“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

“Be the change you want to see in the world.”

አሻራዬ መነቃቂያ ገፅ

ሰኞ ለት ተያየን በድንገት…..እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ

(በሚስጥረ አደራው) “ሰኞ ለት ተያየን በድንገት ማክሰኞ በህልሜ መጣ ሞኞ እሮብን ለፍቅር ተሳሰብን ሀሙስ ልቤን አለው ደስ ደስ አርብ ላይ ብንውል ሳንተያይ ቅዳሜ ተኛሁኝ ታምሜ እሁድ ቅልጥ ያለው መውደድ” ሰኞ ተጠንስሶ እሁድ ከፍጻሜ የደረሰ ፍቅር አጋጣሟችሁ ያውቃል? ፍቅር እንዲህ መንገዱ አልጋ በአልጋ ቢሆን ማን ይጠላ ነበር። ሰኞ ያገኙትን ሰው እሮብ ለፍቅር ማሰብ፤ ሀሙስ በደስታ መጥለቅለቅ፤ አርብ...

ዝምታ መልስ ይሆናል?

“ለዋልኩት ውለታ ይሄነው ወይ ውርሴ? ልፋቴ ድካሜ ይሄ ነው ወይ ውርሴ? እንግዲህ ምን ልበል ይህ ከሆነ ቅርሴ አሃ….ዝምታ ነው መልሴ ክፉ ደግ አትበል አታውጋ ምላሴ አሃ ዝምታ ነው መልሴ…….” ማዳመጫዬን ሰክቼ የማዳምጠው ይህንን ውብ የመሐሙድን የሀዘን ድባብ የተላበሰ ዘፈን ነበር። እውነት ግን ዝምታ ትክክለኛ መልስ ይሆናል? ሰው መልካም ስራ ሰርቶ የማይገባውን ክፍያ...

መጀመሪያ ይሙቀኝና ማገዶውን እጨምራለው!

በ ሚስጥረ አደራው “መጀመሪያ ይሙቀኛና ማገዶውን እጨምራለው ” የአብዛኛዎቻችን ሰዎች የህይወት መርህ ነው። ማገዶ ከሌለው ጓዳችን ውስጥ ሙቀት የምንጠብቀው ምን ከምን እንደሚቀድም ስለማናውቅ ነው። ይህ አለማወቃችን ነው ያሰብናቸው ነገሮች እንዳይሳኩ፤ የጠበቅናቸው ነገሮች እውን እንዳይሆኑ የሚያደርገው። በቂ ማገዶ ሳንጨምር ሙቀት ልናገኝ አንችልም። የቀዘቀዘው ኑሮዋችን እንዲሞቅ ከፈለግን በርከት ያለ ማገዶ...

የወርቅ እንቁላሎች

በየጊዜው በምንጸልየው ጸሎት ውስጥ  “የእዮብን ትዕግስት ስጠኝ” የምንለው የዚህችን ምድር ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መወጣጫው ትዕግስት  ስለሆነ ነው። ትዕግስት ማለት ነገሮች በጊዜያቸው እንዲሆኑ መጠበቅ ቢሆንም፤ ከምንም በላይ ትክክለኛው ትዕግስት በጥበቃችን ወቅት የምናሳየው አመለካከት እና ጽናት ጭምር ነው። እዚህ ላይ ኤዞፕ የጻፈው አንድ ተረት ትዝ አለኝ። ተረቱ እንዲህ ነው……. በድሮ ጊዜ...

የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል፤ በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ!

የተፈጥሮ አድናቂ ከሆነን የወንዝን ውበት በህሊናችን ለመሳል ባልተቸገርን። ወንዝ ውብት ብቻም ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋርም ጥልቅ ግንኙነት አለው። ወንዝ የብዙ ስልጣኔዎች ምንጭ፤ የስነጽሁፎች መጠንሰሻ፤ የፍቅር መጎንጫ ሆኖ በየስነጽሁፉ ተከትቦ እናገኘዋለን። የሰው ልጅ ህይወት በወንዝ ተመስሎ ሲታይ የኑሮዋችን ፍሰት እንዴት እንደሆነ በሶስተኛ አይን ያስመለክተናል። ስለወንዝ የተለያዩ ድንቅ አባባሎች ተነግረዋል። ለዛሬ...