“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ምን ለያየን?

by | Mar 14, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ለአንዳንዶች ህይወት የተለየ ትርጉም አላት። ከጸሃይ መውጣት መግባት ባሻገር፤ ከክረምት በጋ መፈራረቅ ባሻገር፤ ህይወት የሆነ የተለየ ትርጉም አላት። እኒህ ሰዎች ለአቅማቸው ግድብ አያበጁም፤ ታልቅ ለመሆን የሌሎች ሰዎችን ፈቃድ አይጠይቁም፤ የተፈጠሩት ለሆነ አላማ እንደሆነ ያምናሉ። የተቀበረውን ችሎታቸውን ለማውጣት ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይጥራሉ። መውደቅ ማለት የአላማቸው ማክተም ሳይሆን፤ ይበልጥ የሚጠነክሩበት እና ገዝፈው የሚመጡብት እድል ነው። አመንም አላመንም ታላቅነት በሁላችንም ውስጥ ያለ ነገር ነው። ደስተኛ በሆኑት እና ባልሆኑት፤ ስኬታማ በሆኑት እና ባልሆኑት፤ በአሸናፊዎች እና በተሸናፊዎች መካከል ያለው ልዩነት የአስተሳሰብ ልዩነት ብቻ እንደሆነ የተረጋገጠ እውነታ ነው። ታላላቅ ሰዎችን ልዩ ከሚያረጋቸው ባህሪያት እና ከተገለጹላቸው ሚስጥሮች ውስጥ ጥቂቶቹ እነሆ…..

– የተመቻቸ ጊዜ አይጠብቁም- ቆይ ይሄን ሳገኝ ይህንን አደርጋለው፤ ይህ ሲመቻች ያሰብኩትን እፈጽማለው ስንል መቼም የማንደርስበት የህይወት ቀጠሮ እየያዝን ነው። ያሰቡትን ያሳኩ ሰዎች በሙሉ የተመቻቸ ጊዜ አግኝተው ሳይሆን፤ ጊዜውን ላለማጣት ሲሉ ብቻ ባልተመቻቸው ጊዜ እርምጃቸውን በመጀመራቸው ነው። የተመቻቸ ጊዜ የምትጠብቅ ከሆነ መቼም አይመጣም። ሁሉም ሰዓቶች ፤ ሁሉም ጊዜያቶች ከኛ ውስጥ የሆን ነገር ማጉደላቸው አይቀርም፤ ስለዚህ “የተመቻቸ ጊዜ” እየጠበቅክ ጊዜህን አታባክን….ከሁሉ በላይ ምቹዋ ሰዓት ይህች ያሁና ደቂቃ ናት።

-ደግመው ደጋግመው ይውድቃሉ- መጻፍ አትችልም ተብለህ ታውቃለህ፧ መሳል አትችልም ፤ መዝፈን አትችልም፤ መናገር አትችልም፤ ጎበዝ መሆን አትችልም ተብለህ የምታውቅ ከሆነ፤ የመውደቅን ስሜት ታውቀዋለህ ማለት ነው። እኔ በግሌ ከአንዴ በላይ አትችይም ተብዬ አውቃለው። ያኔ ምኞቴ የሞተ ያከተመለት መስሎኝ ነበር። በዚህ ምድር ላይ ህልም አጥፊዎች  በማናችንም ህይወት ውስጥ መኖራቸው አይቀርም። በወደቅክ ቁጥር የሚያነሳህ ሰው አትጥብቅ፤ እራስህን ቀና ማድረግ ካቃተህ ውድቀትህ ማንነትህ እንዲሆን ትፈርዳለህ። ብዙ ስኬታማ ሰዎች ወዳቂዎች ናቸው፤ አንተ በወደቅክ ቁጥር  ምን ያህል ትነሳለህ?

-“እንዴት” አይሉም- ብዙ ስኬታማ ሰዎች ሲጠየቁ፤ “እንዴት” የሚለው ጥያቄ አላማህን እንድትጠረጥር እና በራስህ እንዳትተማመን ሊያደርግህ ይችላል ይላሉ። ምክንያቱም እንዴት ካልን ብዙ መልስ የሌላቸ ጥያቄዎች ይነሳሉ። እንዴት የሚለውን ጥያቄ ለማምልጥ፤ ትኩረታችንን በዛሬ ላይ ማድረግ ነው። አንዴ አንድ ታዋቂ የውጭ ሃገር የፊልም ሰሪ አንድ ግሩም ታሪክ ሲናግር ሰምቼው ነበር። ይህ ሰው ልጅ እያለ አባቱ እሱን እና ወንድሙን ወደ አንድ ወደፈረሰ ግንብ ይወሳደውና፤ መለሰው እንዲገነቡት ይነግራቸዋል። ይሄኔ አባታቸውን “እንዴት ነው ትልቅ ግንብ መስራት የምንችለው፧ አይሆንም ” አሉት። አባትየው መልሶ “እንዴት አትበሉ….ማድረግ ያለባችሁ እያንዳንዱ  ብሎኬት መቀመጥ እንዳለበት ማስቀመጥ ብቻ ነው…..ትልቅ ግንብ መስራት ሳይሆን ፤ ብሎኬቱን በትክክል በማስቀመጥ ላይ ብቻ አተኩሩ፤በመጨረሻ ትልቅ ግንብ ይኖራችሃል” አሉ። አንተም እንዴት ታዋቂ እንደምትሆን፤ እንዴት ስኬታማ መሆን እንዳለብህ አትጨነቅ፤ አሁን ማተኮር ያለብህ፤ ወደዛ የሚወስድህ መንገድ ላይ ነው። በቀን ምን ያህል ጊዜ ለምትፈልገው ነገር ታሳልፋለህ፧……..መስራት ያለብህን ነገርስ ምን ያህል በጥራት እና በልበ ሙሉነት ትሰራለህ

– ልዩ መሆንን አይፈሩም- እርግጥ ነው የተለየ አስተሳሰብ ካለህ ፤ ከብዙሃኑ መለየትህ አይቀርም።በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አታግኝም። ያ ግን ሃሳብህን እና መንገድህን እንድትቀይር አያድርግህ። በተለይ ተዘፍቀህበት ከነበረው ህይወት ለመውጣት የምትታገል ከሆነ፤ ብዙ ሰዎች መልሰው ሊጎትቱህ ይሞክራሉ። ለየት በማለትህ፤ ከስዎች ላትጣጥም ትችላለህ፤ የሰው ስሜት ልትጎዳ ትችላለህ…ላንተ የቱ ይገዝፍብሃል? ሰዎችን ማስደስት ወይስ? የምትፈልገውን መሆን?

-እራሳቸውን እጅግ ይወዳሉ- እራስን መውደድ ማለት ከልክ ያለፈውን እራስ ወዳድነት ሳይሆን፤ እራስን መቀበል ማለት ነው። ሰውነትህን ተንከባከበው፤ ለጤናህ ትኩረት ስጥ፤ ምክንያቱም ስኬታማነት ወይም ደስተኛነት ንቁነትን ይጠይቃል። ተፈጥሮ የሰጥችህን መልክ ውደደው። ትልቁ ውብት እራስን መሆን ነው። አንዳንዴ መላካቸው አይን ውስጥ የማይገባ፤ግን ጠንካራ መንፈሳቸው ፊታቸው ላይ ፈሶ ለመግለጽ የሚከብድ ውበት ያላቸው ስዎች አጋጥማችሁ አያውቅም›፤ እኔ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *