥለው በጊዜዋ ነበር።

ሁላችንም በተለያየ የህይወታችን ገጽታ የወርቅ ሰጎኖች አሉን። በጊዜያቸው ወርቅ እየጣሉ ባለጸጋ ሊያደርጉን ሲችሉ ትዕግስት በማጣችን ብቻ ሰጎናችንን ገድለን ባዷችንን እንቀራለን። ለምሳሌ የፍቅር ግንኙነታችንን እንመለከት፤ ማንኛውም አይነት ጓደኝነት አዲስ ቀን በጨመረ ቁጥር አዲስ የፍቅር እንቁላል ይጥላል። እውነተኛ ግንኙነቶች ልክ ወርቅ እንደምትጠለዋ ሰጎን ናቸው፤ በአንድ ጊዜ በስሜት አያጥለቀልቁንም፤ በአንድ ጀንበር ጽናትና መተማመንን  አይፈጥሩም። ልክ እንደሰጎኗ ዛሬ አንድ ደስ የሚል እምነት፤ ነገ ደግሞ ሌላ እየጣሉ ልባችንን በጊዜ ብዛት በሃሴት ይሞሉታል። እኛ ግን ልክ ኤዞፕ በተረቱ እንደሳላቸው ሞኝ ባልና ሚስቶች ነን፤ ትዕግስት የለሾች።

በስራችን በኩል እንመልከተው ካልን ፤ በትክክለኛውና በእውነተኛው መንገድ ስራችን የሚጥልልንን የወርቅ እንቁላል ከማጠራቀም ይልቅ፤ ሰጎኗን አርደን በአንዴ መክበርን እንሻለን። ለዚህ ነው በስግብግብነታችን እና በትዕግስት የለሽነታችን ምክንያት ብዙ ህይወታችንን ሊለውጡ የሚችሉ ሰጎኖችንን አርደን ባዶዋችንን ቀርተናል። እኔን የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፤ በዚህች አለም ላይ እግዜር ከፈጠራቸው ፍጡሮች ሁሉ በአስተሳሰብ የላቅነው እኛው ሰዎች ሆነን ሳለ፤ ለምን ሌሎች ከሰው ያነሱ ፍጡሮች በተፈጥሮ ህግ ሲገዙ እኛ ቀላሎቹን የተፈጥሮ ህጎች  እንኳን አስተውለን ህይወታችንን መምራት አቃተን?

እስከነገ መታገስ እያቃተን ስንት ነገሮችን አበላሽተናል? ትዕግስት የለሽነታችን የሚያፈነዳቸው የንዴት ቦንቦች ስንት ለጸጸት የሚዳርጉ ውሳኔዎችን እንድንወስን አድርገውናል? የሚነጋ ስላልመሰለን በጨለማው ውስጥ ብዙ ስህተቶችን ፈጽመናል። ህይወት ነገ የምትጥልልን እንቁላል በትዕግስት መጠበቁ ስላቃተን ብቻ ህይወታችንን በአጭሩ የቀጨን  ብዙዎቻችን ነን።

ሲጀመር የጭንቀቶቻችን ሁሉ መንስዔ ትዕግስት ማጣትቻችን ነው። “ለሁሉም ጊዜ አለው” የሚለው የጠቢቡ ሰለሞንን  ንግግር ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሲናገረው ስንሰማ ተራ ነገር መሰለን እንጂ ድንቅ የህይወት መመሪያ ነው። ያለጊዜው የሚሆን ምንም ነገር የለም፤ ያለጊዜው  ቢሆን እንኳን መልካምና የተሟላ አይሆንም። ከጊዜ ጋር መሽቀዳደሙ አንዳንዴ አጉል መከፋት ላይ ይጥለናል፤ የሰው ልጅ አቅም ውስን ነውና። ህይወታችንን ወርቅ እንደምትጥለዋ ሰጎን እንቁጠራት፤ በትዕግስት ከጠበቅናት በጊዜዋ የምትጥልልን ብዙ የወርቅ እንቁላሎች አሏት። ትዕግስት አጥተን ወይም በአቋራጭ እንክበር ካልን ግን ባዷችንን መቅረታችን ነው።

በሚስጥረ አደራው

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

3 Comments

  1. Aklilu

    Hmmm—-
    Hi Mistre, This is Aklilu. some how I ran into this site. This must be the work of you. I am here in Geogia, Alpharetta, at some IT company.

    Aklilu

    Reply
  2. henok

    i would like to thank what u share a best life building process.

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *