“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሌሎች ሰዎች ስለአንተ ያላቸው አመለካከት ያንተ እውነታ እንዳይሆን ተጠንቀቅ

by | Mar 1, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ስለራስህ ተናገር ብትባል እራስህን እንዴት ትግልጻለህ? ብዙ ጊዜ ስለራሳችን ከሰው የምንሰማውን እንደ እውነታ ተቀብለን፤ እራሳችንን ለመግለጽ ለገዛ እራሳችን እድል አንሰጠውም። ከልጅነት እስከ እውቀታችን ድረስ፤ ማንነታችንን የሚሞርዱት ብዙዎች ናቸው። ሁሉም በክፋት አይደለም፤ አንዳንዶች እኛን የጠቀሙን እመስላቸው ነው። ምንም እንኳን ውስጣችንን ለማየት እድል ባይኖራቸውም፤ ከላይ በሚያዩት ነገር ብቻ እየገመገሙ፤ ቅጥያ ማንነት ይልጥፉብናል። እኛም ለምደነው ማንነታችንን ሰዎች እስኪሰጡን እንጥብቃለን።

ሰዎች እውነትኛውን ማንነትህን ለማወቅ ባይቻላቸውም አንትን ከመገምገም አይቆጠቡም። እንድ ጉድለትህን አይተው ደካማ ማንነት አለህ ይሉሃል። አንዲት ውድቀትህን አይተው አትችልህም ይሉሃል፤ ያኔ የማይችል ማንነትን የግልህ አደረግከው ማለት ነው። ሽንፈትህን አይተው ፤ ተሸናፊ ማንነት ያጎናጽፉሃል። የአንድ ቀን ንዴትህን አይተው ፤ ትእግስት አልባ ነህ ይሉሃል። የአንድ ቀን ስህተትህን አይተው፤ ትክክል እንደማትሰራ ያሳምኑሃል።

በተለያየ ጊዜ የተሰጠሁን ማንነት የምትሸከም ከሆነ እውነተኛው ማንነትህ ህይወት እንዲዘራ እድል አትሰጠውም። እንኳን ሌሎች ሰዎች ይቅርና፤እራሳችን እራሱ የገዛ ማንነታችንን በቅጡ ለማወቅ ይከብደናል። የሚገርመው ግን ፤ ሌሎች የሚሰጡንን ስም አይምሮዋችን በቀላሉ መቀበሉ ነው። አንችልም የምንለው እኮ፤ ሌሎች በአንድ ውቀት አትችልም ሳላሉን ነው። አይሆንም የምንለው እኮ እራያችንን በራሳችን አይን ተመልክተነው ሳይሆን በሌሎች አይን ስላየነው ብቻ ነው።

እራስህን እንድ የተለያየ ገጽታ እንዳለው አራት መዓዝን መጫወቻ ቁጠረው። ቤተሰብህ በአንድ ጎን ያለውን ማንነትህን ያያል፤ መምህሩ በሌላ ጎን ያለውን ያያል፤ አለቃህ፤ ጋድኛህ ፤ ሌሎች ሁሉም አንተን በተላያየ አቅጣጫ ነው የሚመለከቱህ። ማናቸውም ሙሉውን አንተነትህን ለማየት እና ለመገምገም እድል አያገኙም።

በአንድ በኩል ባይሳካልህ፤በሌላው ገጽታህ ልዩ እና ስኬታማ ነህ። ሰዎች ግን ያንን ስለማያዩ፤ ከተሸነፍክበት ሜዳ ላይ ተነስተው ደካማ ማንነት ያላብሱሃል፤ ጆሮ ከሰጠሃቸው እውነተኛ ማንነትህ ሆኖ ይቀራል። ደስተኛ ለመሆን ከፈለግክ ግን፤ የገዛ ማንነትህን እራስህ ቅረጸው። የሌሎች ሰዎች አስተያየት የማትፈልገውን ማንነት እንዳያሲዝህ ተጥንቀቅ። ማናቸውም የውስጥህን አያውቁምና፤ በጥቂት ነገር ተነስተው በሚስጡህ አስትያየት፤ አትውደቅላቸው። ሰላንተ ሌሎች የሚሉት እና የሚሰጡህ ማንነት ያንተ እውነታ አይደለም። ያንተ እውነታ መሆን ያለበት፤ መሆን የምትፈልገው ማንነትህ ነው።

“ሌሎች ሰዎች ስለአንተ ያላቸው አመለካከት ያንተ እውነታ እንዳይሆን ተጠንቀቅ; ሁሉም የሚመለከቱህ ከተለያየ አቅጣጫ ነው፤ ደካማ ጎንህን ብቻ ያዩት፤ ጠንካራውን ሳያዩ ደካማ ነህ ማለታቸው አይቀርምና።”

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *