“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

በምክንያት አትታሰር!!!

by | Feb 27, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ለውድቅታችን ብዙ ምክንያቶችን መስጥት ለምድናል። ወደ ሁላ ለቀረንበት፤ የፈለግነውን ሳይሆን ያልፍለግነውን ለመሆናችን፤ ምክንያቱን ብንጠይቅ፤ እጅግ ብዙ ነገሮችን ለመደርደር እንችላለን። ግን ሁሌም ምክንያቶች በኖሩን ቁጥር፤ ውድቀታችንን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ማለት ነው ፤ እንደዛ ማለት ብቻም ሳይሆን ለወደፊቱ ውድቀታችንም ዝግጁ ያደርገናል

ህልም ካለህ እና ህልምህ ለህይውትህ ትልቅ ትርጉም ካለው፤ ከባዶ ማንነት ወጥትህ፤ ትርጉም ያለው ማንነት እዲኖርህ ከፈለግክ ምክንያት መስጠትህን አቁም። ሁላችንም ለውደቀታችን ማስተባበያ የሚሆን ብዙ ምክንያቶችን ማቅረብ እንችላለን…..በገዛ ህይወታችን ሃላፊነት ስለሚጎድለን፤ እራሳችንን እንዳንለውጥ ምክንያቶቻችን አስረው ይይዙናል …

ስኬታማ ሰዎች ግን ለውድቀታቸው ምክንያትን መስጥት የማይወዱ ሰዎች ናቸው። ስኬታማ ስል ገንዘብን ወይም የሃብት ክምችትን ብቻ እንደ ስኬት መለኪያ ቆጠሬው አይድለም። ስኬት በራሳችን መመዘኛ የሚለካ ነው።አንድ የሚያስማማን ነገር ግን ስኬታማ ሰዎች፤ የመረጡትን ኑሮ መኖር የቻሉ ናቸው። ልባቸው የወደደውን፤ ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጠውን መንገድ የተከተሉ፤ ብርሃናቸው ከራሳቸው አልፎ ለሰው የሚያብራ ሰዎች ናቸው::

በዘልማድ ኑሮ ውስጥ ተዘፍቀን፤ ማህበረሰቡ ባወጣልን መስፍርት፤ አካባቢያችን ባሰመረልን መስመር፤ ችሎታችንን ገድበን እስከመቼ እንኖራለን? ህልሞቻችንን ሌሎች ማየት ስለተሳናቸው ብቻ ቅዠት እየመሰለን፤ እውን የሚሆኑ ብዙ ህልሞችን እስከመቼ እናጨልማለን? አላማችንን እደራሳችን አድርጎ የሚመለከትልን ሰው ስላጣን፤ አላማችንን በተስፋ መቁረጥ ጉድጋድ ውስጥ ቆፍረን ቀበርነው። ችሎታችንን ሰው እንዲነግረን ስንጠብቅ፤ አቅም እና ችሎንታችንን፤ እንደቅጠል ጠወለጉብን::

እራሳችንን የሚመስል ከሰው መሃል ፈልገን ስላጣን፤ ሰውን ለመምስል ሙግት ጀመርን። ሌሎችን መሰለን ተራ ሆንን፤ ስራችን የሌላውን መስሎ ተራ ሆነ። መመሳሰል ህይወታችንን የሚያቀልን መሰልንና፤ እኛንታችንን እረስተን ተመሳሰልን፤ ያኔ ልዩነታችን ሞተ፤ ከልዩነታችን ጋር እኛነታችን አብሮ ሞተ፤ ከኛነታችን ጋር ህልማች ሞተ። የገዛ ውበታችን ጠፋ ምክንያቱም ውበት በልዩነት ውስጥ ይሚንጸባረቅ ነበርና::

ስንቶቻችን የምንወደውን ስራ አየሰራን ነው? ትርጉም የሚሰጠን ኑሮ፤ ለመኖር ምክንያት የሚሆን እሴት ያለን ስንቶቻችን ነን? አብዛኛዎቻችን ችግራችንን ለምደነዋል፤ ውድቀታችንን ተቅብለነዋል፤ ስለምንኖረው ኑሮ ምንም አይነት ነገር የማድረግ አቅም የሌለን ይመስለናል፤ ህይወታችንን የሚለውጥ ሰው ወይም አጋጣሚ እስኪመጣ እንጠብቃለን፤ በዛ መሃል ውስጣችን ቀስ በቀስ ይሞታል።

ብዙዎች የሚያውቁት ጥቂቶች ግን ይሚኖሩበት እውነታ ግን ይህ ነው።
ለህይወትህ ሃላፊነት ከወሰድክ እና መሆን የምትፈልገውን ከወሰንክ በዚህ ምድር ላይ ካንተ በቀር ከጉዞህ የሚያስቀርህ ማንም የለም። እርግጥ ነው መንገድህ ሁሉ አልጋ በአልጋ አይሆንልህም፤ ብዙ ችግር ያጋጥምሃል ምክንያቱም የስኬት መንገድ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ይሳካለት ነበር። ግን ከባድ ነው…….መንገድህ ሊያቀልልህ የሚችለው አንድ ሚስጥር አለ እሱም ህይውትህን ለመቀየር ምን ያህል ትፈልጋለህ?

ናፖሊዮን ሂል አንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችለውን ሚስጢር እንዲህ ይናግረዋል “ሰዎች አሸናፊ እንዲሆኑ ሊኖራቸው የሚገባ ባህሪ አለ እሱም ፤ የሚፈልጉትን ነገር በእርግጠኝነት ማወቅ፤ መወሰን እና ውሳኒያቸውን በተግባር ለማዋል የሚያስችላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ማዳበር።” እኒህ ሶስት ነግሮች አንድ ላይ ሲዋሃዱ ህይወታችንን ወደፈለግንበት አቅጣጫ እንድንመራ የሚያስችለንን መሪ ጨበጥን ማለት ነው።

ብዙዎቻችን በህይወታችን የምንፈልገውን ነገር አናውቅም፤ ብናውቅ እንካን መወሰኑ ይክብድናል። ለምን?ለመለወጥ ስለምንይፈራ? ዛሬ ያለንበትን ቦታ ስለለመድነውና መጪውን ስለማናውቅ?ሌሎች አይሳካም አይሆንም ስላሉን? አቅማችንን ማንም ነግሮን ስለማያውቅ? ወይስ ውድቀትን ፈርተን? ሁላችንም ምክንያቶች አሉን፤ እኒህ ምክንያቶች ድግሞ ባለንበት ቦታ እንድቀር የሚቸነክሩን ሚስማሮች ናቸው። ለውድቀትህ ምክንያት እስከሰጠህ ድረስ……ካሰብክበት አትደርስም ምክንያቱም ፤ የመለወጥ ፍርሃትህ ሌላ ምክንያት መፍጥር አያቆምምና።

ከዚህ አለም ስትሄድ በምን መታወስ ትፈልጋለህ? ዳግም በማታገኛት አንዴ በተሰጠችህ በዚህች አጭር ህይወት ምን ማድረግን ትመርጣለህ? መለውጥ የምትፈልገው ምንድን ነው? የምትፈልገውን እና የሚያስደስትህን ስራ መስራት?መልካም ቤተሰብ መመስረት? መማር? ከሱስ መላቀቅ? የጀመርከውን ስራ መጨረስ? ለምትወዳቸው ሰዎች መኖር? ወይስ ምን?
የራስህን ህልም መኖር ካቃተህ የሌላውን ሰው ህልም እውን ለማድረግ ስትለፋ እንደምትኖር እመን፤ አይ የራሴን ህልም ማሳካቱን እመርጣለው ካልክ ደግሞ፤ ሶስቱን ነገሮች አስታውስ፤
-የምትፈልገውን ነገር እወቅ
-ወስን
-ለመለወጥ ፍላጎት ይኑርህ። ከምንም በላይ ምክንያት መስጠትህን አቁም። ሁሉም ስዎች ትልቅ እንዳይሆኑ እንቅፋት ሊሆኑባቸው የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሏቸው። ልዩነቱ ደካሞች በምክንያት ታስረው፤ ከአቅማቸው በታች ሲኖሩ፤ ጠንካሮች ግን ችግሮቻቸው እና እንቅፋቶቻቸውን የውድቀት ምክንያት ከማድረግ ይልቅ፤ እራሳቸውን ይበልጥ ያጠነክሩበታል………ከመንገዳቸው የሚያቆማቸው ምንም ነገር የለም፤ ማንም ከአላማቸው አይግዝፍባቸውምና።

ያንተስ አላማ ምን ያህል ግዙፍ ነው?

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *