“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ለራሳችን ያለን አመለካከት- SELF IMAGE 

by | Jul 23, 2018 | መነቃቂያ inspiring stories | 10 comments

(በሚስጥረ አደራው) 

ከምንም በላይ አንዳችንን ከሌላኛችን የሚለየን ነገር ቢኖር ለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም ምስል በእንግሊዘኛው ደግሞ Self Image ነው። የስነ ልቦና ባለሙያዎች ስለዚህ የስነ ልቦና ጥበብ መጀመሪያ ባጠኑበት ወቅት፤ ታላቁ የስነልቦና ግኝት ብለውት ነበር። ሁላችንም በዚህ አለም ላይ ስንኖር የኑሮዋችን መጠንና ልኩ የሚወሰነው ለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም በአይምሮዋችን ውስጥ ስለራሳችን በምንቀርጸው ምስል ነው። ባህሪያቶቻችን፤ ውሳኔዎቻችን፤ አጋጣሚዎቻችንና በህይወታችን የምንስባቸው ሰዎች በሙሉ ለራሳችን ባለን አመለካከት ተጽዕኖ ስር ይወድቃሉ።

ለራስ የሚሰጥ አመለካከት (self Image) በህይወታችን እጅግ ወሳኝ ነገር ነው። አንድ ሰው ስኬታማና ደስተኛ ሊሆን የሚችለው ለራሱ የተስተካከለና አወንታዊ አመለካከት ሲኖረው ብቻ ነው። ችግሩ ይህንን እውነታ ማንም ሰው ከልጅነታችን ጀምሮ ስለማያስተምረን አብዛኛዎቻችን ለራሳችን የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ እናድጋለን። አቅምና ችሎታችንን የሚገድቡ እምነቶች ( Self Limiting beliefs) ሳናውቀው በአይምሮዋችን ውስጥ ስር ይሰዳሉ። እኒህ አመለካከቶቻችን ናቸው የምንፈልገውን ኑሮ እንዳንኖር እንቅፋት የሚሆኑብን።

“እርሱ እችላለሁ የሚለውም፤ አልችም የሚለውም ሁለቱም ትክክል ናቸው”- ኮንፊሺየስ

ህይወታችንን ሊቀይሩ የሚችሉ እውነታዎች በሙሉ ቀላልና ያልተወሳሰቡ ሀሳቦች ናቸው። ምናልባት ለዛም ይሆናል በቁም ነገር ወስደን የማንተገብራቸው። እኛ ሰዎች በተፈጥሮዋችን የተወሳሰበና ከባድ ነገር ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ይመስለናል። ለችግሮቻችን መፍትሄ ስንፈልግ እንኳን ቀለል ያለ ሃሳብ አንቀበልም። እቃ ስንገዛ የተወደደው እቃ ሁሌም ከረከሰው የተሻለ ይመስለናል፤ በወረፋ ካልተሰለፍን በቀር የምናገኘው አገልግሎት ጥራት ያለው አይመስለንም። ተሻምተን ካላገኘናቸው በቀር ነጻ ለምናገኛቸው ነገሮች ዋጋ አንሰጥም። እራሳችንን ለመለወጥ ስናስብም እንደዛው፤ በቀላሉ አስተሳሰባችንን በመቀየር ህይወታችንን መቀየር እንደምንችል አምነን መቀበሉ ይከብደናል። ሰው አስተሳሰቡን በመቀየር ኑሮውን መቀየር እንደሚችል ለብዙ መቶ አመታት ሲንገር የነበረ ቢሆንም፤ ግልጽና ቀልላ ሀሳብ ስለሆነ ነው መሰል እምነት አንጥልበትም።

እያንዳንድችን ስለራሳችን በአይምሮዋችን የምንቀርጸው ምስል አለ። ይህ ምስል መልካም ምስል ካልሆነ በኑሮዋችን ላይ የሚጸባረቁት እውነታዎችም ከዚህ ምስል የተለዩ አይሆኑም። በተቃራኒው ስለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም በውስጣችን የምንስለው ምስል መልካም፤ጠንካራና አወንታዊ ከሆነ፤ በኑሮዋችን ላይ የሚንጸባረቁት እውነታዎች በሙሉ የአወንታዊው አመለካከታችን ነጸብራቆች ይሆናሉ። ይህ ለራሳችን የምንሰጠው አመለካከትና ግምት ነው፤ በራሳችን ላይ የሚኖረንን እምነት የሚወስነው። በራስ መተማመናችን የሚበቅለው ለራሳችንን ባለን አመለካከት አፈር ላይ።

በትምህርትም ሆነ በስራ፤ በፍቅርም ሆነ በግል ህይወታችን ውስጥ  የምናገኛቸው ውጤቶች ለራሳችን ካለን አመለካከት የሚመነጩ ናቸው። ምናልባት እዚህኛው ጽሁፌ ላይ ትንሽ ስለራሴ መናገር ያለብኝ ይመስለኛል። ከአመታት በፊት ስለራሴ የነበረኝ አመለካከትና አሁን ስለራሴ ያለኝ አመለካከት እጅግ የተራራቁ ናቸው። ለራሴ አነስተኛ አመለካከት በነበረኝ ወቅት ብዙ ነገሮችን “በአልችልም” ስሜት ሸሽቻለሁ። አቅሜን ባለማወቄ ከሚገባኝ በታች የሆኑ ነገሮችን አሜን ብዬ ተቀብዬ ነበር። የተሻለ ህይወት ለሌሎች እንጂ ለእኔ የሚገባኝና የሚቻል ስላልመሰለኝ እራሴን ወደኋላ ጎትቼዋለሁ። ሆኖም ግን እራሴ ላይ መስራት ከጀመርኩኝ ጀምሮ ( After I embarked on the journey of personal development) ኑሮዬ የሚወሰነው ለራሴ ባለኝ አመለካከት መሆኑን ለመረዳት ግዜ አልፈጀብኝም። ደስታና ስኬት፤ ፍቅርና ክብር፤ መውደድና መወደድ ለሁላችንም የቀረቡ ገጸ በረከቶች ናቸው። ለራሳችን አወንታዊ አመለካከት ሲኖረን ብቻ ነው እኛም እንደማንኛውም ሰው ከኒህ ገጸ በረከቶች የፈለግነውን ያህል መቋደስ እንደምንችል የምናምነው።

ለራሳችንን ያለንን አመለካከት መለወጥ እረጅም መንገድ ነው (It’s a Never Ending Process)። ምክንያቱም ስለራሳችን በውስጣችን የምንስለው ምስል የተሳለው በእኛ ብሩሽ ብቻ አይደለም። ቤተሰብ፤ ማህበረሰብ፤ ጓደኛ፤ አስተማሪ እንዲሁም ሌሎች አጋጣሚዎች የየራሳቸውን አሻራ አኑረውበታል ወደፊትም ከተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ማምለጥ አንችልም። ሆኖም ግን አመለካከታችንን የመለወጥ ሙሉው ሃላፊነት የማንም ሰው ሳይሆን የራሳችን ብቻ መሆኑን ማመን መቻል አለብን። ይህ እምነት የመጀመሪያው እርምጃ ስለሆነ።

ስለራሳችን ስናስብ የሚመጣብን ምስል አወንታዊ ካልሆነ በእርግጠኝነት አመለካከታችን ለማስተካከል እራሳችን ላይ መስራት አለብን ማለት ነው። በአይምሮዋችን ውስጥ የምንፈልገውን ኑሮ መኖር እንደማንችል የሚነገርን ድምጽ ካለ፤ በፍርሃትና በአልችልም ስሜት የሚያስፈራራን ምስል በውስጣችን ካለ፤ ለራሳችን ያለንን አመለካከት የተሳሳተ እንደሆነ የሚያረጋገጡልን ምልክቶች ናቸው። ለራሳችን የምንሰጠው አመለካከት የኑሮዋችን ካርታ ነው። አወንታዊና ገንቢ አመለካከት ሲኖረን አቅጣጫችን ወደ ተሻለ ህይወት ነው። በተቃራኒው ለራሳችን ያለን አመለካከት ዝቅተኛ ከሆነና ስለራሳችን ስናስብ አሉታዊ ምስል የሚቀረጽብን ከሆነ እየተጓዝን ያለነው ወደማይጠቅመን ጎዳና ነው። ደስተኛ ለመሆን የተስተካከለ አመለካከት ወሳኝ ነው፤ ስኬታማ ለመሆን ስለራሳችን አወንታዊ ምስል በውስጣች ሊኖር ግድ ይለናል። ይህ ሀሳብ እጅግ ሰፊ ነው፤ ጽሁፌን ግን ማንዴላ በእስር ሳለ ብርታት ይሰጠው ከነበረው ድንቅ ግጥም ውስጥ በተወሰደች ስንኝ ልቋጭ።

“እኔ ነኝ የእድሌ ወሳኝ፤ የእጣ ፋንታዬ መሪ

የነፍሴ ጀልባ ቀዛፊ፤ የኑሮዬ ሹፌር ዘዋሪ”

“It matters not how strait the gate,

How charged with punishments the scroll.

I am the master of my fate:

I am the captain of my soul.”- Invictus poem by William Ernest Henley.

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

10 Comments

  1. Abayneh

    Thank u for Sharing such inspirational & Motivational article u made!

    Reply
  2. Tariku

    ………ደስታና ስኬት፤ ፍቅርና ክብር፤ መውደድና መወደድ ለሁላችንም የቀረቡ ገጸ በረከቶች ናቸው። ለራሳችን አወንታዊ አመለካከት ሲኖረን…………..thank u Mistre…..it is comforting..

    Reply
  3. Estiph Estipho

    You guys have beenthe hub source of such inspirational thoughts and principles on Sheger fm monday night program
    Soo intersesting to hear those energetic pivot for our life
    Keep it u?????

    Reply
  4. Habtamu

    “እኔ ነኝ የእድሌ ወሳኝ፤ የእጣ ፋንታዬ መሪ

    የነፍሴ ጀልባ ቀዛፊ፤ የኑሮዬ ሹፌር ዘዋሪ”
    really it is interesting,inspiring….thanks a lot

    Reply
    • Misker

      Thank you mistre for those amazing and building thoughts you are pioneer for the personal development environment in Ethiopia please continue inspiring us…

      Reply
      • Mistre

        Thank you so much! It means a lot to me. God bless you!

        Reply
  5. Misker

    Thank you so Mach dear mistre you are inspiring generations and for me you are a pioneer to bring personal development online keep rocking .

    Reply
    • Mistre

      Thank You so much! We need to motivate each other.

      Reply
  6. nebro bezahun

    እንዳጠቃላይ የምታካፍይን ጽሁፍ በጣም ጥሩ ነዉ ፈጣሪ ጥበቡን አብዝቶ እንድገልጽልሽ ተመኘሁ

    Reply
    • Mistre

      Thank you! I appreciate your feedback! Blessings to you as well.

      Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *