“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

 አጅሬ ገለባ…….

by | May 11, 2015 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 1 comment

ታላቁ የቻይና ሊቅ ላዎ ቱዝ፤ ዘ ዳዎ በተባለው መጽሃፉ ላይ፤ ምዕራፍ ስምንት እንዲህ በሚያምር ሁኔታ ቀርቧል።

“Water exemplifies the excellence of the way; it benefits all beings whilce being content with low places; because it is content with the low places, itcan be carried into heaven. Aware beings do not try to take advantage of the others; they live close to the ground; theur thoughts are deep; their confrontations are selfless; their speech is sincere; their leadership is without manipulation; their work is effortless”

አለምን ሁሉ ዝቅ ብሎ እንደሚያገለግለው እንደ ውሃ ሁኑ ሲል ጸሃፊው፤ ከፍ ለማለት ስትሞክሩ የሰውነት ተፈጥሯችሁን እንዳታጡ ማለቱ ነው። እንደው ብናስተውለው እኮ፤ ብዙ ነገሮች ከተራራ ወርደው ዝቅ ወዳለው ስፍራ ይወርዳሉ እንጂ፤ ከፍ ወዳለው ነገር መቼ ይወጣሉና። ዝቅ ብለን መኖር ብንለምድ፤ ህይወት ልፋት አትሆንም፤ ሁሉም ነገር ዝቅ ወዳለው ቦታ ያለልፋት ሰተት ብሎ ይወርዳል፤ ይህ የተፈጥሮ ህግ ነውና።

ምዕራፉ ሌላም የሚያትተው ነገር አለ፤ ምሉዕ የሆኑ ከተፈጥሯቸው ጋር የተዋሃዱ ሰዎች፤ እራስ ወዳዶች አይደሉም፤ ወደ መሬቱ ዝቅ ብለው ለሌሎች ይኖራሉ እንጂ። ሙግታቸው ከራስ ወዳድነት የነጻ፤ ንግግራቸው ስርዓት የተሞላበት፤ መሪነታቸው ከብዝበዛ የጸዳ፤ስራቸው ልፋትን የማይጠይቅ፤ እድለኞች ናቸው።

የጭንቀታችን ሁሉ መንስኤ፤ እራሳችንን ከተፈጥሮ  ህግ ማራቃችን ነው። ከልጅነታችን እስከ አሁን በማወቅም ባለማወቅም ያካበትናቸው አስተሳሰቦች  ከእውነተኛ ተፈጥሮዋችን ለያይተውናል። የሰው ልጅ ኑሮ የከበደው፤ ሰው ስለሆነ ሳይሆን፤ ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር እጅግ ሰለተራራቀ ነው።

እራሳችንን ከፍ ከፍ ስናደርግ ነገሮችን ወደራሳችን መሳብ ይከብደናል፤ ብዙ ነገሮች ያለልፋት የሚወርዱት ዝቅ ወዳለው ስፍራ ነውና፤ ዝቅ ብለን በመኖር ህይወታችንን እናቅልለው።

“ከፍ ከፍ ያለው በማዶ ሜዳ

አጅሬ ገለባ እዩት ሲጎዳ” አለ አብዱ ኪያር……ዘፈኑን ተጋበዙልኝ!!!flowing-river

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. Tariku

    liked…….Mistre

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *