ሰው በተስፋ ይኖራል፤ በተስፋ የጠወለገ ማንነቱን ያቀናል፤ የደረቀ ስሩን ያረጥባል። የስኬታማ ሰው መንደርደሪያው ተስፋ ነው። ተስፋ በዛሬ እና በነገ መካከል ያለች ድልድይ ናት……ተጠንቅቀው የሚራመዷት ድልድይ። ለመፍረስ ወዝ …ወዝ የምትል ቀጭን ድልድይ። አላዋቂዎች በጭካኔ ይረግጧታል…ያኔ ትፈርስና ከዛሬ ላይ ታስቀራቸዋለች….ነገን ሳይደርሱባት። ብልሆች ግን ቀስ እያሉ ይራመዱባታል….ያኔ ነገን እንደጓጉለት ታሳያቸዋለች።
የሴት ልብ………
ተስፋ እንደ ሴት ልጅ እንክብካቤን ትሻለች…..ስሜቷ ስስ ነው። ልቡን ሙሉ በሙሉ አምኖ ለሰጣት ….ከልቧ ትታመናለች። ለጠረጠራት ደግሞ…..በገዛ ፍቃዱ እምነቱን ስለገፈፈ ….ላትመለስ ትሸሸዋለች። እንደሴት ልጅ ሲያጨናንቋትም ይጨንቃታል፤ የተስፋን እና የሴትን ልብ ጨፍንገው ስለያዙት ከመሄድ አያስቀሩትም። ነጻነት እስትንፋሳቸው ነው፤ ያኔ የፈቃድ እስረኛ ይሆናሉ።
ሞኝ ካመረረ………..
ተስፋ ሞኝ ናት….የወደዳትን ስትወድ ከነምናምኑ ነው፤ ከነድክመታችን ፤ከነፍርሃታችን። ማንም የሌለ በመሰለን ጊዜ፤ እንደጥላ ከኋላ እየተጓዘች ለብቻ ቢጓዙት የሚረዝመውን መንገድ ተስፋ ታሳጥረዋለች።
“ተስፋ መቀነን ነው መቼም
የሰው ልጅ እይችለው የለም”….ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
0 Comments