“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ህይወታችንን በራሳችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የሚረዱን መንገዶች-ክፍል ፩

by | Mar 18, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories | 1 comment

 

-የሰዎችን አይምሮ እኛ መቆጣጠር አንችልም….መቆጣጠር የምንችለው የራሳችንን አስተሳሰብ እና ምላሽ ነው። በአካባቢያችን ያለው መጥፎ ሁኔታ ደስታችንን የሚንጥቀን ፤ እራስን የመቆጣጠር ልምድን በደንብ ስላላከበትነው ነው። ለምሳሌ ሰዎች ስለኛ ምን ያስቡ ይሆን ብለን እራሳችንን እናስጨንቃለን። ይህን ጭንቀት የሚፈታው ሚስጥር ፤ እኛ የሌሎችን ሰዎች አስተሳሰብ እና አመለካከት እንዲሁም ለነገሮች ያላቸውን ምላሽ ፈጽሞ መቆጣጠር እንደማንችል ለራሳችን መንገር ነው። ሰዎች ሁሉ የተለያየ አስተሳሰብ እና እይታ አላቸው፤ ምንም ያህል ሰዎችን ለመማረክ ብንጥር፤ ሙሉ በሙሉ ፈጽሞ ሊሳካልን አይችልም፤ ስለዚህ ያልን አማራጭ የራሳችንን አመለካከት መቀየር ነው። እራሳችንን ብንሆን እና የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ሰውን ከመማረክ አንጻር ሳይሆን፤ እራሳችን ማድረግ ስለፈለግን ብቻ የምናደርገው ከሆን፤ ሁሉንም ማስደሰት ባንችል እንኳን እራሳችንን ከማስጨነቅ እንድናለን። በአብዛኛው ዝንድ ተወዳጅነት ያላቸው ሰዎች፤ እራሳቸውን የሆኑ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ ልዩነትህን እንደ ጉድለት አትየው። ሰዎችን ለማስደሰት በጣርክ ቁጥር ማንነትህ ስለሚሟሽሽ፤ ሰዎች አንተነትህን ለመቀበል ይከብዳቸዋል።

-ሌላው እራሳችንን ለመቆጣጠር የሚረዳን ነጥብ፤ በአካባቢያችን ተጽዕኖ ምክንያት ደስታችንን ለመነጠቅ ምቹ አለመሆን ነው። ለምሳሌ ደስተኛ ካልሆነ ቤተሰብ ከመጣን፤ ትዳራችን ሰላም ካልሆነ፤ መስሪያ ቤታችን የሚደበረን ከሆነ፤ በቀላሉ ደስታችን ሊሰረቅ ይችላል። ይህንን እንዴት መቀነስ እና ማስወገድ ይቻላል?

መቆጣጠር የማንችላቸው ነገሮች ላይ ሃይላችንን አለማፍሰስ ነው። ለምሳሌ ትዳራችንን እና ቤተሰባችን ውስጥ ሰላም እዲሰፍን የትቻለንን መጣር፤ ችግሩ ግን ከሌላው ወግን ከሆነ፤ ምን ማድረግ እችላለን? መስሪያ ቤታችን ውስጥም ሆነ አንዳንድ ማህበራዊ ሁኔታዎችም ላይ እንደዛው። ሃይላችንን መጠቀም ያለብን መቆጣጠር እና መቀየር የምንችለው ነገር ላይ ነው።ከእንደዚህ አይነት ተጽዕኖ እራሳችንን ለማውጣት፤ ደስታችንን ከኛ ውጪ በሆነ ነገር ሳይሆን በራሳችን ውስጥ መፈለግ አለብን። ሃቁም እሱ ነው፤ ከሰዎች በፊት እራሳችንን ማስደስት ያለብን እራሳችን ነን። ደስታችንን ከውጪ ነገሮች ጋር ለጥፈን ካኖርነው፤ በእርግጠኝነት አንድ ቀን በሆነ ምክንያት ልናጣው እንችላለን። ስለዚህ ደስታህን በገዛ ህይወትህ ውስጥ ፈልገው…..ያኔ ከአካባቢ ተጽዕኖ ለመቅጣት ይቀልሃል።

***መጥፎ ነገሮች ደጋግመው በህይወታችን እንዳይከሰቱ እንዴት እንከላከል?

በመጀመሪያ አይምሮዋንን በጥንቃቄ እንቃኘው፡ ስለነገሮች አስቀድሞ ግምት እና ውሳኔ ይሰጣል? ምን አይነት ግምት እና ውሳኔ ናቸው ? ለምሳሌ ደጋግመው ፈተና የሚወድቁ ሰዎችን እንይ ፤ እኒህ ሰዎች በአብዛኛውን ጊዜ ፈተናውን ከመፈተናቸው በፊት፤ እውድቃለው የሚል ስሜት ውስጣቸው ይጭራሉ። ባለፈው ህይወታቸው ካጋጠማቸው ችግር እና ውድቀት ተነስተው ስለሚጨነቁ አይምሯቸው አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚወድቁ የተነብያል። አይምሮዋችን ውሳኔ ሲወስን፤ ሃይላችን ውሳኔውን ይደግፋል።ካስተዋልነው፤ አንዳንድ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ችግሮች ደጋግመው ሲከሰቱ እናያለን፤ ምክንያቱም ከፍርሃት የተነሳ አይምሯቸው የበፊቱ ክስተት ዳግም እንደሚከሰት ያስጠነቅቃቸዋል፤ ደጋግሞ ይነግራቸዋል (እራሳቸው ለራሳቸው ይነግራሉ) ።በአፋቸው በጎ ነገር ቢመኙም፤ በውስጣቸው ግን ያለፈው ክስተት እየታወሰ ይረብሻቸዋል። ይህንን ለመለወጥ ከሚረዱን መንገዶች ውስጥ

-አይምሮዋችንን በጎነ ነገር እንዲያስብ ማለማመድ። ለምሳሌ አይምሮዋችን ያለፈውን ውድቀታችንን ሲያስታውሰን፤ በፍጥነት አስትሳሰባችንን መቀየር፤ ምስሉን መለወጥ። ስንወድቅ የሚያሳየውን ምስል ሰርዝን ፈተናውን ስናልፍ የሚያሳይ ምስል እና የሚኖረንን ደስታ በሂሊናችን መሳል።

-ሌላው ለአስተሳሰባችን አትኩሮት መስጠት፤ በቀን ምን ያህል እራስን ገንቢ የሆኑ አስተሳሰቦችንን እናስባለ? ምን ያህል ምጥፎ ወይም አስደሳች ያልሆኑ አስተሳሰቦች በአይምሮዋችን ይመላለሳሉ? እኒህን በአትኩሮት ባጤንን ቁጥር አይምሮዋችንን ወደ ቀናው መንገድ ለመቀየር ምቹ ይሆንልናል። አሁን ያለን ኑሮም ሆነ ማንነት የአስተሳሰባችን ውጤት ነው። መቀየት የምንፈልገውን ነገር ሁሉ የምንጀምረው ከአይምሮዋችን ነው…

-በመጨረሻ ማግኘት የምንፈለገውን ነገር በቻልነው አጋጣሚ ለራሳችን መንገር ነው። ይህ ዘዴ ካለፈው ውድቀታችን እንድንሸሽ በእጅጉ ይረዳናል። እውነታችንን ለመለውጥ ያስችለናል፤ ይህ ማለት የብዙዏቻችን እውነት ያለፈው ህይወታችን ነው፤ ያ ድግሞ መጪውም ካለፈው ብዙ ያልራቀ እንዲሆን ያደርገዋል። የምንፈልገውን ነገር ለራሳችንን ደጋግመን መንገርና፤ እራሳችንን ማሳመን፤ እንዲህ ማድረግ ስንጀምር፤እውነታችን ያለፈው ህይወታችን ሳይሆን ወድፊት የምናገኘው እና የምንመኘው ህይወት ይሆናል ማለት ነው።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

1 Comment

  1. Salam Salam

    ጥሩ አስተማሪ ትምህርት ነው እናመሰግናለን

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *