“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ከአፍ የወጣ……..

by | Aug 30, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 4 comments

በቀን ምን ያህል ክፉ ንግግሮችን እንናገር ይሆን? ምን ያህል መልካም ያልሆኑ ሃሳቦች አይምሮዋችንን  ሽው ይሉት ይሆን? መቼም አሁን በተያያዝነው የአኗኗዋር ዘይቤ……አስተሳሰባችን፤አነጋገረራችን፤አስተያየታችን ግራውን መከተሉን ለምዷል።ከራሳችን፤ከቤተሰቦቻችን፤ከጓደኞቻችን ጋር የምንጋጭበት ጊዜ ብዙ ነው።ከህጉ ጋር፤ከማህበረሰቡ ጋር፤ከእምነቱ ጋር የምንላተምበት አጋጣሚዎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።አኗኗራችን  አስተሳሰባችንን ጠምዝዞት፤የተጣመመ ባህሪያችንን እንዳንመለከተው አድርጎናል።መልካም ንግግር፤ከዘመናዊነት የራቀ ባህሪ እየመሰለን፤ቃላቶቻችን ቅርፃቸውን ለውጠዋል።ይህንን ሁሉ ያስባለኝ፤ስለክፉ ንግግር የተፃፈች አንዲት ድንቅ ታሪክ አስታውሼ ነው……እነሆ

አንድ አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት ልጅ ነበረው።ይህ ወጣት በትንሹም በትልቁም ቱግ እያለ፤ሰዎችን ያስቀይም ነበር።ከአንደበቱ ክፉ ቃላቶችን ስለሚያወጣ ከሰው ጋር መስማማት አልቻለም።ትዕግስት ፈፅሞ  የለውም።ይህ ነገር እጅግ ያሳሰበው አባት፤ልጁን የሚለውጥበት ዘዴ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ አንድ መፍትሄ ላይ ደረሰ።አንድ ቀንም በቀረጢት ሙሉ ሚስማር ያዘና ልጁን አስጠርቶ እንዲህ አለው

“ልጄ ሆይ …ይህን በቀረጢት ያለውን ሚስማር ተቀበለኝ፤ሁሌም ትዕግስት በጎደለህ ጊዜ እና ሰው ባስቀየምክ ቁጥር አንድ ሚስማር የእንጨቱ  አጥር ላይ ሰካ” አለው።ልጁ ምንም ግራ ቢገባውም አባቱ እንዳዘዘው ማድረግ ጀመረ።በመጀመሪያ ሰሞን በጣም ብዙ ሚስማሮችን ሰካ….ቀስ እያለ ግን በቀን እንጨቱ ላይ የሚሰካቸው ሚስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ…. እያለ…እያለ….በመጨረሻ ምንም ክፉ ያልተናገረ ቀን አንድም ሚስማር ሳይሰካ ዋለ።ልጁ በጣም ታጋሽ ሆኖ ባህሪው ተስተካከለ ማለት ነው።ይህንንም ለአባቱ አበሰረ።

አባትየውም  “ እሰይ ልጄ……አሁን ደግሞ ምንም ያልተናደድክ ቀን እና ክፉ ያልወጣህ ቀን በፊት ከሰካሃቸው ሚስማሮች ውስጥ አንዱን ንቀል” አሉት።ልጁ እንደተባለው አደረገ፤ከቀናት በኋላ ሁሉንም ሚስማሮች ነቅሎ ጨረሰ።ወደ አባቱም ሄዶ ሚስማሮችን አስረከበ።አባትየውም አንዲህ አለው

“አየህ ልጄ……አሁን የሰካሃቸውን ሚስማሮች ነቅለህ ጨርሰሃል…..በጣም ታጋሽ ሆነሃል ማለት ነው፤ነገር ግን እስቲ አጥሩን ተመለክት….ፈጽሞ እንደ ድሮው ሊሆን አይችልም፤ሚስማሩ ቢወጣም ተበሳስቷል።ክፉ ንግግርም ልክ እንደ ሚስማር ነው፤ሺህ ጊዜ ይቅር ብትልም፤እንደሚስማሩ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ፤እናም ልጄ……..በህይወት ትዕግስት ይኑርህ…..አንደበትህን ቆጥብ” ብሎ አስተማረው።

አንደበት ይገራል፤አንደበትን የሚገራው መልካም አስተሳሰብ ነው።በክፉ ንግግር ፤በጭቅጭቅ፤በስድብ እስከዛሬ ምን መልካም ነገሮች ሲፈጠሩ አየን? ስህተቶቻችን እየጎለጎልን በመነካከስ ምን ልዩነቶችን አጠበብን?………”ቃላት” ለሰው ልጅ ኑሮ የእስትንፋስ ያህል ዋጋ አለው።በቃላት ጦርነት ይነሳል፤በቃላት ሰላም ይሰፍናል…….

እስቲ ለጥቂት ቀናት እራሳችንን እንፈትነው…….መልካም መልካሙን በመናገር

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

4 Comments

  1. Mulualem

    መልካም ማሰብ፣መልካም መናገር ትርፉ ለራስ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡

    Reply
  2. fikre

    betam enamesegnalen astemari new ketlubet

    Reply
  3. Yotor

    Very interesting. Thank you!

    Reply
  4. Tariku(tare)

    words……….ohhh…realy great.
    we thank u Mistre.

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *