“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ከዶሮ መካከል የወደቀ ወፍ አትሁን

by | Jan 29, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories

ከእለታት አንድ ቀን ምድር የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰባት፤ መንቀጠቀጡ መሬት ላይ ያለውን ሁሉ ማነቃነቁ አይቀርምና ሁሉም ተናወጠ። በወቅቱ ከዛፍ ላይ አንድ የወፍ ጎጆ ነበረች፤ ይህች የወፍ ጎጆ በውስጧ እንቁላሎችን ይዛ ነበር። መሬቱ ሲንቀጠቀጥ ግን እንቁላሎቹን ይዛ ከነበረችው ጎጆ ውስጥ አንዱ እንቁላል ከዶሮዎች መንደር ወደቀ።

ዶሮዎቹ እንቁላሉን እንደ እራሳቸው እንቁላል ተንከባክበውና ታቅፈው እንዲፈለፈል አደረጉት። ወፉ እንደ ዶሮ ከዶሮዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ማደግ ጀመረ። እነሱኑ መስሎ ዶሮነቱን አምኖ ኑሮውን መግፋቱን ቀጠለ። ከእለታት አንድ ቀን ከዶሮ ቤተሰቦቹ ጋር አንድ ላይ ሆነው በመሬት ሲንሸራሸሩ ወፎች በሰማይ ሲበሩ ተመለከቱ። ይሄኔ ወፉ “ እኒህ በሰማይ በነፃነት የሚበሩት ወፎች ምነኛ የታደሉ ናቸው ፤ ምናለ እኔም እንደነሱ መብረር ብችል “ ሲል እራሱን እየተመለከተ ተናገረ። አብሮ አደጎቹ ዶሮዎች በወፉ ተሳለቁበት “ አንተ እኮ ዶሮ ነህ እንዴት እንደወፍ ለመብረር ታስባለህ “ ብለው ሃሳቡን አጣጣሉበት። ወፉ ምንም እንኳን መብረር የሚችል ወፍ ቢሆንም እንደ ዶሮ ከዶሮ መሃል ስላደገ ዶሮ ነኝ ብሎ አምኗል። ማንነቱን ለውጦ አቅሙን አሳንሶ እራሱን ሳያውቅ ሌሎች ዶሮዎች በነገሩት ብቻ አለመብበሩን አምኖ ኖረ። ክንፎቹን ታቅፎ ሌሎች ወፎች ሲበሩ እየቀና እድሉን እያማራረ ኖሮ ሞተ። መብረር ተፈጥሮው ሆኖ፤ አልበርም ብሎ በማመኑ ብቻ ወፍ ሆኖ ተወልዶ ዶሮ ሆኖ ምድርን ተሰናበተ።

የዚህ ወፍ ታሪክ የሁላችንም ታሪክ ነው። የምንመኘውን ነገር ለማድረግ ሁሉ ተሰጥቶን እያለ ሉሎች አይቻልም ስላሉን ብቻ፤ አንችልም ብለን በማመን የፈለግነው ኑሮ ሳንኖር እንሞታለን። እንደዛ ምስኪን ወፍ ከሌሎች መሃል ወድቀን ሌለችን እንሆናለን። ማንነታችን ሌሎች እየነገሩን እራሳችንን ሳናውቅ እድሜያችን ይገፋል። አቅማችንን ሌሎች እየለኩት ችሎታችንን እና ተሰጥዖዋችንን ሳንጠቀምበት ህይወታችን ያልፋል።

እስቲ እራሳቹህን ጠይቁት የወደቃቹሁት ከማን መካከል ነው? ይቻላል ይሳካል ከሚሉት ወይስ አይቻልም አይሳካም ከሚሉት? ወፉ መብረር እየቻለ ከዶሮ መሃል ስላደገ እና ዶሮ ነኝ ብሎ ስላሰበ መብረር ምንም እንኳን ቢመኝ ሳይበር ቀረ። የብዙዎቻችን ህይወት ከዚህ ብዙም አይለይም። ሁሉ ነገር እያለን ሌሎች ሲሞክሩት ስላላየን ብቻ የማይቻል መስሎን ምኞታችን ምኞት ብቻ ይሆንብናል። ይህን ነገር አስታውስ በባነነበት ሰዓት የሮጠ ሁሉ አረፈደ አይባልም። ነቅተን ዙሪያችንን እንመልከት፤ የከበቡንን እናስተውል። በዙሪያችን ያሉት አይቻልም ስላሉ ብቻ አይቻልም ብለን እራሳችንን ወደ ኋላ አናስቀረው።

ከዶሮ መሃል እንደወደቀ ወፍ አትሁን። አቅምህን ተጠቀምበት፤ ፍላጎትህን ኑረው፤ ምኞትህን እውን አድርገው። እራስህ መመልከት ከቻልክ አንተ ከምታስበው በላይ ታላቅ ሰው መሆንህን ትደርስበታለህ። ማህበረሰብ፤ ቤተሰብ፤ ጓደኛ ባወጣልህ መስፈርት እና መመዘኛ እራስህን አትመዘን፤ ይልቁንም እራሰህን በስራህ ፈትነው። ብዙዎች እንደ ወፍ ተወልደው እንደዶሮ ሞተዋል። ያ ክፉ እድል እኛን እንዳይገጥመን ሁላችንም የወደቅንበትን እንመልከት………ሌሎች መብረር ካልቻሉ አንተ መብረር አትችልም ማለት እኮ አይደለም።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments