“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ጭንቅት- ዘጠና በመቶው ቅዠት

(በሚስጥረ አደራው) ማን እንዳለው ባላውቅም ይህንን አባባል ከህይወት መመሪያዎቼ እንደ አንዱ አድርጌ ብወስደው እመኛለው። አባባሉ ይህ ነው “ህይወትን የምትወድ ከሆነ ጊዜህን አታባክን፤ ምክንያቱም ህይወት የተሰራችው ከጊዜ ነውና።” ይላል። እውነት ነው፤ ህይወት ከጊዜ ጡብ የሚገነባ ትልቅ ግንብ ማለት ነው። ጊዜውን የሚቆጥብ ሰው ትልቅ የህይወት ግንብ ለመገንባት የሚያስችለው ብዙ ጦቦች ይኖሩታል። ጊዜውን...

ኑሮ እና ዋና

መዋኘት የሚችል ሰው በውሃ ላይ የመንሳፈፍ ጥበቡን በደንብ ያውቀዋል። ውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ጠንካራ መሆንን አይጠይቅም። ይልቅ ውሃ ደግ ሆኖ ከመስመጥ የሚታደገን ፈታ ብለን ስንጫወትለት ብቻ ነው። ውሃ ግትር ሰው አይወድም፤ እጅ እና እግሩን ከማያፍታታ ግትር ጋር ውሃ ልጫወት አይልም። በጉልበት እንሳፈፋለው ለሚል ሰውም ውሃ እርህራሄ የለውም።እኔ በግሌ ውሃ ላይ እምብዛም ድፍረት አለነበረኝም። ዋናን ከልጅነቴ ስላልተማርኩት፤...

ባገኘኸው ቦታ ብቀል…..

ይህች አበባ ከቤቴ በራፍ ላይ ያለች አበባ (አበባ መሳይ ቅጠል) ናት። ዘወትር ደረጃውን ስውጣም ሆነ ስወርድ እንዳልረግጣት እጠነቀቃለው። ጥንቃቄዬ የመጣው ግን ከብዙ ጊዜ በኋላ በተለየ አይን ስለተመለከትኳት ነው። አንድ ቀን በሬን ቆልፌ ወደታች ስወርድ፤ ድንገት ቁልፌ ከመሬቱ ላይ ወደቀ። ቁልፌ ወድቆ ያረፈው፤ ከዚህች ትንሽ አበባ መሳይ ቅጠል ጎን ነበር። ቁልፌን ከማንሳቴ በፊት፤ ይህችን ቅጠል አስተውዬ ተመለከትኳት።...

ለራስህ ያለህን አመለካከት የሚለውጡ አራት ነጥቦች

ኸርል ናይቲንጌይል በሰው ልጆች ባህሪ እና አስተሳሰብ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አበርክተው ካለፉ ተናጋሪ እና ጸሃፊያን መካከል ቅድሚያ የሚሰጠው አሜሪካዊ ነው። በብዙ ስዎች ዘንድ “The Strangest Secret” በተሰኘው ስራው ዛሬም ድረስ ይታወሳል። የናይቲንጌይል ስራዎች ሁሉም መሰረታቸው አንድ ነው “ሰው የራሱ ህይወት ፈጣሪ ነው” የሚል። በተለያየ ስራዎቹ ላይም፤ የሰው ልጅ...