“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

እንዳትወጣ የሚጎትቱህ ብዙዎች ናቸው!

by | Nov 27, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 0 comments

ምቀኝነት አይደለም፤ ምቀኝነት የሚመስል ግን ካለማወቅ የሚመጣ ባህሪ ነው። አንዳንዴ እራሳችንን ለመለወጥ እናስብና ሌሎችን ማሳመኑ ዳገት ይሆንብናል። ከሱሰኝነት ለመላቀቅ ብንወስን፤ ሱስ ውስጥ የተዘፈቁትን ጓደኞቻችን ጥለን መሄዱ ይከብደናል፤ እኛ ብንለውጥ ጓደኝነታችን ይቀራል ብለን ስለምናስብ። እረጅም አመታትን በሌብነት የኖረ ሰው ስራው ጸጽቶት ቢለውጥ እንኳ፤ ማህበረሰቡ አያስለውጠውም። ሁሌም እንደሌባ ስለሚታይ፤ አለመታመኑ ለመለወጥ ካደረገው ትግል በላይ ይከብደዋል። ሱስን እና ሌብነትን እንደምሳሌ ወሰድኩኝ እንጂ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ውስጥ ብንሆንም፤ እራሳችንን እንዳንለውጥ የሌሎች ተጽዕኖ ከባድ ነው።

የሚገርመው ደግሞ እራስን ለመለወጥ ሲታሰብ ትልልቆቹ እንቅፋቶች የምንቀርባቸው ስዎች መሆናቸው ነው። ምቀኝነት አይደለም፤ ዋና ምክንያታቸው የለመዱትን ማንነታችንን ማጣት ስለማይፈልጉ ነው ። “ምነው እንደድሮህ አይደለህም?” እያሉ ለውጣችን ስህተት እስኪመስለን ደረስ ይሞግቱናል። ለምሳሌ ሁሌም አብረሃቸው የማይረባ ነገር እየሰራህ ጊዜህን ስታባክን የሚያውቁህ የቅርብ ጓደኞችህ፤ የጊዜን ዋጋ አውቀህ ጊዜህን በአግባቡ መጠቀም ስትጀምር “ምነው ተለውጥክ፤ በጣም ኮራህ፤ እንደድሮ አይደለህም” በማለት ለውጥህ ስህተት እንደሆነ ይነግሩሃል። እንዳልኳችሁ ምቀኝነት አይመስለኝም፤ አዲሱን ማንነትህን ለመቀበል ስለከበዳቸው ብቻ ነው።

ማርከስ ጋርቬይ ለጥቁሮች ነጻነት ሲታገል ከነጮች በላይ ጥቁሮችን ማሳመን እዳ ሆኖበት ነበር። የምነቀርባቸው እና የምናውቃቸው ሰዎች ሁሌም ለለውጣችን እንቅፋቶች መሆናቸው አይቀርም፤ አውቀው በክፋት የኛን መልካም ነገር ላለማየት ብለው ሳይሆን፤ ስንለወጥ የለመዱትን ማንነታችንን እንደሚያጡት በመስጋት አልያም ለኛ የተሻለው ነገር እነሱ የሚያስቡት ነገር ስለሚመስላቸው ነው። ይህንን የሚያስረዳ ድንቅ አባባል ከማከስ ጋርቬ መጽሃፍ ላይ ቀንጠብ አድርጌያለው።
“we are like crabs in a barrel. That none would allow the other to climb over, but on any such attempt all would continue to pull back into the barrel the one crab that would make the effort to climb out”
“እኛ ማለት በጎድጓዳ ገንዳ ውስጥ እንዳለን ነፍሳቶች ነን፤ ማናችንም ሌላው ከገንዳው እንዲወጣ አንፈልግም፤ እንደው ጥሮ ግሮ እራሱን ከገንዳው ለማውጣት የሞከረ ካለም፤ ከጫፍ ሲደርስ ሌላው ተባብሮ ወደታችን ይጎትተዋል”

እውነት ነው፤ እኔ በበኩሌ ገንዳውን እንደህይወት ልምድ ወይም ባህሪ እወስደዋለው። ብዙ ሰዎች በድሮ ባህይሪያችን ወይም ልምዳችን ለምደውናል፤ እራሳችንን ለማሻሻል ከገንዳው ለመውጣት ስንታገል ይጎትቱናል። እንዳልኳችሁ እኔ በምቀኝነት አይመስለኝም ባለማወቅ እንጂ። ውሳኔው እንግዲህ እዚህ ላይ፤ ነጻነትህን የሚሰጥህ የመረጥከውን ጎዳና የሚቀበልልህ ካለ እሰየው፤ ሊያስቆሙህ የሚሞክሩት ግን ያንተ ለውጥ ስህተት ሆኖ ሳይሆን (መልካም ለውጥ እስከሆነ ድረስ) የነሱን መንገድ መከተል ስላቆምክ ነውና አያሳስብህ።

ጓደኛ እና ቤተሰብ መስዋት ሊከፈልላቸው የሚገቡ ነገሮች እንደሆኑ አምናለው፤ ነገር ግን የአላማችን እንቅፋት እንዲሆኑ መፍቀድ የለብንም። ስንት ስኬታማ ሰዎች ናቸው በስተመጨረሻ ሲመሰክሩ “ቤተሰቦቼ እንድሆን የሚፈልጉት ነገር ሌላ ነበር፤ ከቤተሰብ እና ወዳጅ ደጋፍ አላገኘሁም” ብለው የሚመሰክሩት። በእርግጠኝነት አላማናችንን የማይደግፉት ብዙዎች ናቸው፤ በተለይ የምናውቃቸው እና የምንቀርባቸው ሰዎች። ነገር ግን አላማችን እውን ከሆነና ስሩን ከሰደደ ማን ሊያቆመን ይችላል? ሌሎች እንዲወዱን ብቻ ብለን የማንፈልገውን ኑሮ መኖር የለብንም!!!

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *