“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ህይወታችን በራሳችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የሚረዱን መንገዶች-ክፍል ፫

by | Mar 23, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 0 comments

ለማን ነው የምንኖረው?…..መልስ የሚያስፈልገው ጥያቄ!!!

በትንሹ እበድ- አንዳንዴ በእብድ ሰው ቀንታችሁ አታውቁም? ያሰበውን ተናግሮ፤ የፈለገውን አድርጎ፤ ስለሰው ሳይጨነቅ፤ በይሉንታ ሳይታሰር፤ ከሰው በላይ ነጻነት አግኝቶ ሲኖር ትንሽ አይገርምም?  እንበድ እያልኩኝ ሳይሆን የኛ ጤንነት ትንሽ አልበዛም ትላላቹ? ስለሰው ኖርን፤ ስለሰው አስበን፤ በይሉኝታ የማንፍልገውን ህይወት መርጠን፤ እስከመቼ እንኖራለን? ሰውን ለማስደሰት ስንጥር ምስኪኑ “እኛነታችን” መብቱን ሲያጣ አያሳዝንም? በጤነኛነት ስም ሰው ነጻነቱን እንዴት ያጣል? እውነቱን ለመነጋገር የሆነ ነገር ማድረግ ተመኝተህ ሰው ምን ይለኛል ብለህ የተውካቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? የማን መብት ነው መጀመሪያ መከበር ያለበት? ያንተ ወይስ የሰው? ይህንን ጥያቄ ኑሮህን በደንብ በማስተዋል፤ መልሱን ለራስህ መልሰው።

እያንዳንዱ አስተሳሰብህን ልብ ብለህ አስተውለው- ሳይንስ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ ሰዎች እንደሚያስቡት ሀሳብ ነገሮችን ወደራሳቸው ህይወት ይስባሉ ይባላል:: “The law of attraction” የተባለው የተፈጥሮ ህግ የብዙዎችን ህይወት ሲለውጥ ይታያል። ቀና የሆኑ ነገሮችን ማሰብ ስንጀምር፤ ቀና ይሆኑ የህይወት ገጠመኞችን ወደራሳችን እንስባለን። በአንጻሩ መጥፎ አስተሳሰቦችን የምናስብ ከሆነ….መጥፎ ነገሮችን ወደ ህይወታችን መሳባችን አይቀርም። ምን አልባት በዚህ አስተሳሰብ የማይሳማሙ ሰዎች ሊኖር ይችላሉ፤ ግን ሁላችንም በራሳችን ህይወት መሞከር እና ማርጋገጥ የምንችለው ህግ ነው። ይህ ህግ አለም ሁሉ የምትመራበት ህግ ነው….ተመሳሳይ ይሆኑ ነግሮች ይሳሳባሉ፤ ነው የህጉ መሰረታዊ ትርጉም፤( The law of attraction is the name given to the term that “like attracts like” and that by focusing on positive or negative thoughts, one can bring about positive or negative results.)። ስለዚህ የምትፈልገውን ውጤት በህይወትህ ለማምጣት….ለነገሩ ያለህን አመለካከት በደንብ አስተውል።

የትላንት ታሪክህ የነገውን እጣፋንታህን እንዲወስን አትፍቀድ- ምናልባት የትላንት ታሪክህ እምብዛም አይጥምህ ይሆናል፤ ግን አስሮ እንዲያስቆምህ አትፍቀድ። ከማናችንም ህይወት ጀርባ መጥፎ እና አሳፋሪ ታሪክ አለ። እራሳቸውን ይቅር የማይሉ ሰዎች ግን እራሳቸውን በጥፋተኝነት ስሜት እየቀጡ፤ በራስ መተማመናቸው ስለሚወርድ፤ አዲስ ህይወት ለመመስረት ይከብዳቸዋል። በውድቀትህ፤ በስህተትህ ከቶ አትፈር…ስለኖርክ ነው ስህተት የፈጸምከው፤ ስለሞከርክ ነው የወደቅከው። ጠባሳዎችህ የሚያሳፍሩህ ሳይሆኑ የሚያኮሩህ ይሁኑ…..ምክንያቱም ጠበሳ ያለው ሰው ልብ አግኝቶ ከህይወት የተፋለመ ሰው ነውና።

እራስህን ከሸሸግክበት አውጣው- የአንዳንዶቻችን ማንነት በሱስ፤ ያንዳንዶቻችን ማንነት በስራ፤ ያንዳንዶቻችን ማንነት በግርግሩ፤ ያንዳንዶቻችን ማንነት በቸልተኝነት ውስጥ ተሸሽጓል። እራሳችንን ሽሽት….ጎዶሎነታችንን ላለማየት፤ ደካማ ጎናችንን ላለማስተዋል፤ አይናችንን ከህይወታችን ዞር ለማድረግ፤ በሆነ ነገር እንጠመዳለን። ግን እስከመቼ ከራሳችን እንሸሻለን? እራሳችንን እስከመቼ እናታልላለን? ብዙ ሰዎች መጠጥ ጨንጓራቸውን እስኪያካጥለው ድረስ የሚጠጡት፤ መጠጡ ጣፍጧቸው ነው?  አይመስለኝም። ሊያደብኑት የሚፈልጉት ሃሳብ በውስጣቸው ስላለ ነው። ደስተኛ ሰዎች ለመደነስ፤ ለመደሰት የመጠጥ ሃይል አያስፈልጋቸውም። መስከር ካለብህ፤ በተፍጥሮ ስከር፤ በደስታ ስከር፤ በፍቅር ስከር። ዋናው ነጥብ….እራስህ ለመለወጥ ስታስብ…በመጀመሪያ እራስህን የሸሽግክበትን ጉድጓድ ፈልገው፤ከዛ በፍቅር እና በተስፋ እራስህ አባብለህ ለማውጣት ሞክር….

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *