“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

መንፈሳዊነት ወይስ ሃይማኖተኛነት?

by | Feb 14, 2016 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 1 comment

አንዳንዶች በ”ሃይማኖተኛነት” (Religious)  እና “በመንፈሳዊነት” (Spiritual) መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ያምናሉ። በአንድ ወቅት ይህንን ጥያቄ ለአንድ አባት አቅርቤላቸው  የሰጡኝ መልስ እንዲህ የሚል ነበር “በመንፈሳዊነት የሚያምኑ ሰዎች መልካም ባህሪ ቢኖራቸውም መንፈሳቸውን የሚያጠነክሩበት እና ጸንተው እንዲቆሙ የሚያደርጋቸው አንድ እምነት የላቸውም” የሚል ነበር። በሌላ በኩል አንድ ሰው ሃይማኖተኛነትን እንዲህ ሲገልጸው ሰምቻለው ” ለምሳሌ አንድ ሰው በባህር ውስጥ ይሰምጣል፤ በመንገዱ የሚያልፉ ሁለት ሰዎች ነበሩ አንደኛው ለሰመጠው ሰው እንዴት ከባህሩ መውጣት እንዳለበት ከዳርቻው ቆሞ ያስረዳዋል “በደንብ ቅዘፍ፤ ጭንቅላትህን ወደ ውሃው አትቅበር” እያለ ይጮሃል። በሌላ በኩል ሁለተኛው መንገደኛ ወደ ባህሩ በመጥለቅ የሰመጠውን ሰው ያወጣዋል። ይህ የሃይማኖተኛነት እና የመንፈሳዊነት ልዩነት ነው፤ ሃይማኖት ማመን መንፈሳዊነት መሆን ናቸው እንደማለት ነው” ይላል።  በሌላ በኩል አንዳንድ ጽሁፎችን ሳገላብጥ ይህንን ትርጉም አገኘሁኝ

“Religion and spirituality are two related yet distinct terms associated with faith. Religion denotes “a set of beliefs concerning the cause, nature, and purpose of the universe, usually involving devotional and ritual observances and a moral code.” In contrast, spirituality can be defined as “the quality of being spiritual” (both definitions adapted from www.dictionary.com).

Based on these definitions, the major difference between religion and spirituality is one of believing versus being. Religion’s focus is the content of one’s belief and the outworking of that belief; spirituality’s focus is the process of becoming more attuned to unworldly affairs. It’s possible to be religious without being spiritual and spiritual without being religious” http://www.compellingtruth.org/ ይህ ሊያከራክረን የሚገባ ሃሳብ አይመስለኝም ሁላችንም የራሳችን የሆነ አመለካከት ስላለን።

ይህንን እንዳነሳ ያደረገኝ ግን፤ ድንገት ከተለያየን ብዙ ጊዜ የሆነን  ጓደኛዬ በህሊናዬ ቢመጣ ነው። ፋሲካ ይባላል አብረን ለጥቂት ጊዜያት በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሰርተን ነበር። አንድ ቀን ጨዋታን ጨዋታ ያነሳውና ሃይማኖቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኩት። የመለሰልኝ መልስ መቼም ከህሊናዬ የማይጠፋ ነበር። “እስካሁን በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ኖሬያለው፤ በስተመጨረሻ ከሁሉም የሃይማኖት ህግጋት መካከል ህይወቴን በስርዓት እንድመራ የሚያደርገኝን መርህ አገኘው” አለኝ። እኔም ምን ስል ከሃይማኖት ሃይማኖት መዝለሉ እየገረመኝ ጠየቅኩት ። ጓደኛዬም መልሶ “”አንተ ላይ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አታድርግ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እጅግ እወደዋለው፤ እድሜዬን በሙሉ በዚህ መርህ ብመራ ስህተት ለመፈጸም እድሌ ጠባብ ነው” ሲል ከህሊናዬ የማይጠፋ መልስ መለሰልኝ።

ስለ ሀይማኖት የማውራት እውቀቱም ሆነ ጥበቡ የለኝም። ነገር ግን የጓደኛዬ አባባል እወነትነቱ ይታየኛል። ሰው በራሱ እንዲደርስ የማይፈልገውን ነገር ሌላው ላይ ባያደርግ፤ አለም ምን መልክ ይኖራት ነበር? አንዳችን በአንዳችን ጫማ  ወስጥ ለደቂቃ መቆም ቢቻለን፤ ምን አይነት ኑሮ ይኖረን ነበር? እንደኔ እንደኔ የሃይማኖት መሰረቱ ፍቅር ነው።እስከየትኛውም ድረስ ብንመረምረው መነሻውም መድረሻውም ፍቅር ይመስለኛል። “አንተ ላይ እዲደረግብህ የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አታድርግ” የሚለው የመጽሃፍ ቅዱስ አባባል፤ ጥልቁን ሃይማኖት፤ በትንሽ ቃላቶች እንድንረዳ የሚያደርገን ድንቅ አባባል ነው።

ሁላችንም በውስጣችን የምንዋጋው የራሳችን የሆነ የኑሮ ጦርነት አለብን። ቆሞ ከሚታዬው ማንነታችን ጀርባ ከራሳችን በቀር ሌሎች በቀላሉ ሊረዱት የማይችሉት ፈተናን ይዘን ነው የምንጓዘው። የቆምንበት እንጂ የመጣንበትን ሰዎች አያውቁትም እኛም እንደዛው ሌሎች የቆሙበትን እንጂ የመጡበትን አናውቅም። ነገር ግን ነገሮችን እንደራሳችን  መመልከቱን ስላልለመድንበት እርስ በርሳችን እንወቃቀሳለን። ሌሎችን ከመረዳት ይልቅ መፍረዱ ይቀለናል።

ጓደኛዩ ፋሲካ ብልህ ነው ፤ እንደ ህይወቱ መመሪያ የመረጣት “አንተ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አታድርግ” የምትለዋ ጥቅስ ከብዙ ስህተቶች፤ ከብዙ ጥፋቶች፤ ከብዙ ጸጸቶች፤ ከብዙ ሃጥያቶች የምትታደግ ድንቅ መርህ ናት። መዋረድ፤ ክብር ማጣት ምንድን ነው ስሜቱ? ስሜቱን የሚያውቀው ሰው በቀላሉ ሌላው ላይ አያደርገውም። የመክዳትን፤ የመጥላትን፤ የበቅለን ጦር ወደራሳችን ፊት ብናዞረው በቀላሉ እንወነጭፈው ነበር? በጭራሽ!!!

በእለት ተለት ህይወታችን ለኛ እንዲደረግብን የማንፈልገውን  ነገር በሌሎች ላይ ላለማድረግ ብንጥር፤ ሰይጣን በእርግጠኝነት ስራ ይፈታ ነበር። አባቶቻችን “ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” ይላሉ። ሃይማኖተኛ ባንሆንም መንፈሳዊ በመሆን አለምን የተሻለች ቦታ ማድረግ የሚቻል ይመስለኛል። ወይም የትኛውንም ሃይማኖት ብንከትል መንፈሳዊነትን ባህላችን፤ የኑርዋችን መስረት፤ የአስተሳሰባችን መመዘኛ እንዳርገው።  ሃሳብዎን ማካፈል አይርሱ።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. Abereham

    EWUNET NEW SEW BERASU LAY ENDEDEREG YEMAFELEGWUN BESEW LAY KALAREG BEKA YEHE NEW MENEFESAWINET MALET BEZU EREMEJA LENEHEDEBET YEMIYASECHELEN

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *