“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ለብ…….

by | Feb 19, 2017 | Guest writer-እንግዳ ጸሃፍት | 4 comments

እግዜር ግን እንዴት ነው እንዲህ ውሉ የጠፋው?

ከቀዝቃዛው ይልቅ ለብ ያልውን ገፋው.

ያልሞቁ ወይም ያልቀዘቀዙ ስሜቶች፤ ያልሞቁ ወይ ያልቀዘቀዙ ሰዎች፤ እጅግ አስቸጋሪዎች ናቸው። ለውሳኔ የሚያስቸግሩ፤ ልክ መንታ መንገድ ላይ ቆሞ ወዴት መሄድ እንዳለብን መወሰን የሚከብደን አይነት ስሜት ማለት ነው። ወደ ግራ አልያም ወደቀኝ ላለማለት ከወዲያ ወዲህ መውለብለብ፤ የለብታ ባህሪ ነው። እሺ ወይም እምቢ ለማለት መቸገር፤ ለመቀበል ወይም ለመተው መውሰን አለመቻል “ለብ” ማለት ነው።

“ወይ ሙቅ ወይ ቀዝቅዝ፤ ለብ ግን አትበል” ሲባል እንሰማለን። ግን እንደሰው ብናስበው ከቀዝቃዛ ይልቅ ለብ ያለ ነገር አይሻልም? አባባሉን እንደቅኔ ስንመረምረው ግን እውነትም ለብ እንደማለት የሚደብር ነገር የለም። ለብ ያሉ ሰዎች ለማንኛውም አይነት ግንኙነት ምቹ አይደሉም። “ለብ” ማለት በሙሉ ልብ ነገሮችን አለመከወን ማለት ነው።

ለብ በሚሉ ሰዎች ጊዜያቶች ይቃጠላሉ። ለብ በሚሉ ስሜቶች እውነት ትደበዝዛለች፤ ደስታ መፍካት ያለባትን ያህል አትፈካም። በልብታ ብዙ ስሜቶች እንደዘበት የእድሜ አውቶቢስ ላይ ተንጠልጥለው ይጓዛሉ።

አንዳንዴ ጓደኝነታችን የሚከስመው፤ ትዳራችን የሚቀዘቅዘው ለብ በሚል ስሜት ስለምንመራቸው ይሆናል። እድሜያችንን ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ብዙ ነገሮችም በስተመጨረሻ ውጤት አልባ የሚሆኑብን ለብ ባለ ስሜት ስለምንከውናቸው ነው።

ለብ ማለት እኮ “ልበል ልተው” “ልስራው ይቅር” “ልውደድ ልጥላ” “ልረፍ ልስራ” በሚሉ መንታ ሃሳቦችን ዘወትር መወጠር ማለት ነው። አንዳንዶቻችን እኮ ህይወታችን ከቀውስ የማይወጣው ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ለማስታረቅ ስለምንሞክር ነው። ለምሳሌ፦

ትክክለኛውን ነገር ማድረግ እንፈልጋለን በተቃራኒው ደግሞ ሁሉንም ለማስደሰት ልባችንን እናወልቃለን፤ ይህ እኮ ለብ ማለት ነው።

የሀይማኖተኛነት እርጋታ ይስበናል፤ በተቃራኒው ደግሞ የአለም ሞቅታ ያጓጓናል፤ ይህም ለብ ማለት ነው።

እውነተኛ ፍቅርን እንመኛለን፤ ውጫዊውን ነገር ግን አሳልፈን መስጠት አንችልም፤ ይህም ለብ ማለት ነው።

ሰርቶ መክበር ያምረናል፤ በተቃራኒው ደግሞ እረፍቱም ልባችንን ይሰርቀዋል፤ ይህም ለብ ማለት ነው።

ባጠቃላይ አብዛኛዎቻችን በመንታ መንገድ ላይ የቆምንን ነፍሶች ነን፤ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ለማስታረቅ የምንሞክር ምስኪኖች…..ምናልባት ወደ ውስጥ…..አዎ ወደውስጥ ማየት ከቻልን….በጫጫታ የሸፈንነውን መንታ መንገድ ማየት እንችላለን። “ወይ ሙቅ ወይ ቀዝቅዝ ለብ ግን አትበል” የተባለው ለጽድቅ እና ኩነኔ ብቻም ሳይሆን…..የዚህንም አለም መንታነት የሚያሻግረን ድንቅ ሚስጢር ይመስለኛል።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

4 Comments

  1. henok

    thanks my dear once again

    Reply
  2. henok

    i admire you a lot what i tell you beyond the power that the word could not express.never give up it until what your life were finished from the planet of earth.

    Reply
  3. Lilyana

    You reminded me a chritian song which i used to sing when i was young “Berad alhonk we tikus aluhonk, leb bye aschegrehalehu”
    God bless you and thanks

    Reply
  4. Tariku

    wooow….des yilal……we respect u Mistre.

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *