“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

እርሳስ የሆነ ነፍስ ይስጠን

by | Jan 31, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories

ይህን ታሪክ ያገኘሁት ድንቅ ከሆነው የባህርማዶው ፀሃፊ፣ ከፓውሎ ኮሄሎ አጫጭር የታሪክ ስብስቦች ላይ ነው….የጎበጠን ህይወት ለማቅናት ከስነፅሁፍ የላቀ ሃይል ያለው ነገር ምን አለ? ለእኔ ምንም የለም። ይህችንም አጭር ፅሁፍ ሳነብ፣ ነፍሴ ሲሞረድ ተሰማኝ። እናም ለናንተም እንዲህ ተርጉሜ ላቀርበው ወደድኩኝ

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን አያቱ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል። እናም እናቱን እንዲህ ሲል ይጠይቃታል
“አያቴ ይህ የምትፅፊው ደብዳቤ ስለኛ ነው? እኔ እና አንቺ ስላደረግነው ነገር?”
አያቱም መልሰው “አዎ ልጄ የምፅፈው ስለ አንተ ነው፣ ነገር ግን ከምፅፈው ፅሁፍ ይበልጥ የምፅፍበት እርሳስ ትልቅ ትርጉም አለው፤ አንተም ስታድግ እና ትልቅ ሰው ስትሆን እንደዚህ እርሳስ እንድትሆንልኝ እመኛለው “ አሉት የልጅ ልጃቸውን ቁልቁል እየተመለከቱት።

ህፃኑም አያቱ በጨበጡት እርሳስ ላይ ምንም አዲስ ነገር ባለማየቱ ግራ ተጋብቶ “አያቴ አሁን የያዝሽው እርሳስ ከሌላው እርሳስ በምን ይለያል” አላቸው፤ አያቱም ቀጥለው
“አየህ ልጄ፤ ሁሉም ነገር እንዳመለካከትህ ይለያል፤ ይህ እርሳስ አምስት ድንቅ ባህሪዎች አሉት
አንደኛው፤ ይህ እርሳስ ያለ እጅ መፃፍ አይችልም፤ አንተም ምንም ድንቅ ተዓምር መስራት እና መከወን የምትችል ሰው ብትሆንም እጅ የሚሆንህ ፈጣሪ ከሌለ ወጋ የለውም።
ሁለተኛው፤ እንደምታየኝ እፅፍ እፅፍና እርሳሱ ሲዶለዱም አረፍ እልና በመቅረጫ እቀርፀዋለው፤ ይበልጥም ሹል ይሆናል። ሰውም ቢሆን በህይወቱ ብዙ ውጣ ውረዶች ያጋጥሙታል፤ ፈተናውም ሲያልፍ ግን ይበልጥ ሹል ይሆናል ማለት ነው።
ሶስተኛው ደግሞ ልጄ….. ይህ እርሳስ በማንኛውም ሰዓት የምሰራውን ስህተት በላጲስ አጥፍቼ እንዳስተካክል እድል ይሰጠኛል። ይህ ማለት በህይወታችን የምንፈፅማቸውን ስህተቶች ማስተካካል ነውር አይደለም፤ ይልቁንም እራሳችንን እያረምን እረጅም መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል:
አራተኛው ድንቅ ባህሪ ደግሞ፤ የዚህ እርሳስ ታላቅነት ያለው የውጪ አካሉ ላይ ማለትም አንጨቱ ላይ ሳይሆን፤ ውስጡ የተቀበረው ቀጭን ነገር ላይ ነው። ሰውም ቢሆን እንደዛው፤ ሁሌም ቢሆን ታላቅ ነገር የሚሰራው ውስጣችን ያለው ነገር ነው። እናም ልጄ ለውስጥህ ሰላም እና ደስታ ትኩረት ስጥ። ውስጥህ መልካም ነገር ከሌለ መልካም ነገር ማድረግ ይሳንሃል።
አምስተኛው እና የመጨረሻው ምን መሰለህ ልጄ….. ይህ እርሳስ በተፃፈበት ቁጥር ምልክት ይተዋል። አንተም እንደዛው…..በህይወት ጎዳና ስትጓዝ ምልክትህን መተውህ አይቀርምና በኑሮህ የምትወስናቸውን ነገሮች ሁሉ አስተውል። ምልክት ጥለው ማለፋቸው ስለማይቀር።” አሉት

ድንቅ ታሪክ አይደለም?……የዚህ  ገፅ አለማ ምንም ሳይሆን መልካም መልዕክትን ማስተላለፍ ብቻ ነው። እንደ እኔ አስተሳሰብ፤ ቤተሰብን፤ ማህበረሰብን፤ አገርን ብሎም አለምን ለመለወጥ ከማሰባችን በፊት፤ እራሳችንን መለወጥ መቻል አለብን። እስቲ አስቡት፤ ቀና አሳቢ ትውልድ ማነፅ ከቻልን፤ ምን አይነት ተዓምር መስራት እንደምንችል? ቅድሚያ ግን እራሳችንን ለመለወጥ እንትጋ……ይህንን መልዕክት ለሌሎችም እንድታስተላልፉልኝ አደራ እላለው፤ ካልተደሰታችሁበት ግን መተው መብታችህ ነው።

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments