“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ውስጣዊ ሰላም

by | Mar 1, 2016 | መነቃቂያ inspiring stories | 1 comment

“what is this inner strength that enables one to maintain calm in the face of difficulties? It is not the result of external factors,medicines, injections, drugs or alcohol. Nor some kind of external blessing. Inner strenghth stems from true training of he mind.”- living a Better way, Dalai Lama

አንዳንዴ ሰዎች ለሸክም በሚከብድ ችግር  ውስጥ ሰላምን ሲያገኙ፤ በህመም ውስጥ ደስታን ሲያጣጥሙ፤ በመከራ ወቅት ብርታትና ተስፋን ከጎናቸው አድርገው ሲጓዙ ስናይ ሚስጥሩ ምን ይሆን ብለን እራሳችንን የጠየቅንባቸው ወቅቶች እርግጠኛ ነኝ ጥቂቶች አይደሉም። ቀና ማሰብ በማይቻልባቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው አሉታዊነት የማይታይባቸው ሰዎች እውነት በዙሪያቸው የሚያንዣብበው አሉታዊ ስሜት አልጫናቸው ብሎ ነው?  ወይስ ስሜታቸው በቀላሉ የማይነካ ጠንካሮች ሆነው ነው?

መልሱ ውስጣዊ ሰላም ስላላቸው ስላላቸው የሚል ይሆናል።

ውስጣዊ ሰላም ወይም የአይምሮ እርጋታ የምንለው ምንድን ነው? ውስጣዊ ሰላም ስንል በዙሪያችን የሚከሰቱ ነገሮች ጭራሽ አይረብሹንም ማለት ነው?

እውቁ ጸሃፊ ዋየን ዳየር “እርግጥ ነው ትናንት ብለን የምንጠራው ህይወት አለን፤ ነገ ብለን የምንጠራውም ህይወት አለን፤ ስለትናንት እና ስለነገ የሚያስብ አይምሮ ዛሬን በቅጡ አይኖርም። ያ ደግሞ ውስጣዊ ሰላማችንን ይነጥቀናል” ሲል በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። ውስጣዊ ሰላም በሁለት ዋና የህይወት መርህዎች ላይ የተመሰረተ ነው። አንደኛው ዛሬን መኖር የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ነገሮችን መቀበል የሚል ነው።

ዛሬ ላይ መኖር ትልቅ የአይምሮ ልምምድን የሚጠይቅ የአኗኗር ስልት ነው። ብዙዎቻችን ገና ከትናንት ጎዳና አልወጣንም አልያም የነገ ተራ ላይ ተሰልፈናል። ምንም እንኳን ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ጥልቅ ጣዕም ቢኖራቸውም የዛሬን ያህል ውበት እና ሰላም ግን ፈጽሞ ሊኖራቸው አይችልም። የህይወትን ጣዕም ከሚሰርቁ ነገሮች ዋነኛው ፍርሃት ነው። ፍርሃት ወይ በትናንት አልያም በነገ ጉያ  ብቻ የሚሸሸግ በዛሬ ውስጥ መኖር የማይችል የውሸት ስሜት ነው። የመኖር ፍርሃት፤ የመውደድ ፍርሃት፤ የመለወጥ ፍርሃት፤ የስኬት ፍርሃት፤ እኒህ ሁሉ አልያም በትናንት የኑሮ ተሞኩሮዎች ወይም በገና ለገና የነገ መላምቶች የሚፈበረኩ ውሸቶች ናቸው።

ዚግ ዚግለር ፍርሃትን እጅግ ውብ በሆነ አገላለጽ እንዲህ ይገልጸዋል ” FEAR- is FALSE EVIDENCE APPEARING REAL” ፍርሃት ሁሌም እውነት ያልሆኑ ነገሮችን እውነት አስመስሎ የማቅረብ ችሎታ አለው። ፍርሃት ማለት ገና እውን ያልሆኑ ነገሮችን ቢሆኑስ እያልን በአይምሮዋችን ውስጥ መሳል ስንጀምር የሚፈጠር መጥፎ ስሜት ነው። ከዚህ በላይ ውስጣዊ ሰላምን የሚነጥቅ ምን ነገር አለ?

ለዚህ ነው ከላይ እንዳነሳሁት አንዳንዶች ምንም እንኳን በአስቸጋሪ የህይወት ጎዳና ላይ ቢሆኑም አይምሮዋቸው እንደፈለገው እንዲጋልብ አይፈቅዱለትም። በእያንዳንዱ እርምጃ የሚገጥማቸውን እንጂ ገና መታጠፊያው ጋር ሲደርሱ ሊገጥማቸው የሚችለውን ነገር እያሰቡ አይብረከረኩም። ውስጣዊ ሰላም በዙሪያችን ካሉ ነገሮች ጋር ግንኙነት እንደሌለው የብዙ ሰዎች ህይወት ተሞክሮ ያረጋግጥልናል። ሃብት፤ ዝና፤ ክብር ኖሮዋቸው ሰላም የሚናፍቃቸው ብዙ ሰዎች ሞልተዋል። በአንጻሩ ምንም እንኳን ውጫዊ ነገሮቻቸው ባያምሩም የሰላማቸው ብርጭቆ እስከአፉ የሞላ ሰዎችን ደግሞ ስናይ፤ ሰላም መገኛዋ የት ነው ያሰኛል?

የሰላም እና የደስታ ምንጩ አይምሮዋችን ነው። መፍለቂያው የምንኖረው መልካም ህይወት ነው። ውስጣዊ ሰላም እለት ተዕለት ህሊናችንን በማጽዳት፤ አይምሮዋችንን በማለማመድ ልናገኘው የምንችለው ሃብት፤ ልንጎናጸፈው የሚቻለን ጸጋ ነው። በትናንት ውስጥ የታጨቁ ብዙ ቁጭቶች፤ ብዙ ቂሞች ፤ ብዙ ጸጸቶች፤ ብዙ ውድቀቶች አሉ። በነገ ውስጥ ደግሞ ብዙ ፍርሃቶች፤ ብዙ ጥርጣሪዎች፤ ብዙ በቀሎች አሉ።  እኒህን ሁሉ ከላያችን ማራገፍ ካልቻልን ውስጣዊ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ አይቻለንም።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. solomon

    ደስ የሚል ነው !!!

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *