“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ኑሮ እና ዋና

by | Sep 17, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

መዋኘት የሚችል ሰው በውሃ ላይ የመንሳፈፍ ጥበቡን በደንብ ያውቀዋል። ውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ጠንካራ መሆንን አይጠይቅም። ይልቅ ውሃ ደግ ሆኖ ከመስመጥ የሚታደገን ፈታ ብለን ስንጫወትለት ብቻ ነው። ውሃ ግትር ሰው አይወድም፤ እጅ እና እግሩን ከማያፍታታ ግትር ጋር ውሃ ልጫወት አይልም። በጉልበት እንሳፈፋለው ለሚል ሰውም ውሃ እርህራሄ የለውም።እኔ በግሌ ውሃ ላይ እምብዛም ድፍረት አለነበረኝም። ዋናን ከልጅነቴ ስላልተማርኩት፤ ካደግኩኝ በኋላ መማሩ አስፈርቶኝ፤ ለረጅም ጊዜ አቆይቼው ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ፍራቻዬን ወደዳር አድርጌ ከወሃ ጋር በጥቂቱም ቢሆን ለመስማማት ችያለው። እናም ወሃ ሳይ ሁሌም ትዝ የሚለኝን አባባል ላካፍላችሁ ወደድኩኝ…..

አለን ዋትስ የተባለ አንድ ምሁር በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ሰምቸው ነበር ” እምነት ልክ እንደዋና ነው። ዋናተኛ ከውሃው ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለገ፤ እጁን ዘርጋ አድርጎ በነጻነት በውሃው ላይ ይወራጫል እንጂ፤ ላለመስመጥ ሲል ዉሃውን ልጨብጥ አይልም። ውሃውን ልጨብጥ ብሎ ግትር የሚል ሰው እጣ ፋንታው መስመጥ ብቻ ነው፤ በውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ምንም ነገር መጨበጥ የለብንም ፤ ዋና መዋኘት እና ህይወትን መኖር በጣም ተመሳሳይነት አላቸው”

“To have faith is to trust yourself to the water. When you swim you don’t grab hold of the water, because if you do you will sink and drown. Instead you relax, and float”.-Alan Watts

እናም ሁል ግዜ ውሃ ሳይ ትዝ የሚለኝ ይህ አባባል ሆነ። ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። እርግጥም ኑሮ እንደዋና ፈታ ብለው የሚኖሩት ባህር ነው። ግትር መሆን ውሃውን ለመጨበጥ እንደመሞከር ይሆናል። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። በኑሮ ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው።

 

አንድ ዋናተኛ ከሆዱ እየተሳበ እጅ እና እግሩን እያወራጨ ወደፊት ካልሄደም የመስመጥ እድሉ ሰፊ ነው። ኑሮም ላይ እንደዛው ትላንት ከቆምንበት ቦታ ካልተንቀሳቀስን፤ ውሃ ላይ እንደመቆም ይከብደናል። የሚገርመው የህይወት ሚስጢር በየተፈጥሮ ገንባር ላይ ተጽፎ መገኘቱ ነው፤ እርግጥ ነው ሶስተኛ አይን ኖሮት ላስተዋለው ሰው ብቻ የሚገለጥ ሚስጢር ነው።

ሌላው ብዙዏቻችን የሚያሰምጠን ዋነኛው ምክንያት ለለውጥ ያለን አመለካከት ነው። አሁንም ከግትረነት ጋር የተያያዘ ነው። ለውጥ ምንም አይነት ይሁን ማስፈራቱ አይቀርም። ከማላውቀው መላዕክ የማላውቀው ሰይጣን ይሻላል አይነት ነገር ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ዋናተኛው በእምነት ፈታ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም። #relax #beflexibleእምነታችንን አስቀድመን ፤ ከጭንቀት ተላቀን፤ ከጠባብ አስተሳሰብ ወጥተን፤ ከጊዜው ጋር መለዋወጡን ልምድ አድርገን መኖር ከቻለን በቀላሉ ለመንሳፈፍ ይቻለናል።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *