“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

የመቀበል ሀይል- The power of Acceptance

by | Apr 25, 2018 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 7 comments

(በሚስጥረ አደራው)

ማንም ሆን ብሎ የማያስተምረን፤ ነገር ግን በህይወታችን ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ። እኒህን የኑሮ ትምህርቶች በራሳችን ግዜ አደናቅፎን እስክንወድቅ ድረስ ማንም እንዲህ ነው ብሎ ሊያሳውቀን አይችልም። ባለፉት ቀናቶች ስለ “መቀበል” ወይም “Acceptance” በእጅጉ ሳስብ ነበረ። እራስን ስለመለወጥ፤ ሁኔታዎችን ስለመቀየር፤ የጎደለንን ስለማሟላት፤ ስለነዚህ ሁሉ ከልክ በላይ ሰምተናል። ስለ “መቀበል” “Accepting what it is” ግን ያን ያህል አጽንዎት ተሰጥቶት ሲነገር አንሰማም። የእኔም የእራሴም መንገድ በለውጥ ላይ ብቻ እንጂ በመቀበል ላይ የተመሰረተ አልነበረም። ለብዙ ጊዜ ስለለውጥ እንጂ ስለመቀበል አስቤ አላውቅም ነበር። ባስብም የለውጥን ያህል ጉልበት አላወጣሁበትም።

ለውጥ ወሳኝ ነገር ነው። ሁላችንም ልንልወጣቸው የምንፈልጋቸው ብዙ ሁኔታዎች አሉ። ልናያቸው የምንፈልጋቸው ለውጦች፤ በራሳችን ህይወት አልያም ከእኛ ውጪ በሆኑ ነገሮች ሊሆን ይችላል። ልናሟላቸው የምንሻቸው ብዙ ነገሮች፤ ልንደርስባቸው የምንመኛቸው ብዙ ግቦች በእርግጠኝነት አሉ። ነገር ግን ለብዙዎቻችን ይህ የመለወጥ ህልማችን የማይሳካው፤ ቢሳካም እንኳን የማያረካው፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ መንገዱ አድካሚ የሚሆነው፤ የሚቀድመውን ነገር ባለማወቃችን ይመስለኛል። የምንለወጣቸውን ነገሮች ከመዘርዘራችን በፊት ያለንበትን ሁኔታ መቀበል ቀዳሚው ተግባር ነው። የተቃረነ ነገር ሊመስል ይችላል። ምክንያቱም ሰው ያለበትን ነገር ከተቀበለ፤ ለውጥ ለምን ይሻል? ብለን ልናስብ እንችላለን።

አሁን ያለንን ነገር መቀበል ስንችል ፤ ማለትም ያለንንም ሆነ የጣነውን፤ የሚያኮራንንም ሆነ የሚያሳፍረንን፤ የሚጸጽተንንም ሆነ የሚያስደስተንን ነገር ያለምንም ዳኝነት ስንቀበለው፤ ከእራሳችን እና ከሌሎች እንዲሁም ከሁኔታዎች ጋር የምንገጥመው ጦርነት ይበርዳል። በአብዛኛው ስለራሳችን የማንወደውና ልንለውጠው የምንፈልገው ነገር እኮ በሌሎች መስፈርት ተቀባይነት ስላጣ እንጂ እውነት ስላልፈለግነው አይደለም። ወይም ደግሞ ልንለውጣቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች ከእኛ ውጭ የሆኑ ነገሮችን ነው። ለዚህ  ነው እራሳችንን ከመቀበል፤ ካለንበት ሁኔታ ጋር ከመስማማት ኑሮን መጀመር ያለብን።

ያለንበትን ሁኔታ መቀበል ስንል፤ ስለመሸነፍ እያወራን አይደለም። ይልቁንም ስለበለጠ ድል እያወራን እንጂ። አሁን ያለንበትን ሁኔታ ስንቀበል ፤የምንፈልገው ለውጥ ሰላም ባለው መልኩ መምጣቱ አይቀርም። በትግል ሳይሆን በፍቅር ከህይወት የምንፈልገውን ነገር እናገኛለን። አንዴ የሆነ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ አንድ ሰው የተናገረው ነገር መቼም አይረሳኝም። ሰውየው አሁን ላይ ስለመኖር ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው “እንደው ከአቅም በላይ የሆነ ህመም ካልተሸከምን በቀር፤ ለብዙዎቻችን “አሁን” “The Present” ያን ያህል መጥፎ አይደለም፤ ነገር ግን ይህን ባለማወቃችን በትናንትና በነገ መካከል ስለምንዋዥቅ ይህንን መልካም ጊዜ እናጣዋለን።” ዛሬን እንዳለ መቀበል ስለማናውቅበት፤ ሁሌም የመንፈስ ትግል ውስጥ ነን።

“Always say “yes” to the present moment. What could be more futile, more insane, than to create inner resistance to what already is? what could be more insane than to oppose life itself, which is now and always now? Surrender to what is. Say “yes” to life — and see how life suddenly starts working for you rather than against you.” ~ Eckhart Tolle

በመጀመሪያ እራሳችንን ከጥሎ ያለንበትን ሁኔታ መቀበል ካልቻልን፤ ነገ የምንመኘውን ማንነትም ሆነ ሁኔታ ስናገኝ እራሳችንንም ሆነ ሁኔታውን ተቀብለን ለመደሰት አይቻለንም። ደስታ እና እርካታ በጭራሽ ግቦች አይደሉም። የብዙዎቻችን ስህተት ይህ ይመስለኛል፤ ለመደሰትና ያለንን ነገር ተቀብለን ለመርካት ብዙ ነገሮችን እስክንለውጥ እንጠብቃለን። ይህ ግን ሞኝነት ነው፤ ከዛሬ ጋር ባለንና በሆነው ነገር ካልተስማማን፤ የነገም ነገር አስተማማኝ አይሆንም። እራስንን እና ሁኔታዎችን አሁን ባሉበት ሁኔታ መቀበል ፈጽሞ ሽንፈት አይደለም። በመቀበል ውስጥ በፍቅር የተሞላ ሀይል አለ። በመቀበል ውስጥ በትግል ሳይሆን በፍቅር የሚመጣ ለውጥ አለ። ይህ ለራሳችን የምንሰጠው ፍቅር እሩቅ ያስጉዘናል፤ ምንም ሊያስቆመው የማይችል የሰላም ሀይል ስለሆነ። መቀበል ጉልበት አለው። አንዳንዴ እኮ የምንታገለው ከተፈጥሮ ከራሱ ጋር ነው።

ከምንም በላይ ግን መቀበል ወይም “Acceptance”  ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙት ሰላማዊ ያደርገዋል። ከራሳችንን ጋር መስማማታችን ከሌሎችም ሰዎች ጋር ያስማማናል። ሁላችንም በየራሳችን እውነት የምንመራ ነን፤ ሌሎች በእኛ መነጽር ነገሮችን እንዲያዩ እንፈልጋለን። የሌሎችን አስተሳሰብና አኗኗር ለመለውጥ ትግል ውስጥ እንገባለን። እኛ በራሳችን ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለን በሌሎች ስዎች ህይወት ውስጥ ያንን ተቀባይነት ለማግኘት ሰማይ እንቧጥጣለን፤ ይህን ነው ዘወትር እረፍት የሚነሳን። እራሳችንን በመቀበልና ለራሳችን ያለንን ፍቅር በመኮትኮት የሌሎች ሰዎች የሃሳብ ልዩነት ወይም የሁኔታዎች እኛ እንደፈለግናቸው አለመሆን ያን ያህል የማይረብሸን ደረጃ ላይ እንደርሳለን። ከሁሉም በላይ ግን ከኑሮ ጋር የምንገጥመው ጦርነት ይበርድና ከእራሳችንም ሆነ ካለንበት ሁኔታ ጋር እቅር እናወርዳለን።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

7 Comments

  1. afework

    Yes i agree with you, we shall to have the habit to say”THIS IS IT.”in Amharic” ይኸው ነው::”

    Reply
  2. Bereket

    ኑሪልን አቦ

    Reply
  3. Hirsi bashikr

    Astemariye Mistire aderaw thank you a lot

    Reply
  4. Hirsi bashiir

    Astemariye mistera aderaw. Thank you a lot

    Reply
  5. ANTIPAS OjO

    yene dekama gone meslo new yetesemagn alemekebel txs a lot

    Reply
  6. Habure

    Thank very much!

    Reply
  7. Jemaledin Muzeyin

    mistir, I hear about your site from henok ( one of your regular reader) What you said in a very eloquent way about living in the present moment is true.but, it is one sided only. We all should live in the present moment I couldn’t agree with you more, but how, with all that involuntary chatter, commentary, judgment about this and that. How could one live in the present moment. I once heard Dr.joe dispense bluntly saying, “an average individual experience more than 75,000 thought per day” that is an average it could get higher and I never heard of anyone who found the switch off button for this negative, repetitive and worthless mental chatter. Sadhguru refer it as a Mental Diarrhea so, if anything turn up for the how I look forward to it. so many thanks and keep it up.

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *