“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሰው መንገዱን መረጠ ወይስ መንገዱ ሰውን?

by | Jan 29, 2015 | መነቃቂያ inspiring stories

እየተራመድክበት ባለው ጎዳና ላይ ለደቂቃ ቆም ብለህ አስብ፤ እንዴት ይህንን የህይወት መስመር መረጥከው? የህይወት አጋጣሚዎች ጎትተውህ ወይስ በምርጫህ? ብዙዎቻችን የተዘፈቅንበትን የህይወት ስህተት ላለማመን አሁን ካለንበት ጎዳና ጋር “እጣፋንታ” በሚሉት ፈሊጥ እንደተገናኘን እናስባለን።

እጣፋንታ እና እድል የሰው ልጅ የኑሮ ስህተቶቹን የሚሸፍንባቸው መጋረጃዎቹ ናቸው። እራሱን መመለክት የሚችል ሰው ለሚኖርበት ህይወት ሃላፊነት መውሰድ እይከብደውም። ነገር ግን የብዙዎቻችን አይኖች እንደአቀማመጣቸው ሁሉ ውጪ ውጪውን ብቻ ይመለከታሉ። ውደ ውስጥ መመለከት ይከብደናል፤ ምክንያቱም እራስን መመለከት ወኔ ይጠይቃልና።
የእያንዳንዱ ሰው የህይወት ጉዞ እርቀቱ ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን አጋምሰነዋል፤ አንዳንዶቻችን አገባድደነዋል፤ አንዳንዶቻችን ደግሞ ገና መጀመራችን ነው። በህይወት ጎዳና አቀርቅረን ስንጓዝ በእለት ተእለት ኑሯዎችን ውስጥ ያላስተዋልነው አንድ ቁምነገር ነገር አለ። እግራችን ያለፈቃዳችን ወደማንፈልገው እና ወደ አላዘዝነው ጎዳና ይዞን ሄዶ ያውቃል? ካልመራነው በቀር ወደ አልፈለግንበት ቦታ አድርሶን ያውቃል? በጭራሽ።

የገዛ እግራችን በገዛ ፈቃዳችን እና ምርጫን ብቻ ነው የሚምራው። በዚህ መንገድ ሂድ ስንለው ይሄዳል፤ ተመለስ ስንለው ይመለሳል፤ ፍጠን ስንለው ይፈጥናል፤ ቀስ በል ስንለው ይዘገያል እንጂ እራሱን በራሱ ፈፅሞ ሊያዝ አይችልም። አይምሮዋችን እየመራ እግራችን ወደፈለግንበት ጎዳና ያደርሰናል። ይህ የማይፋለስ ህግ ነው። ታዲያ ኑሮዋችን ከዚህ በምን ይለያል? እየሄድንበት ያለውን መንገድ ካልመረጥነው በቀር እንዴት ጀመርነው? አካላችንን አዘን ወደፈለግንበት ቦታ እንደሚወስደው ሁሉ ነፍሳችንን አዘን ወደምንፈልገው የህይወት መንገድ ልንመራት አንችልም? ትክክለኛው ጎዳና ካልሆነ ከመመለስ የሚያግደን ነገር ምንድን ነው? ነፍሳችንን ስትዘገይ ፍጠኚ …..ስትፈጥን ቀስ በይ ልንላት አይቻለንም?

ሰው መንገዱን መረጠ ወይስ መንገዱ ሰውን መረጠ? ።ታላላቅ ሰዎች ታላቅ የሆኑበት ቁልፍ ሚሰጥር መንገዳቸውን መምረጥ እንደሚችሉ ከጅምሩ በማመናቸው ነው። ውድቀታቸውን እና ስህተቶቻቸውን በእድል አና በእጣፋንታ መጋረጃዎች አልሸፈኑትም ይልቁንም እራሳቸውን ተመልከትው መንገዳቸውን ቀየሱ እንጂ። ማንም ሰው በመጀመሪያው ሙከራው ትክክለኛውን መንገድ አያገኝም። እየሄድክበት ያለው መንገድ ልክ ካልመሰለህ……ተመለስ…. መድረስ ወደፈለግክበት የሚያደርሰህን መንገድ ለመቀየስ አትፍራ……
መንገዳችንን መረጥነው እንጂ…….መንገዳችን እኛን አልመረጠንም…….

Mistre

Mistre

About Mistre I am the founder of this website www.asharaye.net. I enjoy learning and sharing personal development topics and love to entertain thought-provoking ideas. Writing to me is the best way to express my feelings and understandings about life in general. I am not an expert on any of the subject matters shared. I am just an individual with an opinion; therefore, anything I write and share on this platform is my understanding of the topic.

0 Comments