“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ዘሩ ብቅ አላለም ብለህ ውሃ ማጠጣቱን አታቁም

by | Apr 3, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

አንዳንዴ ለፍተን ለፍተን ምንም ነገር ጠብ ሳይል ሲቀር ተስፋ መቁረጥ፤ ከተፍ ማልቱ አይቀርም። የምንለፋው ለምንድን ነው? ያሰኘናል። የምጓዘው ጨለማ መቼ ነው የሚነጋው? የልፋቴን ዋጋ መቼ ነው የማገኘው? እያላችሁ ከሆነ ፤ ምላሽ የምታገኙበትን አንድ ድንቅ ታሪክ ላካፍላችሁ። እኔ በግሌ የምጠቀምበት ዘዴ ነው። አንድ ነገር ሞክሬ ለማቋረጥ ሳስብ ይህንን ታሪክ ምልሼ ለራሴ እነግረዋለው።

የቻይና ባምቡ ዛፍ አስተዳደጉ ከሌሎች ዛፎች በጣም ይለያል። ሌሎች ዛፎች ከተተከሉ ጀምሮ ማቆጥቆጥ ሲጀምሩ፤ ይህ የቻይና ባምቡ ዛፍ ግን፤ በቀን በቀን ውሃ ቢጠጣም እስከ አምስተኛው አመት ድረስ አፈሩን በርቅሶ አይወጣም። ያለማቋረጥ እለት ተእለት ውሃ መጠጣት አለበት፤ ነገር ግን አራት አመት ሙሉ ምንም አይነት እድገት አያሳይም። በአምስተኛው አመት ግን በአምስት ሳምንት ወስጥ በአንዴ 90 ፊት ውይም 27 ሜትር ያድጋል። ታዲያ ይህ ዛፍ በአምስት ሳምንት ውስጥ ነው ያደገው? ወይስ በአምስት አመት?

መልሱ በአምስት አመት ነው። ጽናት የሌለው ሰው ግን ቶሎ ብቅ ለማይል ዘር አምስት አመት ሙሉ ውሃ ማጠጣቱ አይዋጥለትም እናም ዛፉን በእንⶽጩ ይቀጨዋል። የእኛም ነገር እንዲህ ነው፤ ሃሳባችን ግቡን ባሰብነው ሰዓት ካልመታ፤ አላማችን በአቀድነው ቀን ካለተሳካ፤ ምኞታችን በእለቱ እውን ካልሆነ፤ የማይሳካ ይመስለናል። ለዚህ ነው ብዙዎቻችን ጉዞዋችንን የምናቋርጠው።

የእውነት አላማ በውስጥህ ካለ፤ ውሃ ማጠጣትክን እንዳትተው። ዛሬ ባይሳካ በጊዜው መሳካቱ አይቀርም። አንባቢ ባታገኝም መጻህፍህን አትተው፤ የሚጎበኝልህ ብታጣም መሳልህን አትተው፤ የሚሰማህ ብታጣም መዝፈንህን አታቋርጥ፤ አይዞህ የሚልህ ባታገኝ መማርህን አታቁም። የብዙዏቻችን አላማ ልክ እንደ ቻይናው ባምቡ ዛፍ ነው፤ ሳናቋርጥ ውሃ ካጠጣነው እና ትዕግስት ካለን፤ ማቆጥቆጡ ብሎም ማደጉ አይቀርም። ለሁሉም ጊዜ አለው ይል የለ መጽሃፉ………በጊዜው የተከልነው ችግኝ ሰማይ ማከሉ አይቀርም፤ እስከዛ ግን ማድረግ የሚገባህን ከማድረግ አትቆጠብ፤ ነፍስህ በቀን በቀን ውሃ አጠጣት።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *