“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ያልተሄደበት ጎዳና

by | Jan 29, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories

 

ህይወትን ሲኖሩዋት ደስ የምትለው ለመኖር ምክንያት ሲኖረን ነው። ለመኖር ምከንያት እና አላማ የሌለው ሰው እንዴት ነገው ያጓጓዋል? እንዴትስ ወደፊት ለመራመድ ብርታት እና ጉልበት ይገኛል? ህይወት ያቀረበችልንን ብቻ የምንቀበል ከሆነና የምንፈልገውን የማንጠይቅ ከሆነ የምድር ሸክም ከመሆን የዘለለ ኑሮዋችን ምን ትርጉም ይኖረዋል?

ሰው የተጓዘበትን መንገድ ተከትሎ የሚጓዝ ፤ ለዘመናት የተደቀደቀው ጎዳና ላይ የሚራመድ ሰው እንዴት የራሱን አሻራ አኑሮ ሊያፍ ይችላል? የመኖር መክንያት እና አላማ የሌላቸው ሰዎች ጎዳናቸው አንድ እና አንድ ነው…..እሱም የብዙ ሰዎች ኮቴ ያረፈበት ጎዳና….ለዘመናት የተደቀደቀ መንገድ። እረጅም ጉዞ ቢጓዙም እንኳን በዛ መንገድ ማለፋቸውን የሚያውቅላቸው ማን ነው?….እልፍ አዕላፍ ሰው አልፎበት የለ?

በአለም ላይ ያሉ ስኬታማ ሰዎች ሁሉ አንድ የሚጋሩት ነገር አለ። እሱም ከሌላው ሰዎች በተለየ ያስባሉ። ከሌላ ሰዎች በተለየ ማሰብ ምን ማለት ነው? ሁሉም ከሚጓዝበት ጎዳና የተለየ ሌላ አዲስ ጎዳና መቀየስ።አብዛኛዎቻችን ለመሆን የምንፈልገው ነገር ቢኖርም እንኳን ማንም ሰው ተጉዞበት እና ደርሶበት ስለማያውቅ ብቻ የማይሆን ይመስለናል። ነገር ግን ከሁሉም ስኬታማ ሰዎች አንደበት የሚሰማ አንድ ነገር አለ “ እስከዛሬ ተከስቶ የማያውቅ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ማመን የስኬት መንደርደሪያ ነው”።

ብዙዎቻችን የማንፈልገውን ኑሮ ለምን እንኖራለን?
የራሳችንን ጎዳና መቀየሱ አቅቶን? ተሂዶበት የማያውቀው መንገድ ላይ መጓዙ አስፈርቶን? ማንም ሰው አድርጎት የማያውቀውን ነገር ለማድረግ መሞከሩ ከብዶን ወይ አላውቅበት ብለን? ወደ ስኬታችን ስንጓዝ ብቸኝነቱ ተሰምቶን? መልሱ ለየራሳችን የሚመለስ ነው። እራሱን የሚጠይቅ ሰው፤ ከገዛ እራሱ ጋር በሂደት ይተዋወቃል። እራሱን የሚያውቅ ሰው ደግሞ፤ በውስጡ ያለውን መክሊት ለማወቅ እምብዛም መልፋት አይጠበቅበትም። ያኔ የራስን ጎዳና የመቀየስ ፍላጎቱ ይጠነሰሳል። ሁሉም ሰው ግን የጀመረውን ጎዳና አይጨርስም….ጥቂቶች ግን ይቻላቸዋል። ከሰው የተለየ አቅም ኖሮዋቸው ወይም ፈጣሪ አዳልቶላቸው ሳይሆን፤ የአላማቸው ጽናት እንደ መላዕክት ክንፍ ከፍርሃት ስለሚታደግላቸው ነው። የፍርሃትን ነበልባል የሚያጠፋው ውሃ ……..ጽኑ አላማ ብቻ ነው።

የማናችንም አሻራ እንደማይመሳሰል ሁሉ …..የሁላችንም የስኬት ጥሪ አይመሳሰ+ልም። ስኬታችን በራሳችን መስፈርት ብቻ የሚመዘን ነው። ዋናው ነጥብ ግን አሁን እየኖርነው ያለነውን ኑሮ መርጠነው ነው?……..ወይስ ብዙዎች ሲጓዙበት ስላየን?

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments